72 - midrocmidroc-ceo.com/sites/default/files/newsletters/r_issue72.pdfaddis ababa, ethiopia 1...

16
1 Addis Ababa, Ethiopia ከሊቀመንበሩ ማኅደር Volume 14, Issue No. 72 July — August 2013 u¨<eØ Ñ뉋” Inside Pages 4 4 4 4 4 4 4 4 A BI-MONTHLY PUBLICATION OF THE OFFICE OF THE CHIEF EXECUTIVE OFFICER This Newsletter provides customers, employees, suppliers, shareholders and the community at large with current information on major performance and other activities of the companies under the leadership of the CEO ወደ ገጽ 2 ዞሯል ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ከ1,400 በላይ ተማሪዎቹን.......................... 2 ትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ የመጀመሪያውን የሀገር......................... 8 Public lecture was delivered on leadership ................. 9 Instructor publishes book on Ethiopian.....................10 ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ከ1,400 በላይ ተማሪዎቹን በዲግሪና በዲፕሎማ አስመረቀ Unity University graduated over 1,400 students ‹‹ሀገሪቱ ድህነትን ማሸነፍ የምትችለው በትምህርት ነው፡፡ ተመርቆ ሀገርን ማገልገል የበለጠ እርካታ እንደሚሠጥ አውቃችሁ ወደ ውጭ ሀገር የመኮብለል ሀሳብን እርግፍ አድርጋችሁ በመተው እዚሁ ሀገራችሁ ውስጥ ሠርታችሁ መለወጥ እንደምትችሉ እምነት ይኑራችሁ›› ክቡር ዶ/ር ሼክ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ በዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ የ2005 ዓ.ም. የ30ኛው ዙር ምሩቃን በዓል ላይ ካደረጉት ንግግር የተቀነጨበ፡፡ በግል አውሮፕላናችን ወደ ምሥራቁ ሀገራችን .......................10 የሠራተኞች ቅጥር፣ ዝውውር፣ የለቀቁ ................................13 ጫትና የወጣቱ ትውልድ ጥምረት .......................................13 መልዕክት ከሲኢኦ ..............................................................16 ክቡር ዶ/ር ሼክ ሙሐመድ ለተመራቂዎቹ ዲግሪና ዲፕሎማ ሲሰጡ

Upload: others

Post on 22-Feb-2020

5 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

Page 1: 72 - MIDROCmidroc-ceo.com/sites/default/files/Newsletters/R_Issue72.pdfAddis Ababa, Ethiopia 1 ከሊቀመንበሩ ማኅደር Volume 14, Issue No. 72 July — August 2013 u¨

1Addis Ababa, Ethiopia

ከሊቀመንበሩ ማኅደርVolume 14, Issue No. 72 July — August 2013

u¨<eØ Ñ뉋”

Inside Pages

4444

4

4

4

4

A BI-MONTHLY PUBLICATION OF THE Office Of the chief executive OfficerThis Newsletter provides customers, employees, suppliers, shareholders and the community at large with current information

on major performance and other activities of the companies under the leadership of the CEO

72

ወደ ገጽ 2 ዞሯል

ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ከ1,400 በላይ ተማሪዎቹን.......................... 2ትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ የመጀመሪያውን የሀገር......................... 8Public lecture was delivered on leadership ................. 9Instructor publishes book on Ethiopian.....................10

ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ከ1,400 በላይ ተማሪዎቹን በዲግሪና በዲፕሎማ አስመረቀUnity University graduated over 1,400 students

‹‹ሀገሪቱ ድህነትን ማሸነፍ የምትችለው በትምህርት ነው፡፡ ተመርቆ ሀገርን ማገልገል የበለጠ እርካታ እንደሚሠጥ አውቃችሁ

ወደ ውጭ ሀገር የመኮብለል ሀሳብን እርግፍ አድርጋችሁ በመተው እዚሁ ሀገራችሁ

ውስጥ ሠርታችሁ መለወጥ እንደምትችሉ እምነት ይኑራችሁ››

ክቡር ዶ/ር ሼክ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ በዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ የ2005 ዓ.ም. የ30ኛው ዙር ምሩቃን በዓል ላይ ካደረጉት ንግግር የተቀነጨበ፡፡

በግል አውሮፕላናችን ወደ ምሥራቁ ሀገራችን .......................10የሠራተኞች ቅጥር፣ ዝውውር፣ የለቀቁ ................................13ጫትና የወጣቱ ትውልድ ጥምረት .......................................13መልዕክት ከሲኢኦ ..............................................................16

ክቡር ዶ/ር ሼክ ሙሐመድ ለተመራቂዎቹ ዲግሪና ዲፕሎማ ሲሰጡ

Page 2: 72 - MIDROCmidroc-ceo.com/sites/default/files/Newsletters/R_Issue72.pdfAddis Ababa, Ethiopia 1 ከሊቀመንበሩ ማኅደር Volume 14, Issue No. 72 July — August 2013 u¨

2

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 72 July — August 2013

Addis Ababa, Ethiopia

ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ከ1,400 በላይ ተማሪዎቹን በዲግሪና በዲፕሎማ አስመረቀ

ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ፣ በሁለተኛና በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በዲፕሎማ እንዲሁም በሰርተፊኬት ያሠለጠናቸውን 1,241 ተማሪዎች በአዲስ አበባ፤ እንዲሁም 179 ተማሪዎች በአዳማ ለ30ኛ ጊዜ ነሐሴ 25 እና 26 ቀን 2005 ዓ.ም. በታላቅ ድምቀት አስመረቀ፡፡ የሚድሮክ ኢትዮጵያ ባለሀብትና የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ሊቀመንበር እንዲሁም በዕለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት ክቡር ዶ/ር ሼክ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ በተደረገው የምረቃ በዓል ላይ በመገኘት ለተመራቂዎቹ ዲግሪና ዲፕሎማ እንዲሁም በትምህርታቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ሽልማት ከሰጡ በኋላ ለኢትዮጵያ የወደፊት ዕድገት ክህሎትና ዕውቀት የተላበሰ አምራች ዜጋ በብዛት መኖሩ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሼክ ሙሐመድ አያይዘውም የመጀመሪያው የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የሆነው ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ቀዳሚ አርዓያ በመሆን የሰለጠኑ ዜጐችን ለማፍራት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን አስገንዘበዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በትምህርቱ መስክ ሴቶች የሚያደርጉት ተሳትፎ የላቀ በመሆኑ መደሰታቸውን የገለፁት ሼክ ሙሐመድ ከአሁኑ ይበልጥ የሴቶች ተሳትፎ ጐልብቶ ቢታይ ለሀገሪቱ የወደፊት ዕድገት ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው ተናግረዋል፡፡ በተለይ ወጣቶች በሀገራቸው በተመቻቸው የመማርና ሠርቶ ራስን የመቀየር ዕድል በመታገዝ ለልማትና ለዕድገት መነሳት እንዳለባቸው ካስገነዘቡ በኋላ ‹‹ሀገርን ጥሎ ለመሰደድና ለችግር ለመዳረግ ማሰብ አይኖርባችሁም፤ ስለዚህም ሀገራችሁ ላይ ሠርታችሁ ለመለወጥ ሞክሩ›› በማለት አሳስበዋል።የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አረጋ ይርዳው በበኩላቸው ከብዙ ድካም በኋላ ለምረቃው የበቁትን ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ በማለት በዩኒቨርሲቲው ቆይታቸው ያገኙትን ዕውቀት በይበልጥ በማሳደግ ለሀገር ዕድገት አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡ ዶ/ር አረጋ አያይዘውም ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በቀየሰው የረጅም ጊዜ ዕቅድና ስትራተጂ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛና በሦስተኛ ዲግሪ የማስተማር ተግባር፤ በተለይም በማኔጅመንትና በሊደርሺፕ ዘርፍ ልዩ ትኩረት እንደሚሠጥ ገልፀዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በምህንድስና ትምህርት ዘርፍ፤ በማዕድን፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በአርክቴክቸርና ኧርባን ፕላኒንግ እንዲሁም በሜካኒካል ኢንጂነሪንግ የጀመራቸው ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የጠቆሙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት፤ በጤናው መስክ በሰላም የነርሶች ኮሌጁ አማካኝነት ከፍተኛ ክሊኒክና ፋርማሲ ማስፋፋትን አቢይ ትኩረት እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡ ዶ/ር አረጋ ዩኒቨርሲቲው ወደ ዲግሪ ትምህርት የሚሸጋገሩ ተማሪዎችን የዕውቀት ይዘት ለማሻሻል የዩኒቲ አካዳሚን በመክፈት ከአፀደህፃናት እስከ አራተኛ ክፍል ድረስ የመማሪያ ክፍሎችን በማዘጋጀት በመስከረም 2006 ዓ.ም. ሥራ ለመጀመር መዘጋጀቱን ጠቁመው ይህ ሥራ ዩኒቨርሲቲው ቀደም ሲል ይዞ የተነሳውን የጥራት ማዕከል የመሆን ዕቅድ ተግባራዊ እንደሚያደርግ አስገንዝበዋል፡፡ክቡር ዶ/ር ሼክ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ በአገልግሎት ዘመናቸው ወቅት የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ሁለት መምህራን አቶ መኩሪያ ኃይሌና አቶ ሙሉጌታ ካብትይመር እንዲሁም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ለሆኑት ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ ለሀገሪቱ ባበረከቱት አስተዋፅኦ የዓመቱን የሊቀመንበሩ ሜዳሊያ ሸልመዋል፡፡ በሌላም በኩል ዩኒቨርሲቲው በአዳማ ልዩ ካምፓሱ በመጀመሪያ ዲግሪና በዲፕሎማ መርሀግብር ያሠለጠናቸውን 179 ተማሪዎች እሁድ ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም. በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አስመርቋል። በዕለቱ በትምህርታቸው ብልጫ ያመጡ ተማሪዎች የፕሬዚዳንቱን ዋንጫና ሜዳሊያ እንዲሁም ዲግሪና ዲፕሎማቸውን ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ከዶ/ር አረጋ ይርዳው እጅ ተቀብለዋል፡፡ ተመራቂዎች በመደበኛ፣ በማታና በርቀት በተከታታይ ትምህርት ከሁለት እስከ አምስት ዓመት ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው፡፡

Unity University, member of the MIDROC Ethiopia Technology Group Companies, has graduated its 30th batch of graduates consisting 1,241 students from Addis Ababa and 179 from Adama with MA, MBA, BA, Diploma and Certificate upon completion of two to five years of studies on August 31, and September 1, 2013. The owner and Chairman of MIDROC Ethiopia Investment Group Dr. Sheik Mohammed Hussein Ali Al-Amoudi was the guest of honor at Addis Ababa Millennium hall and handed out Degrees, Diplomas and Certificates to the graduates and awards to outstanding students. Speaking at the graduation ceremony Sheik Mohammed said that, we need to have skilled and qualified productive force in greater number for future growth of Ethiopia. Sheik Mohammed also noted that Unity University’s achievement as being the first private university and a model in the country has well been recognized. Unity University's president Dr. Arega Yirdaw on his part conveyed his congratulatory message and urged graduates to effectively discharge their responsibilities by translating the knowledge they have acquired in the university into deeds for the benefit of their country, their families and themselves. Dr. Arega noted that, as a private higher institution that is committed to play a leading role in advancing the cause of education in the country, Unity University had already taken a pioneer role of offering post graduate programmes in the field of Business Administration and Development Economics. Preparations are also finalized to launch Doctorate Degree in Management and Leadership. He also stated that the University identified four major areas of focus, Business Economics and Leadership Executive program as one area, Engineering Science, Information Technology, Architecture and Urban Planning and Mechanical Engineering as second. Medical college or University clinic as third. The fourth, Unity Academy, is recently opened to integrate Kindergarten, Primary, Secondary and preparatory school to produce outstanding students. This last area of focus is believed to help achieve the motto of the university being a quality house. “The chairman, Sheik Mohammed Hussein Ali Al-Amoudi award for distinguished services” was awarded to two selected winners Ato Mekuria Haile and Ato Mulugeta Kabtimer. W/ro Shitaye Minale, Deputy Speaker of the House of Peoples' Representatives received the award for her great contribution to her country. Meanwhile the University graduated 179 students from Adama Special Campus on September 1st, 2013 at Abagada Hall. The graduates received their degrees, diplomas and awards from the president, Dr. Arega Yirdaw. The total graduates followed their education in Regular, Extension, Distance and Continuing Education as well as Technical and Vocational Education Training Programs.

Unity University graduated over 1,400 students

Page 3: 72 - MIDROCmidroc-ceo.com/sites/default/files/Newsletters/R_Issue72.pdfAddis Ababa, Ethiopia 1 ከሊቀመንበሩ ማኅደር Volume 14, Issue No. 72 July — August 2013 u¨

3

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 72 July — August 2013

Addis Ababa, Ethiopia

የአዲስ አበባ ገርጂ ካምፓስ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት በሚሊኒየም አዳራሽ

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት፣ ሊቀመንበርና ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት የዩኒቨርሲቲው የሴኔት አባላት በከፊል

ተጋባዥ እንግዶች በከፊልየዩኒቨርሲቲው መምህራን

የተመራቂ ተማሪዎች ቤተሰቦች በከፊል

Page 4: 72 - MIDROCmidroc-ceo.com/sites/default/files/Newsletters/R_Issue72.pdfAddis Ababa, Ethiopia 1 ከሊቀመንበሩ ማኅደር Volume 14, Issue No. 72 July — August 2013 u¨

4

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 72 July — August 2013

Addis Ababa, Ethiopia

የአዲስ አበባ ገርጂ ካምፓስ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ...

የዕለቱ ተመራቂዎች

Page 5: 72 - MIDROCmidroc-ceo.com/sites/default/files/Newsletters/R_Issue72.pdfAddis Ababa, Ethiopia 1 ከሊቀመንበሩ ማኅደር Volume 14, Issue No. 72 July — August 2013 u¨

5

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 72 July — August 2013

Addis Ababa, Ethiopia

በትምህርታቸው ብልጫ ያገኙ ሽልማት በተቀበሉበት ወቅት (አዲስ አበባ ገርጂ ካምፓስ እና አዳማ ልዩ ካምፓስ)

ፍስሐ ሞላ በሪ - /ከአዲስ አበባ ካምፓስ/ በማኔጅመንት (ኤም.ቢ.ኤ.) ሁለተኛ ዲግሪ

ራሄል ዓለማየሁ ደመቀ - /ከአዲስ አበባ ካምፓስ/ በአካውንቲንግ ዲፕሎማ

ቢላል አክደር አሊ - /ከአዲስ አበባ ካምፓስ/ በማኔጅመንት የመጀመሪያ ዲግሪ

አበባየሁ ገላው ዮሐንስ - /ከአዳማ ልዩ ካምፓስ/ በአካውንቲንግ እና ፋይናንስ በዲፕሎማ

ዝናሽ ጌታቸው ደጀኑ - /ከአዳማ ልዩ ካምፓስ/በማኔጅመንት በመጀመሪያ ዲግሪ

Page 6: 72 - MIDROCmidroc-ceo.com/sites/default/files/Newsletters/R_Issue72.pdfAddis Ababa, Ethiopia 1 ከሊቀመንበሩ ማኅደር Volume 14, Issue No. 72 July — August 2013 u¨

6

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 72 July — August 2013

Addis Ababa, Ethiopia

በአገልግሎት ዘመናቸው የላቀ አገልግሎት ያበረከቱት የዓመቱ ተሸላሚዎች በስተግራ አቶ መኩሪያ ኃይሌ በስተቀኝ አቶ ሙሉጌታ ካብትይመር

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ ከሽልማቱ በኋላ

Page 7: 72 - MIDROCmidroc-ceo.com/sites/default/files/Newsletters/R_Issue72.pdfAddis Ababa, Ethiopia 1 ከሊቀመንበሩ ማኅደር Volume 14, Issue No. 72 July — August 2013 u¨

7

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 72 July — August 2013

Addis Ababa, Ethiopia

የአዳማ ልዩ ካምፓስ የምረቃ ሥነሥርዓት በአባገዳ አዳራሽ

የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አረጋ ይርዳው የሴኔት አባላት

የተመራቂ ቤተሰቦች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች

የዕለቱ ተመራቂዎች በከፊል

Page 8: 72 - MIDROCmidroc-ceo.com/sites/default/files/Newsletters/R_Issue72.pdfAddis Ababa, Ethiopia 1 ከሊቀመንበሩ ማኅደር Volume 14, Issue No. 72 July — August 2013 u¨

8

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 72 July — August 2013

Addis Ababa, Ethiopia

ትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ የመጀመሪያውን የሀገር ውስጥ

በረራ አካሄደ

Trans Nation Airways has conducted its First Local Flight

after the ban lift

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች አካል የሆነው ትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ ኃ.የተ.የግ.ማ. /ቴ.ኤን.ኤ/ በግል የአውሮፕላን ኦፕሬተሮች ላይ የተጣለው መንገደኞችን የመጫን ገደብ ከተነሳ በኋላ የመጀመሪያውን ልዩ የሀገር ውሰጥ በረራ በማድረግ የቴክኖሎጂ ግሩፑን ሠራተኞች ሐምሌ 18 ቀን 2005 ዓ.ም. ወደ ድሬዳዋ በማጓጓዝ አገልግሎት ሠጠ፡፡

ትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ የመጀመሪያውን የሀገር ውስጥ በረራ ሲያካሂድ ለንግስ ወደ ቁልቢ ገብርኤል የሚጓዙ የቴክኖሎጂ ግሩፑን ሠራተኞች ይዞ ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ የደርሶ መልስ ጉዞ በማከናወን የተሳካ በረራ አድርጓል፡፡

37 መንገደኞችን በሚይዘው በዚሁ አውሮፕላን የደርሶ መልስ ጉዞ ያደረጉት የኩባንያዎቹ ሠራተኞች በተመጣጣኝ ክፍያና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ በዓሉን ለማክበር ችለዋል፡፡

በዕለቱ መንገደኞቹ ወደ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለጉዞ ሲዘጋጁ ዶ/ር አረጋ ይርዳው በመቻሬ ግቢ በመገኘት ለተጓዦች ሽኝት አድርገውላቸዋል፡፡

መንገደኞቹ በድሬዳዋ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግ.ማ. የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ እናትዓለም ከበደ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን፤ በድሬዳዋ ራስ ሆቴልም የምሳ ግብዣ ተደርጐላቸዋል፡፡ በመቀጠልም ከድሬዳዋ ንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ አስጐብኚ በመጋበዝ ስለድሬዳዋ አመሠራረትና በአካባቢዋ ስለሚገኙ የቱሪስት መስህቦች ገለፃ ተደርጓል፡፡

ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግ.ማ. የድሬዳዋ ቅርንጫፍ መ/ቤት ለተጓዞቹ በቁልቢ ገብርዔል ቤተክርስቲያን አካባቢ ማረፊያ የሚሆኑ ስምንት ያህል ድንኳኖችን በመትከል አገልግሎት አንዲያገኙ አድርጓል፡፡

እንደ ሌሎች የግል አውሮፕላን ኦፕሬተሮች ሁሉ ትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ መንገደኞችን የመጫን አቅሙ በ20 መንገደኞች ብቻ የተገደበ ስለነበር በአገር ውስጥ መንገደኞችን የማጓጓዙን ሥራ አዋጪ ስለማያደርገው እንደ ሩዋንዳ፣ ኬንያ፣ ሱዳን እና ሊቢያ ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ሲሰራ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

የትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ ዋና ሥራ አስኪያጅ ካፒቴን ተረፈ ኃይሌ ተጓዦቹ ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ ሲጓዙ አሸኛኘትና ወደ አዲስ አበባ በተመለሱበት ወቅትም በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት አቀባበል አድርገዋል፡፡

ትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ ከ20 መንገደኞች በላይ የመጫን ገደቡ የተነሳ በመሆኑ የጉዞ አድማሱን በማስፋት በሀገር ወስጥ ወደተለያዩ አካባቢዎች በረራ በማካሄድ ልዩ ልዩ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎችን ለመጐብኘት እንዲሁም ከቦታ ቦታ መጓጓዝ ለሚፈልጉ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱን

የኩባንያው ዋና ሥራ አስኪያጅ ገልፀዋል፡፡

A member of the MIDROC Ethiopia Technology Group Companies, Trans Nation Airways P.L.C., has started operating local flight following the ban lift on private flight operators. This is the first local flight carrying Technology Group’s employees from Addis Ababa to Dire Dawa on 25 July 2013.

TNA conducted a successful flight with its Dash 8 having a capacity of 37 passengers for the Technology Group employees who left for the East to take part in Qulubi Gebriel annual event at a very reasonable price.

While the employees prepared themselves to depart to Bole International Airport, Dr. Arega Yirdaw, MIDROC Ethiopia CEO saw them off at Mechare Meda Corporate Center.

When the number of passengers for private operators was limited to 20, TNA used to lease its Airplanes to different African countries like Rwanda, Kenya, Sudan and Libya as it would not be lucrative to operate locally.

TNA’s General Manager Captain Terefe Haile saw the passengers off while they were leaving to Dire Dawa and welcomed them when they came back at Bole International Airport.

According to the General Manager, following the ban lift, TNA is on the move in arranging flight to tourist destinations and various other locations in different part of the country availing option to users.

ተጓዦች ወደ አውሮፕላኑ በመግባት ላይ እያሉ

Page 9: 72 - MIDROCmidroc-ceo.com/sites/default/files/Newsletters/R_Issue72.pdfAddis Ababa, Ethiopia 1 ከሊቀመንበሩ ማኅደር Volume 14, Issue No. 72 July — August 2013 u¨

9

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 72 July — August 2013

Addis Ababa, Ethiopia

Public lecture was delivered on leadershipDr. Lenneal J. Hendersen, Guest Lecturer from the Fielding Graduate University, School of Educational Leadership and change, delivered a public lecture on “Leadership: Research, Action and Rethinking Education” at Unity University Gerji Campus on July 10, 2013.

Following the scholarly issues raised in the presentation, the floor was open for discussion whereby participants made interventions by way of raising pertinent questions, and forwarding constructive comments, to which Dr. Hendersen responded accordingly.

Dr. Arega Yirdaw, president of Unity University and CEO of MIDROC Ethiopia, in his closing remarks pointed out that the public lecture was preliminary to a training programme planned to be conducted for instructors of the University which is believed

to increase the quality of education delivered.

He also noted “If we need to upgrade the quality of education, what we need to do is to improve the quality of instructors; and we would like Unity University to be an example in the country.”

Dr. Hendersen besides his rich profile he is involved in various areas of academic, non-academic, research and administrative activities commensurate with his wide area of studies and experience. As an international lecturer, his works have taken him to various countries in Africa, Asia, Europe and the Middle-east.

The public lecture was attended by invited guests, academic staff of the University and higher management bodies of the MIDROC Ethiopia Technology Group Companies.

Dr. Lenneal J. Hendersen while delivering a public lecture

Unity University President, Dr. Arega Yirdaw while delivering a speech during the closing ceremony

Page 10: 72 - MIDROCmidroc-ceo.com/sites/default/files/Newsletters/R_Issue72.pdfAddis Ababa, Ethiopia 1 ከሊቀመንበሩ ማኅደር Volume 14, Issue No. 72 July — August 2013 u¨

10

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 72 July — August 2013

Addis Ababa, Ethiopia

ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢው ደመናማ ነው፡፡ ወቅቱ የክረምት ጊዜ በመሆኑ አየሩ ቀዝቃዛ፤ ቀናቱ ዝናባማ መሆን ከጀመረ ሰንበትበት ብሏል፡፡ የዛሬው ዕለትም ከወትሮው የተለየ አይደለም፤ በአውሮፕላን ማረፊያው ፈካ ያለ የአየር ሁኔታ አይታይም፡፡

37 መንገደኞችና አምስት የአውሮፕላኑ ሠራተኞች ለጉዞ ተዘጋጅተናል፡፡ አውሮፕላኑ የማኮብኮቢያ መስመሩን ጨርሶ የአየር ላይ ጉዞውን ከጀመረ አሥር ደቂቃ ተቆጥሯል፡፡ በአውሮፕላኑ የድምጽ ማሰራጫ አንድ ድምፅ መሰማት ጀመረ፡- ‹‹ክቡራን እንግዶቻችን እንኳን ለቁልቢ በዓል አደረሳችሁ፤ አብራችሁን ለመጓዝ ከእኛ ጋር ስለተገኛችሁ በጣም እናመሠግናለን። አቅጣጫችን ወደ ምሥራቅ ነው፤ አሁን ያለንበት የበረራ ከፍታ 19 ሺህ ጫማ ነው፤ የአየሩ ሙቀት መጠን 23 ዲግሪ ሴንቲግሬድ፤ ከዚህ በኋላ ለ45 ደቂቃ አብረን እንጓዛለን፤ መልካም ጉዞ›› በማለት ንግግሩን አጠናቀቀ።

ከአውሮፕላኑ ተጓዦች አንድም ድምፅ አይሠማም፡፡ በርካቶች በፍርሀት

የተዋጡ ይመስላል፤ በእርግጥም በአውሮፕላን ሄዶ የማያውቅ ብዙ ሰው እንዳለ መረዳት ይቻላል፡፡ ሌላው ቀርቶ በአውሮፕላን መስኮት እንኳ ማየት የማይፈልግ በርካታ ሰው ነው፡፡ ግማሹ አይኑን ጨፍኖ ነጠላውን ተከናንቦ ፀሎት ያደርጋል፤ ግማሹ የአውሮፕላኑን የውስጥ አካል አንድ በአንድ የሚቆጥር ይመስላል፡፡ ያም ሆነ ይህ ጉዞአችን የተጀመረው በፀሎት ነው። እኛው በእኛው ጉዞአችንን በሰላም አስጀምሮ እንዲያስጨርሰን ሁላችንም በአንድ ድምፅ ፀልየናል፡፡

ሐምሌ 18 ቀን 2005 ዓ.ም. ማለዳ ከመቻሬ ሜዳ በመነሳት ጉዞውን ወደ ቁልቢ ገብርኤል ሊያደርግ የተሰባሰበውን የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች ሠራተኞች «በሰላም ደርሳችሁ ተመለሱ» በማለት በማለዳ ተገኝተው ሽኝት ያደረጉት የሚድሮክ ኢትዮጵያ ሲኢኦ ዶ/ር አረጋ ይርዳው ነበሩ፡፡

Instructor publishes book on Ethiopian calendarA new book on Ethiopian Calendar, authored by Ato Fassil Tasew, Department Head, Economics, College of Business, Economics and Social Sciences, Unity University, was launched on July 20, 2013, at Gerji Campus. The 200-page book, which was printed at the Banawi Printing Press, mainly focuses on “Pagumen”, which is the five or six-day “thirteenth month” of the Ethiopian Calendar year. It is an outcome of thorough research.Announcing the purpose of the gathering, which brought together invited guests as well as family and friends of the Author in the presence of Dr. Arega Yirdaw, President of Unity University, Wzo. Tegest Hiruy, Administrative Assistant to the President, noted that Unity University organized the launching event, which is the first of its kind, in collaboration with the Author. She congratulated the Author and requested Dr. Seltene Seyoum, Director of the Research and Publications Office (RPO), Unity University, to chair the launching procedure.Dr. Seltene underlined that the book is an outcome of scientific research on Ethiopian Calendar. He went on to note that foreign scholars depict Ethiopia as “a country of diversities”. This diversity, he said, is not only in landscape or topography; but also in culture and tradition. Within the diversity, there is a uniting factor, he said, adding that the foreign scholars also call Ethiopia “the home of humanoids”.Going into further details, Dr. Seltene stated that Ethiopia has its own alphabets and “this gives the country a unique position in history”. He went on to note that Ethiopia also has its own calendar. The RPO Director stressed that Ethiopia is not only a country that staunchly fought for the independence of Africa. It is also a country that has never been colonized by an external force, except for the five years of occupation by Fascist Italian forces. This is also another feature that gives Ethiopia a unique position in history, Dr. Seltene stressed.Following this, Dr. Seltene gave a brief account of the education and work experiences of Ato Fassil and touched on highlights of the book. He underlined, “Whereas we just call ‘Pagumen’ the ‘thirteenth month’ of the Ethiopian Calendar year, the book gives the issue a scientific analysis based on research findings.” Having said this, the Chairperson invited two scholars to present their reviews of the book. Ato Terfasa Digga, Dean, Students’ Affairs, Unity University, and Dr. Girma Gizaw, owner and General Manager of the Training and Consultancy Services Centre and former Lecturer at Unity University, delivered their presentations.Ato Terfasa presented his review, which focused on seven points, that is, the overall formatting, the objective of the book, main findings of the research, sources of data, glossary of words, readability of the book, editorial works and proofreading. He went through the strengths and flaws of the book and concluded

that Ato Fassil’s work is a pioneer in the University; and “since there are many scholars in the University, many such works are expected to come forward”. Speaking on his part, Dr. Girma pointed out, “Ato Fassil’s work is something that calls for a lot of courage. Since it is an original work, it invites critics from not only local but also international scholars. It involves a lot of challenging ideas.”Following the reviews presented by the two scholars, the floor was open for discussion. Highlights among the issues raised during the discussion focused on the originality of the work and the need to translate the book into English. It was also noted that Ato Fassil’s work is an ice-breaker for those scholars who have the capacity but are not daring enough or are reluctant to publish such research works. One speaker said, “The work is clear indication of the fact that if we have the courage to write, there are numerous unique features that we could write on.”In his closing remark, Dr. Arega Yirdaw said that it is because Unity wanted to develop the culture and encourage scholars to write books that the University intervened in organizing the launching event. “Had the University been fully involved in the publication of the book, we could have further scrutinized the work. We are fully behind the publication of books by our scholars”, he said. The President further noted that the culture of reading has diminished. “It is the responsibility of the scholars of the University to revive this culture”, he underlined.Dr. Arega reminded the scholars that the research works and publications should give practical answers to the problems of development in the country. He reiterated that the launching event had provided the University with the opportunity to arouse the interests of those scholars who hesitate to do research works and publish their findings into books. Dr. Arega granted a sum of money to Ato Fassil, as a token of the University’s support to his work. He also ordered the purchase of 50 of the newly-published book for the Library. Unity University is prepared to meaningfully support such works in the future, Dr. Arega promised.In conclusion, Ato Fassil expressed his sincere thanks to all those who contributed to the success of his work and his special thanks to Unity University for the assistance accorded him. He also thanked all in attendance for coming to the event and expressed his appreciation for the interventions made and comments forwarded during the discussion.

ወደ ገጽ 11 ዞሯል

በግል አውሮፕላናችን ወደ ምሥራቁ ሀገራችን /የጉዞ ማስታወሻ/

Page 11: 72 - MIDROCmidroc-ceo.com/sites/default/files/Newsletters/R_Issue72.pdfAddis Ababa, Ethiopia 1 ከሊቀመንበሩ ማኅደር Volume 14, Issue No. 72 July — August 2013 u¨

11

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 72 July — August 2013

Addis Ababa, Ethiopia

በዓሉን ካለችግር በቦታው ተገኝተው እንዲያከብሩ ትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ ኃ.የተ.የግ.ማ /ቲ.ኤን.ኤ/ የማጓጓዝ አገልግሎቱን ለሠራተኞች በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ፤ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ደግሞ የየኩባንያዎቹ ሠራተኞች እንዲሆኑ ሲኢኦ ዶ/ር አረጋ በመፍቀዳቸው ከመቻሬ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ፣ ከአውሮፕላን ማረፊያ እስከ ድሬዳዋ-ቁልቢ ካለምንም ውጣ ውረድ የተሳካ ጉዞ ተከናውኗል፡፡

ትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ ኃ.የተ.የግ.ማ /ቲ.ኤን.ኤ/ እ.ኤ.አ. በ2004 የአየር የበረራ ፈቃድ ከሲቪል አቪዬሽን፤ የሥራ ፈቃዱን ደግሞ ከንግድ ሚኒስቴር ካገኘ በኋላ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ነበር፡፡ ይህ የሆነው ደግሞ በአገር ውስጥ የግል አውሮፕላን በረራ ፈቃድ እስከ ሃያ መንገደኞች ብቻ መጫን እንጂ ከዚያ በላይ የተጓዦች መቀመጫ መጠቀም እንደማይቻል በሕግ የተደነገገ ስለነበረ ነው፡፡

አንድ ለእናቱ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁሉንም የበረራ መዳረሻዎች ብቻውን ለመድረስ ከላይ እታች ሲማስን ‹‹እኛም አስተዋፅኦ ማድረግ እንችላለን›› ያሉ የግል የበረራ አገልግሎት ሠጪ ተቋማት መፈጠራቸው ደስ የሚያሰኝ ቢሆንም የተጓዦች ቁጥር በአገር ውስጥ በረራ እንኳ በአነስተኛ መጠን መገደቡ ስጋ ሰጥቶ ቢላዋ የመከልከል ያህል ነበር፡፡

ይህ በመሆኑም በሥራ ላይ ለመዋል በከፍተኛ ወጪ ተገዝተው የመጡት አውሮፕላኖች የሥራ እጦት ችግር ስለገጠማቸው ለአገር ቤት ወገናቸው አገልግሎት መስጠት ባለመቻላቸው ወደ ጐረቤት አገራት ፊታቸውን አዞሩ፡፡ የአፍሪካ አገራት ግን የአውሮፕላኖቹን አገልግሎት አልገፈተሩም፤ እጃቸውን ዘርግተው ‹‹እንኳን ደህና መጣችሁልን›› በማለት ተቀበሏቸው እንጂ!

ከብዙ ዓመታት የውጭ አገር አገልግሎት በኋላ በአገር ውስጥ የመንገደኞች ቁጥር መጨመር በሕግ ተሻሽሎ ወደ 50 መቀመጫ በማደጉ የትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ አውሮፕላን የመጀመሪያውን የአገር ውሰጥ በረራ ለማድረግ እነሆ የየኩባንያዎቹን ሠራተኞች ይዞ በረራውን ወደ ድሬዳዋ አደረገ፡፡

አውሮፕላኑ ደመናውን ሰንጥቆ የመጨረሻ የበረራ ከፍታውን ይዞ ከላይና ከታች የተነደፈ ጥጥ በሚመስለው ደመና መካከል ይንሳፈፋል። ዙሪያችንን የምናስተውለው ወሰን የሌለው ከባቢ አየር ብቻ ነው፡፡ በዚህ መካከል የዚህ ፅሁፍ ፀሐፊ የደህንነት ቀበቶዬን ፈትቼ ካሜራዬን አስተካክዬ ተጓዦችን ፎቶግራፍ ለማንሳት በአውሮፕላኑ ተንቀሳቀስኩ፡፡ የቻልኩትን ያህል ከፊትም ከኋላም እየተንቀሳቀስኩ ቪዲዮም ቀረጽኩ፡፡

በዚህ ድርጊቴ የአውሮፕላኑን ጉዞ ለማስተጓጐል ሞከርክ የሚለኝ የለም፤ ይህ የኩባንያችን አውሮፕላን ነው፤ የሁላችንም ንብረት ነው፤ በሌላ አየር መንገድ የተሳፈርኩ ቢሆን ይህንን አይነቱን እንቅስቃሴ ማድረግ እንደማልችል አውቃለሁ፤ እንዲህ እንደልብ ከታች እስከ ላይ መንቀሳቀስ ቀርቶ ወደ መጸዳጃ ሲሄዱ እንኳ በአይነ ቁራኛ የሚከታተል ሞልቷል። ይህ የሚደረገው ደግሞ የአውሮፕላን ጠለፋን ለመከላከል ነው፡፡ እኛ ግን የራሳችንን አውሮፕላን ደህንነት ከመጠበቅ ሌላ አማራጭ የለንም፡፡ ስለዚህም በሰላም እንድንደርስ በፀሎት የጀመርነው ጉዞ ፍሬያማ እየሆነ ነው፡፡

መጀመሪያ ላይ ከበረራ ክፍሉ የመጣው ድምፅ አሁንም መደመጥ ጀምሯል። ‹‹የድሬዳዋ ጉዞአችንን ለማጠናቀቅ 15 ደቂቃ ብቻ ቀርቶናል፤ የድሬዳዋ አየር ፀባይ ደመናማ ነው፤ የአየሩ ሙቀት 25 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ነው፤ መልካም ጉዞ›› በማለት ንግግሩን አጠናቀቀ፡፡

ሁላችንም የመቀመጫ ቀበቶአችንን አጠበቅን፤ አውሮፕላኑ በወጣበት ፍጥነት ሳይሆን ቀስ እያለ ወደ መሬት እየቀረበ ነው፡፡ አሁን የድሬዳዋ ገጠራማ ቦታዎች፣ ጐጆ ቤቶች፣ ፍየሎችና ግመሎች ለአይን ደቃቅ ሆነው ይታያሉ፡፡ አውሮፕላኑ የማረፊያ ቦታው ላይ ደርሷል፡፡ የአውሮፕላኑ የኋላ እግሮች መንደርደሪያውን ሲነኩ ሁሉም ተጓዥ እልልታውን አቀለጠው፡፡ ነፍሳቸው በአፋቸው ልትወጣ የደረሱ በርካቶች ነበሩ፡፡ በእልልታቸው ነፍስ የዘሩ ይመስላሉ፡፡ በፀጥታ ተውጦ የቆየው የአውሮፕላኑ ክፍል በአንድ ጊዜ በጫጫታ ተሞላ፡፡

በድሬዳዋ አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረስን አቀባበል ያደረጉልን በድሬዳዋ የሚገኘው የኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግ.ማ. ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ እናትዓለም ከበደ ነበሩ፡፡ በተዘጋጁልን ሁለት ሎንቺን መኪኖች ጉዞአችንን ወደ ራስ ሆቴል አድርገን የምሳ ቆይታ በዚያ አደረግን፡፡ የኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃላ.የተ.የግ.ማ. የማኔጅመንት አባላት የምሳ ግብዣ ብቻ አይደለም ያደረጉልን ስለ ድሬዳዋ ከተማ አመሠራረት፣ በውስጧና በዙሪያዋ ያሉ የቱሪስት መስህቦችን እንድንተዋወቅ ከድሬዳዋ ንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የቱሪዝም ባለሙያ የሆኑትን አቶ ግዛው ሀይሌን በመጋበዝ ሰፊ ግንዛቤ እንድናገኝ አመቻችተዋል፡፡

በግል አውሮፕላናችን ወደ ምሥራቁ ...

ወደ ገጽ 12 ዞሯል

የቁልቢ ገብርዔል ቤተክርስቲያን

የተጓዥ ቡድኑ አባላት

የቲ.ኤን.ኤ አውሮፕላን አብራሪዎች

ተጓዦች በድሬዳዋ አየር ማረፊያ

ቆይታ በድሬዳዋ ራስ ሆቴል

Page 12: 72 - MIDROCmidroc-ceo.com/sites/default/files/Newsletters/R_Issue72.pdfAddis Ababa, Ethiopia 1 ከሊቀመንበሩ ማኅደር Volume 14, Issue No. 72 July — August 2013 u¨

12

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 72 July — August 2013

Addis Ababa, Ethiopia

ከቀኑ 8፡34 ያመለክታል፡፡ ከራስ ሆቴል ቆይታ በኋላ በየመኪኖቻችን ገብተን ጉዞአችንን ወደ ቁልቢ ገብርኤል አድርገናል፡፡ በተጓዦች ላይ የደስታ ስሜት ይነበባል፡፡ በቡድን ተደራጅቶ መጓዝ ጥቅሙ የላቀ መሆኑን ተገንዝበናል፡፡

ወደ ቁልቢ ያደረግነው ጉዞ ካለምንም እንከን ተጠናቅቋል፡፡ በዚያ ስንደርስ ስምንት አነስተኛ ድንኳኖች ተተክለው መሬቱ ላይ የሳር ጉዝጓዝ ተደርጐ ስለጠበቀን የያዝነውን የጉዞ ሻንጣ በመረጥነው ድንኳን እያስገባን አረፍ አልን፡፡

የቁልቢ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ዙሪያ ከየቦታው በተሰባሰቡ በርካታ ሰዎች ተሞልቷል፤ መኪኖች ቀድመው በሄዱበት አኳኋን ተደርድረው ለሌሎች መኪኖች መተላለፊያ መስመር በማመቻቸት በሥርዓት ቆመዋል፡፡

ከዚህ ሰዓት በኋላ ሁሉም እንደየፍላጐቱ ፀሎቱን ለማድረገ በየአቅጣጫው ተበታትኗል፡፡ በአካባቢው የሚታየው ትዕይንት እጅግ ያስገርማል በቁልቢ ገብርኤል ንግሥ በዓል የሚታየው ተዓምር ልዩ ነው በቤተክርስቲያኑ ዙሪያ በስለት የመጡ ሠንጋዎች ይታረዳሉ፤ ለእኔ ቢጤዎች ሥጋቸው ይከፋፈላል፤ አዲስ አበባ ላይ አንድ ኪሎ ሥጋ ከአንድ መቶ ሀምሳ ብር በላይ የሚሸጠው እዚያ አምስትና ስድስት ኪሎ ሥጋ አንድ ሰው በላስቲክ ተሸክሞ ሲሄድ ማየት የሚያስገርም አይሆንም፡፡ ምክንያቱም ይህ የስለት ስጦታ ነው!

ከአንዱ ቦታ በአንድ ጊዜ ከሚወስዱት በርካታ ሥጋ በተጨማሪ ከየቦታው እንደዚያው ስለሚወስዱ አንድ ሰው ብቻውን አንድ መደብ ሥጋ ይዞ ወደቤቱ የሚሄድ ይመስላል፡፡ በዚያው ልክ ደግሞ በላስቲክ ቤት የተዋቀሩ ጊዜያዊ ልኳንዳ /ሥጋ/ ቤቶች አንድ ኪሎ ሥጋ አንድ መቶ ብር ለበላተኛ ይሸጣሉ፤ የፈለገው ጥሬውን ያወራርዳል፤ የፈለገው ደግሞ ሥጋ ቤቱ ደጃፍ ላይ በብረት ምጣድ ከሚጠበሰው ይመገባል፡፡

በሌላም በኩል ትልቅ ገበያ ላይ እንደሚሸጥ የጎመን ቅጠል ክምር በረጅም ሰልፍ የተደረደሩት የጫት ቅጠሎች ለሽያጭ ቀርበዋል፡፡ የመቀመጫ ንጣፍ ላስቲክ፣ እጣን፣ እርጥብ ሣር፣ ዳቦ፣ ብስኩት፣ ጀበና፣ ስኒ ወዘተ … የሚሸጡ ብዙ ናቸው፡፡

ያጓጓዘንን አየር መንገድ አርማ የያዙ ባነሮችን በድንኳኖቻችን ላይ ከሰቀልን በኋላ ካሜራዬን በደረቴ ታቅፌ ወደ ቤተክርስቲያኑ ዘለቅኩ፤ ለንግሥ የተጓዘው ምዕመን በቤተክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ አስቀድሞ ማደሪያ ቦታውን ይዧል፡፡ በቤተክርስቲያኑ ውስጥም እንዲሁ ቦታ ቦታቸውን ይዘዋል፡፡ የቻልኩትን ያህል በካሜራዬ ፎቶ ካነሳሁ በኋሉ ተመልሼ ወደ ድንኳናችን አመራሁ፡፡

ቁልቢ አካባቢ የአየሩ ሁኔታ ፀሐያማ ሆኖ ነው የዋለው፡፡ ቀኑ እየመሸ መሄድ በመጀመሩ ፀሐይዋ እየጠፋች ለአይን መያዝ ጀምሯል፡፡

ድንኳኖቻችን ከተተከሉበት ጀርባ ከአንድ ጉብታ ሥፍራ ብቻዬን ተቀምጫለሁ፤ ከቤተክርስቲያኑ የሚተላለፈው የስብከት ትምህርት ስሜትን ይስባል፤ ከዚህ ቀደም ወደ ቁልቢ የተጓዙ ምዕመናን የሠሩትን በጐና ጥሩ ያልሆነ ተግባር እየጠቀሱ የሚያስተምሩት ሰባኪ መምህር አንደበተ ርቱዕ ናቸው፡፡

‹‹ምዕመናን ሆይ ለንግስ ስትመጡ አእምሮአችሁንና ልባችሁን አጥርታችሁ ኑ! ቂም ይዞ ፀሎት አይገባም፤ የምትሳሉትን ስለትም በልኩ አድርጉት፤ የማትችሉትን ቃል አትግቡ፤ ‹ቁጭ ብለው የሰቀሉትን ቆሞ ለማውረድ ይቸግራል፤› የዛሬ ሁለት ዓመት አንዲት ሴት ከነበረባት ጭንቀት ለመገላገል ስትል ‹አይጥ ይዤ እመጣለሁ፤ ብቻ ሀሳቤን ሙላልኝ› ስትል ተሳለች፡፡ ሀሳቧ ሞላላት፤ ይዛ የመጣችው ግን ሰንጋ በሬ ነበር፤ እዚህ ስትደርስ ግን ችግር ገጠማት፤ ቃል የገባችውን አልፈፀመችምና!›› እያሉ ያስተምራሉ፡፡

ሙሉ ሀሳቤን በመምህሩ ትምህርት ላይ አድርጌ አካባቢዬን እየቃኘሁ ነው። ከተቀመጥኩበት አሥር ሜትር ርቀት ላይ መደዳውን ሁለት ድንኳኖች ተተክለዋል፡፡ በመጀመሪያው ድንኳን ውስጥ መሬት ላይ በተዘረጋው ፍራሽ አንድ ጐልማሳ ጋደም ብሎ ፊትለፊቱ በላስቲክ ተጠቅልሎ ከተቀመጠው የጫት እንጨት ቅጠሉን እየቀነጣጠሰ ወደ አፉ ይከታል፡፡ እዚያው ድንኳን በር ላይ አንዲት ሴት ከእርሱ ጋር እያወራች በብረት የሻይ ማፍያ ከሰል ማንደጃ ላይ ያስቀመጠችውን እያርገበገበች ለማፍላት ጥረት ታደርጋለች፡፡ ከሰውየው አጠገብ አንዲት ሴትና አንድ ወንድ ልጅ ተቀምጠው ይጫወታሉ። ይህ ቤተሰብ እንግዲህ ለንግሥ የመጣ ነው፡፡

በሁለተኛው ድንኳን በከሰል ማንደጃ ብረት ድስት ጥዳ የምታማስል ሴት ትታየኛለች፤ አንድ ወንድ ከድንኳኑ ውጭ በትንሽ መቀመጫ ላይ ተቀምጧል፡፡ ከድንኳኑ ፊት ለፊት አንድ መኪና ቆሟል፤ አንድ ወጣት ከድንኳኑ ውስጥ ጀሪካን አውጥቶ የመኪናውን አካል ማጠብ ጀመረ፤ ከጀሪካኑ ውስጥ የሚቀዳው ግን ጠላ ነበር፡፡ ይህንን ትዕይንት እያስተዋልኩ የቀኑ መጨለም እይታዬን ገደበው፤ ከተቀመጥኩበት ተነስቼ አብረውኝ ወደነበሩት ጓዶቼ ለመቀላቀል ሄድኩ፡፡

አርብ ሐምሌ 19 ቀን 2005 ዛሬ የንግሥ ቀን ነው፤ የቤተክርስቲያኑ ዙሪያ በሰዎች ተጨናንቋል፤ ወደ ውስጥ መግባትም ወደ ውጭ መውጣትም ጭንቅ ነው፡፡ እስከ ቀኑ አምስት ሰዓት ድረስ ያለው ጊዜ ወደየትኛውም ስፍራ ለመንቀሳቀስ አያስችልም፡፡ ይሁን እንጂ ከቤተክርስቲያኑ ባሻገር ባለው ግዙፍ ተራራ ላይ ካሜራዬን አንግቼ ወጣሁ፡፡ ከዚያ ላይ ሆኜ ሙሉ ቤተክርስቲያኑንና አካባቢውን በካሜራዬ ፎቶ ለማንሳት ቻልኩና ወደ ማረፊያችን ተመለስኩ፡፡

ከቀኑ ስምንት ሰዓት ከሠላሳ ሲሆን ከፊት ለፊታችን የተደረደሩት መኪኖች ቦታ ሲለቁልን ተራችንን ጠብቀን ከአካባቢው ወደ ድሬዳዋ መንገዳችንን ጀመርን፤ በመጣንበት አካኋን ድሬዳዋ ራስ ሆቴል ተሰባስበናል፡፡ የምሳ ቆይታ በራስ ሆቴል አድርገን ስናበቃ 11፡15 ሁላችንም በድሬዳዋ አውሮፕላን ማረፊያ ፍተሻ ስፍራ ላይ ዕቃዎቻችንን እያስፈተሽን አለፍን፡፡

ከአዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ለጉዞ ስነሳ ካሜራው የኩባንያችን መሆኑን በመግለጽ ስመለስ ችግር እንዳይገጥመኝ አስቀድሜ የይለፍ ወረቀት አውጥቼለት ስለነበር ስለያዝኩት ካሜራ ስጋት አልገባኝም፡፡ የያዝኩትን ሻንጣ ከፍቼ ካሳየሁ በኋላ ወደ አውሮፕላኑ ገባሁ፡፡

አውሮፕላኑ የማኮብኮቢያ ሜዳውን ጨርሶ አፍንጫውን ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ወድሮ አየሩን እየሰነጠቀ ይምዘገዘጋል፡፡ ተጓዦች እንዲያ እንዳልፈነጠዙ በፍርሀት ዝም ብለዋል፡፡ ዛሬም እንደ አመጣጣችን በአንድነት ፀሎት አድርገናል፡፡

ከበረራ ክፍሉ ድምፅ መሠማት ጀምሯል፡፡ ‹‹በዓሉን አክብረን ስለመጣን እንኳን ደስ አላችሁ፤ የአዲስ አበባ የአየር ሁኔታ ከፊል ደመናማ ነው፤ የሙቀት መጠኑ 15 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ያለንበት ከፍታ 22 ሺህ ጫማ ነው፤ ከዚህ በኋላ ለ27 ደቂቃ ብቻ በረራ እናደርጋለን በሰላም ያግባን›› ንግግሩ ተጠናቀቀ፡፡

አንዳንድ ተጓዦች ዛሬም በአውሮፕላኑ መስኮት ለመመልከት አልደፈሩም፤ በዚህ የመልስ ጉዞ ፓይለቶቻችንን አስፈቅጄ ቪዲዮ እንድቀርፃቸው ወሰንኩ ስለዚህም አብሮን ለተጓዘው የአውሮፕላኑ ሠራተኛ ነገርኩት፤ ወደ አብራሪዎቹ ክፍል ተጠግቶ ሲነግራቸው ተቃውሞ አልነበራቸውም ሰላምታ አቅርቤላቸው ትንሽ ካነጋገርኳቸው በኋላ በቪዲዮ ቀረጽኳቸው። የቴክኖሎጂን መራቀቅና የሠሪዎቹን ጥበብ እያደነቅኩ አብሬያቸው ትንሽ ቆየሁ፡፡ በአውሮፕላኑ ረቂቅ መሣሪያዎች ከመመራት ውጪ በዚያ ወቅት ፊትለፊታቸው እያዩ የሚጓዙበት የዕይታ አድማስ አልነበራቸውም፡፡ ዙሪያቸው በዳመና የተሞላ ነበር፡፡

ከምሽቱ 12፡55 ይላል፤ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በሠላም ደርሰናል፡፡ በጉዞአችን እንከን ሳይገጥመን አድርሰው የመለሱን የአውሮፕላኑ ሠራተኞች የመጀመሪያውን የተሳካ የሀገር ውስጥ በረራ ያደረጉ ሲሆን፤ ወደ ድሬዳዋ ስንጓዝና ስንመለስ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ሽኝትና አቀባበል ያደረጉልን የትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ ኃ.የተ.የግ.ማ. ዋና ሥራ አስኪያጅ ካፒቴን ተረፈ ኃይሌ ለሚያረካው መስተንግዶአቸው ምስጋና ሊቸራቸው ይገባል፡፡

ቲ.ኤን.ኤ. ድንቅ አገልግሎቱን መስጠት ጀምሯል፤ ኩባንያው በአውሮፕላንና በሄሊኮፕተር ብቃትና ልምድ ባላቸው አብራሪዎቹና ሠራተኞቹ የተሟላ የበረራ አገልግሎት መስጠት መቻሉን ለመመስከር ችለናል፡፡ ከእንግዲህ በኢትዮጵያ ያሉ የቱሪስት መዳረሻዎችን እንደልብ ለመጐበኘት ‹‹በየትኛው አውሮፕላን ልጓዝ?›› ብሎ መጠየቅና መወሰን የእያንዳንዱ ፍላጐት ይሆናል፡፡ እኛ ግን በእንክብካቤ ደህንነታችን ተጠብቆ ያሰብነው ቦታ ደርሰን ተመልሰናል፡፡ መልካም ላደረጉልን ኃላፊዎቻችን መልካሙን ሁሉ እንመኛለን፡፡

በግል አውሮፕላናችን ወደ ምሥራቁ ...

የድንኳን ውስጥ ዕረፍት እንዲህ ይመስል ነበር

Page 13: 72 - MIDROCmidroc-ceo.com/sites/default/files/Newsletters/R_Issue72.pdfAddis Ababa, Ethiopia 1 ከሊቀመንበሩ ማኅደር Volume 14, Issue No. 72 July — August 2013 u¨

13

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 72 July — August 2013

Addis Ababa, Ethiopia

ጫትና የወጣቱ ትውልድ ጥምረትበወርሀ ታህሣሥ ሰኞ ዕለት የጉዞዬን አቅጣጫ ወደ ሣሪስ አደረግኩኝ። ማለዳ 12፡00 ሰዓት የጀመረው ጉዞዬ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ሲል ሣሪስ አበቃ፡፡ የቀኑ ቅኝት ደግሞ የጫትን ገመና ገላልጦ ማወቅ፡፡

እነሆ ይህ ርዕሠ ጉዳይ ለዘመናት ሳስብና ስብሰለሰልበት የነበረ ነው። በተለይ ከጫት ጋር የተቆራኙት የሕብረተሰብ ክፍሎች ተጠቀሙ ወይስ ተጐዱ የሚለውን ባለኝ አቅም ለሌሎች ለማሳወቅ ካለኝ ከፍተኛ ፍላጐት የመነጨ ነው።

በመሀል ሣሪስ ዋና መንገድ ያለው የጫት ማከፋፈያ መጋዘን በበርካታ ሰዎች ተጨናንቋል፤ ከሰው ብዛት የተነሳ በአካባቢው አንድ ነውጥ የተፈጠረ ይመስላል፡፡ የውጭ በሩ ሳይቀር እንደዚያው በሰዎች ብዛት ተጨናንቋል፡፡ በወፊቾ የተጠቀለለ ጫት በሁለት እጃቸው፣ በአንገታቸው ዙሪያና በራሳቸው እንዲሁም በጀርባቸው የተሸከሙ ሴቶችም ወንዶችም ጫት ነጋዴዎች ወደ ውጭ ለመውጣትና ወደ ግቢው ለመግባት በሩ ላይ ትንቅንቅ ይዘዋል፡፡

እንደ ምንም ተጋፍቼ ወደ መጋዘኑ በር ዘለቅኩኝ፤ መጋዘኑ በጫት ተሞልቷል፡፡ ቀኑን ሙሉ ከየአቅጣጫው በአይሱዙ እየተጫነ የሚመጣው ጫት ወደዚህ መጋዘን ይታጨቃል፡፡ በጠዋቱ ለነጋዴዎቹ ይከፋፈላል፡፡ ይህ የዘወትር ተግባር ነው፡፡ ጫቱን በቀጥታ ከመጋዘኑ የሚገዙ ነጋዴዎች፣ እዚያው ገዝተው አትርፈው ለሌሎች ነጋዴዎች የሚሸጡ፤ ከእነዚህ ነጋዴዎች ደግሞ ገዝተው በትንሽ ትርፍ በችርቻሮ የሚሸጡ ቸርቻሪ ነጋዴዎች በጫቱ ላይ ሲረባረቡ ማየት በዚህ ዕፅ ላይ አንዳች ጠቃሚ ነገር አለበት እንጂ ጐጂ ነው ብሎ ማን ያስባል?

በግቢው ያለኝን ቆይታ ጨርሼ ወደ ውጭ ለመውጣት ሞከርኩ፤ ትንቅንቁ ያው ነው፡፡ በዚያ አካባቢ ያለው የጫት ሽያጭ ነጋዴዎቹን ብቻ ሳይሆን እያንገላታ ያለው በዚያ መስመር ያሉ ማንኛውንም የህብረተሰብ ክፍል ለመሆኑ በግልፅ ይታያል፡፡

ጠዋት ወደ ሥራ ወይም ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ መንገዱ ላይ ችምችም ብለው ቆመው መጓጓዣ የሚጠብቁ ሰዎች በጫት ነጋዴዎቹ ምክንያት ከሥራቸውና ከትምህርት ገበታቸው ይስተጓጐላሉ፡፡ ምክንያቱም ታክሲዎቹ ለጫት ነጋዴዎቹ ቅድሚያ በመስጠታቸው አንድ ነጋዴ ጫቱን በሞላ በታክሲው ጠቅጥቆ ብቻውን ሲከንፍ ማየት የተለመደ ነው፡፡ አልያም በሰዎች ላይ ጫቱ ተደርቦ በችግር የሚጓጓዙበት ሁኔታ የሁልጊዜ ተግባር ነው፡፡

በጫት ነጋዴዎቹ ምክንያት በሚፈጠረው የትራንስፖርት እጥረት የሚቸገረው ተገልጋይ በእግሩ ረጅም ጉዞ ለመጓዝ ተገድዷል፡፡ የጫት ንግዱ እያስከተለ ያለውን ችግር ተመልክቶ መፍትሔ ለመስጠት የተሞከረበት አንድም ጊዜ እንደሌለ ችግር እየደረሰባቸው ያሉ የሕብረተሰብ ክፍሎች በግልጽ ይናገራሉ፡፡

የአካባቢውን ቅኝቴን ጨረስኩና ወደ ዘንባባ ሆስፒታል ወደሚወስደው መንገድ ትንሽ ተራመድኩኝ፡፡ ሰዓቱ ከጠዋቱ 3፡00 ይላል በአካባቢው ባሉ ካፊቴሪያዎች በረንዳ ላይ ጫቱን በላስቲክ ሸፍኖ ጠረጴዛ ላይ ተደግፎ እየቀነጣጠሰ ወደ አፉ እየከተተ ያለውን ወጣት ስመለከት ቁርሱን አስቀርቦ የሚመገብ መሰለኝ! እርሱ ብቻ መቼ ሆነ! በየጥጋጥጉ በጠዋቱ የጫት መቃሙን ተግባር ሲፈጽሙ ማየት የሚያስደንቀው ለእኔ እንጂ ለካስ የተለመደ ነው፡፡

የተቀጠሩአብነት ደመቀ በአሲስታንት ኮንስትራክሽን ማሽን ኦፕሬተር፣ ዳግም ስብሐት በሲቪል ኢንጂነር፣ አዝመራው አይቼው በቬኼክል ኦፕሬተር የሥራ መደብ በሁዳ ሪል እስቴት፡፡ ብዙአየሁ ይመን በሴክረተሪ፣ ቀናው አበራ በአቴንዳንት /ፓኪንግ/ ፣ አይሻ መሐመድ፣ ትዕግሥት ገዛኸኝ፣ መንበረ ሙሉጌታ፣ ወጋየሁ ተፈራ፣ አስካለ አሸናፊ እና እቴቱ ደሳለኝ በአቴንዳንት /ስቶር/፣ የሥራ መደብ በኩዊንስ ሱፐር ማርኬት፤ ጋዲሣ ጋሩማ በከባድ መኪና ኦፕሬተር የሥራ መደብ በኤምቢአይ፤

አሚር የሱፍ በሲኒየር ፕላነር፣ ፍቅርተ ተፈራ በኤግዚኪዩቲቭ ሴክሬተሪ በዋንዛ፤ ሲሳይ ተፈራ በጄነራል ሰርቪስ ክለርክ፣ እድገት ንጉሴ እና ቢዞ ጣፋ በአቴንዳንት፣ ስዩም ነጋ እና ፍሬው አለማየሁ በመልቲ ስኪልድ ኦፕሬተር፣ አሰለፈች ዲላ በጁኒየር ላቦራቶሪ ቴክኒሽያን፣ አስቴር ጉተማ፣ ቀለሟ ኤዳ፣ ይልፋሸዋ አወቀ፣ ዘቢደሩ ፍስሀ እና ቅድስት ለማ በስቶር ኪፐር፣ ብዙወርቅ መርጊያ እና ትዝታ ጴጥሮስ በዳታ ክለርክ፣ ፍቅርተ አያሌው በካሸር፣ ስንታየሁ አለሙ በፊዩል አቴንዳንት፣ ጌቱ ፈጠነ በፎርክሊፍት ኦፕሬተር፣ ዳንኤል ተካልኝ ቱልስ ኪፐር፣ ሰለሞን ሀይሉ በላይት ቬኼክል ኦፕሬተር፣ እርቅይሁን ገብሬ በዳይኒንግ ሆል ሊደር፣ እታፈራሁ አበበ ተሰማ በቴብል አቴንዳንት፣ አብዮት ዘርፉ በላይት ቬኼክል ኦፕሬተር፣ አልማዝ በቀለ እና ጽዮን ደጀኑ በኦፊስ አቴንዳንት፣ ተክሉ ቱሉ፣ ጌትዬ ሐምዛ እና አድነው ሙጨ በስቶር አቴንዳንት በሚድሮክ ወርቅ ተቀጥረዋል፡፡

ሀና መላክ በሲኒየር ኦዲተር፣ ማርታ አጥላው በጁኒየር ኦዲተር፣ ሳምሶን ተረፈ በኢንጂነር፣ ዳንኤል ጌታሁን በጁኒየር ኢንጂነር፣ ዮናታን ተስፋዬ በፕሮጀክት ኦፊሰር፣ ፀዳለማርያም በለጠ በኦፊስ ፋሲሊቲ ሜይቴናንስ ዋን የሥራ መደብ በሚድሮክ ሲኢኦ ተቀጥረዋል፡፡

አዳሙ ገብሬ እና መንበረ የሱፍ በአቴንዳንት ፋርም፣ አረጋ ስመኝ በጁኒየር አግሪካልቸራል ኢኮኖሚስት በኤልፎራ፤ ቢላል ሱልጣን በምርት ክፍል

ማናጀርነት በዴይላይት ተቀጥረዋል፡፡

የለቀቁአቶ የወንድወሰን በቀለ ከአዲስ ጋዝና ፕላስቲክ፤ ሀሰን መሐመድ፣ መሰረት ጥላሁን፣ ኤርሚያስ አድማሱ፣ ሂሩት አሰፋ፣ ሳራ ተስፋዬ እና ዲቻ ቀነኒ ከሚድሮክ ወርቅ፤ ረጋሳ ገበየሁ ከኤልፎራ፤ ሽታዬ ማሞ ከዋንዛ፤ ቸሬ ታደሰ ከዴይላይት፤ ተክሉ አቦምሳ ከሲኢኦ በራሳቸው ፈቃድ ለቀዋል፡፡

የተዛወሩብሌን አመንሸዋ እና ራሄል ደስታ ከኩዊንስ ወደ ሁዳ፣ አይናለም መንገሻ ከሁዳ ወደ ሲኢኦ፣ ኢዮብ ወልዴ ከኩዊንስ ወደ ሴፕኮ፤ ሂሩት አሸቱ ከሴፕኮ ወደ ዋንዛ፤ አስካበች ግዛቸው እና ርብቃ ገብሩ ከሲኢኦ ወደ ሁዳ፣ ትዕግሥት ግዛቸው ከሲኢኦ ወደ ኮስፒ፣ አዝመራ ካሣሁን ከሲኢኦ ወደ አዲስ ሆም ዴፖ፣ የሻነው መንግሥቱ ከሲኢኦ ወደ ትረስት ተዛውረዋል፡፡

የተሰናበቱወ/ት ሰአዳ ኑር አህመድ ከዋንዛ ኩባንያ ተሰናብተዋል፡፡

በሞት የተለዩ አቶ አዳነ ኤዳ ከሚድሮክ ወርቅ በሞት ተለይተዋል፡፡ ለሥራ ባልደረቦቻችን ቤተሰቦች እግዚአብሔር መጽናናትን እንዲሰጣቸው እየተመኘን የሐዘናቸው ተካፋይ መሆናችንን እንገልጻለን፡፡

ጡረታ የወጡአቶ ገ/ኪዳን ኪ/ማሪያም፣ አቶ ሰለሞን ማሞ፣ አቶ አብርሃም ዳምጠው፣ አቶ ደሳለኝ ኃ/መስቀል፣ አቶ ይትባረክ ይግዛው፣ አቶ ዘሪሁን መንግሥቱ ከአዲስ ጋዝና ፕላስቲክ፤ አቶ መንክር ይገብሩ፣ አቶ በላይ ይመኑ፣ አቶ ጌታቸው ተ/ማሪያም እና አቶ ፀጋዬ ወ/አረጋይ ከሚድሮክ ወርቅ፤ አበበ አካሉ እና አላዬ አሊ ከኤልፎራ፤ አቶ አበራ ደያሳ፣ አቶ ተክሌ ጉልቴ፣ አቶ በላይ ጌታነህ እና አቶ ጥላሁን መኩሪያ ከዋንዛ በጡረታ ተገልለዋል። ለሥራ ባልደረቦቻችን ቀሪው ዕድሜያችሁ መልካም የዕረፍት ጊዜ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡

ከሠራተኞች ማኅደርየሠራተኞች ቅጥር፣ ዝውውር፣ የለቀቁ፣ በጡረታ የተሰናበቱ፣ ጋብቻ የፈፀሙና ዜና ዕረፍት

ወደ ገጽ 14 ዞሯል

ጠቅላላ ዕውቀት

Page 14: 72 - MIDROCmidroc-ceo.com/sites/default/files/Newsletters/R_Issue72.pdfAddis Ababa, Ethiopia 1 ከሊቀመንበሩ ማኅደር Volume 14, Issue No. 72 July — August 2013 u¨

14

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 72 July — August 2013

Addis Ababa, Ethiopia

በሣሪስ አካባቢ በርካታ የጫት ማስቃሚያ ቤቶች እንዳሉ በግልጽ ይታያል። መኖሪያ ቤታቸውን ሣይቀር ለዚሁ ተግባር ያዋሉ ቤተሰቦች ያሉበት ቦታ ነው፤ ሣሪስ፡፡ ቤታቸውን አነስተኛ ንግድ ነገር ጀምረውበት ወደ ውስጥ ያለውን ጓዳ መሣይ ቦታ በመጋረጃ ጋርደው፤ ወለሉ ላይ ምንጣፍ አንጥፈው ጫት ቃሚዎችን የሚጠብቁ አገልጋይ ሴቶች በጠዋቱ ተጣጥበውና ውበታቸውን ጠብቀው በየበሩ ላይ ቆመው ይታያሉ፡፡ ግማሾቹ ቀድመው የገቡ ቃሚ ደምበኞች ስላሉዋቸው ከሰል እያቀጣጠሉ ቡና ለማፍላት ይጣደፋሉ፡፡ ጫቱን በእጁ የያዘ፣ ጫቱን የሚቅመው፣ ጫቱን ለመግዛት የሚርመሰመሰው ሕዝብ ብዛት ሲታይ ይህ ሁሉ ህዝብ ምን እየሆነና ወደየት እያመራ ነው የሚል እሳቤን ይፈጥራል፡፡

ይህቺ ምልከታ በሣሪስ አካባቢ ብቻ የተከናወነች ነች፡፡ የቀኑ ውሎዬ እዚያው ሆኗል፤ ረፋዱ ጊዜ እየተጣደፈ ወደ ቀትሩ ሰዓት እየተሸጋገረ ነው፡፡ የጫት መጋዘኑ አካባቢ በሰዎች መጨናነቅ በመጠኑ ቀንሷል፡፡ ሁሉም ድርሻውን ስለወሰደ! ቸርቻሪ ነጋዴዎች ከሣሪስ የጫኑትን ጫት ወደ መሀል ከተማ በታክሲ እያጓጓዙ ከሄዱ ቆይተዋል፡፡ የሄደው ጫት ሳይበላ እንደማይቀር ገምተን ወደ ሌላው ምልከታ እንሸጋገር፡፡

የቀኑ ቀትር መሆን ትርምሱን ፀጥ አድርጐ በየካፊቴሪያው በራፍ፣ በየአትክልት መሸጫ ቦታ፣ በየጥጋጥጉ፣ በየመቃሚያ ቤቶች ጫት ቃሚዎችን ምሽግ አስይዟቸዋል፡፡ በዚያው የቆየሁት የጫት ቃሚዎችን ድርጊት ለማየት ነውና ወደ አንዱ የጫት ማስቃሚያ ቤት ድንገት ገባሁ። ዙሪያውን ቤቱን የሞሉት ወጣቶች ናቸው፡፡ በአንድ ጥግ ቡና የምታፈላው ወጣት ቁጭ ብላ ከሰሉ ላይ የተጣደውን ቡና እንዲፈላ ከሰሉን ታርገበግባለች፤ ከወጣቶቹ ፊት ለፊት የተቀመጠ ጀበና መሳይ የሺሻ ማጨሻ እቃ ይታያል፡፡ ረጅም ገመድ መሳይ ቱቦ በላዩ ላይ ተገጥሞለታል፡፡ ጠፍጣፋ ነገር ፈረካከሰችና በሺሻው አናት ላይ ከእሳት ጋር አኖረችበት። ወጣቶቹ እየተቀባበሉ ጭሱን ይምጋሉ፤ ሺሻው ይንደቀደቃል፤ እነርሱም በአፍና በአፍንጫቸው ጭሱን ያስተነፍሳሉ፡፡ ሁሉም በአግራሞት ተመለከቱኝ አንድ ተንኮል እንደያዝኩ ገብቷቸዋል፡፡ ምን እንደምሰራ፤ ምን እንደፈለኩኝ ደግሞ ለመጠየቅ አስፈርቷቸዋል። ቡና አፍይዋ ሴት ‹‹አባ ተቀላቀላ!›› አለችኝ። ‹‹ጫት ገዝቼ እመለሳለሁ›› አልኩዋት፡፡ ‹‹እዚሁ አለ!›› መለሰችልኝ። ‹‹የራሴን ይዤ እመጣለሁ›› ብዬ ውልቅ አልኩኝ፡፡ ተከትላ አየችኝ፡፡ ከዚያ አካባቢ እስከምርቅ ድረስ በአይኗ እያባረረችኝ ከአሁን አሁን ምን ይዞ ይመጣብን ይሆን ብላ እንደምታስብ እገምታለሁ፡፡ የእኔ ተግባር ግን ማየትና መታዘብ ብቻ ነበር፡፡

ትንሽ ከተጓዝኩ በኋላ ወደ አንድ መታጠፊያ ቦታ ገባ ብዬ አካባቢውን ቃኘሁና የተጋረደውን መጋረጃ ገለጥ አድርጌ የሚሆነውን ለማየት ሞከርኩ፤ የቤቱ ብርሃን ደብዛዛ ነው፡፡ በበሩ አጠገብ ካለችው ዱካ መሣይ መቀመጫ ላይ አረፍ ብዬ አይኔን አሻሸሁ፤ እንደገናም ለማየት ሞከርኩኝ፤ የትምህርት ቤት ዩኒፎርም ሹራብ ያጠለቁ ጎረምሶችና ሁለት ሴት ተማሪዎች፤ አንድ ወፍራም እድሜው በግምት ወደ 48 ዓመት የሚጠጋ ጐልማሳ፤ ሌሎች ፀጉራቸው የተንጨበረረ፣ ፊታቸው ዘወትር በጫትና በመጠጥ የነበዘ የሚመስሉ በአጠቃላይ 15 ያህል ሰዎች በተጨናነቀ ሁኔታ ተጠጋግተው የቤቱን ዙሪያ ጠርዝ ይዘው ሁለት እግሮቻቸውን ዘርግተው ተቀምጠው ይታያሉ፡፡ አቀማመጣቸው በጠላት እጅ ተይዘው ለመረሸን የተዘጋጁ ፍርደኞች መስለው ታዩኝ፡፡ እዚህም ‹‹እኛን ምሰል›› የሚል ጥያቄ በጥርጣሬ ቀረበልኝ፡፡ ‹‹በቂ ቦታ የላችሁም!›› አልኩኝ፡፡

‹‹ኧረ ይኸው ደግሞ ለቦታ!›› ሁሉም የግብዣ አይነት ቃላት አዘነቡ፡፡ ‹‹እንግዲያው መስተንግዶአችሁ እጅግ ማራኪ ነው፤ ስለዚህ ለሁለት ሰው ቦታ ይዘጋጅ ጓደኛዬን ይዤው ልምጣ›› ብዬ ከቤቱ ተፈትልኬ ወጣሁ። ያንን ቤት መለስ ብዬ እንኳን አላስተዋልኩትም፡፡ የሣሪስ እይታዬን በመንገዱ ላይ ብቻ አድርጌ ትራንስፖርት ለመያዝ ከአስፋልቱ ዳር ቆምኩኝ፡፡

የጠዋቱ ግርግር አሁን ቀንሷል፡፡ ሁሉም ጫቱን ታቅፎ በየራሱ ዓለም

ነጉዷል፡፡ ጠዋት ለሠራተኛው፣ ለተማሪውና ለባለጉዳዩ ግድ ሳይኖራቸው አገልግሎታቸውን ለጫት ነጋዴ የሰጡት ታክሲዎች የሰው ያለህ እያሉ ይጣራሉ፡፡

ቀጥታ ታክሲ የመያዝ ሀሳቤን ቀየርኩና በአደይ አበባ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ፊት ለፊት ወደ ሣሪስ አዲሱ ሰፈር በሚወስደው መንገድ አመራሁና ቀለበት መንገዱ ላይ ወደ ቦሌ የሚወስደውን ሎንቺን ተሳፈርኩኝ፡፡

ይህንን ቦታ እንደ ሣሪሱ ብዙ አልቆየሁበትም፡፡ የጫት ማስቃሚያ ቤቶቹ እጅግ የተዋቡና ዘመናዊነታቸውን የጠበቁ ናቸው፡፡ የተከበረ በሚመስለው ግቢ የሚያውቁት ቃሚዎች ሰተት ብለው እየገቡ ጫማቸውን እንደ ቤተክርስቲያን እያወለቁ በተነጠፈው ምንጣፍ ወይም አረቢያን መጅሊስ ደገፍ ብለው ይቀመጣሉ፡፡ መስተንግዶው ሁሉ እዚያው ድረስ ይመጣል፤ ጫት ገዝቶ መሄድ አይጠበቅም፡፡ ዳጐስ ያለ ብር መያዝ ብቻ በቂ ነው፡፡ የሚያቃቅም ሴት ከተፈለገም እንደ በግ ገዢ አማርጦ ከአንዷ ጋር መሆን ይቻላል፡፡

በዚህ ቦታ ይህንን ለመታዘብ ያስቻለኝ የኮምፒውተር ባለሙያ የሆነ የማውቀው ሰው በማግኘቴ ከእርሱ ጋር ትንሽ ቆይታ ባደረግኩበት ጊዜ ያስተዋልኩ በመሆኑ ነው፡፡ እዚህም እንደዚያው ጫቱ በጋራ ይቀርባል፤ በጋራ ይቃማል፤ ሺሻው ይጨሳል፤ ሺሻው ላይ የሚቀመጠው የሚጨስ ነገር እንደየፍላጐት የሚስተናገድ ነው፡፡ ሂሳቡም ለእያንዳንዱ እንደየድርሻው ተሰልቶ ይከፈላል፡፡ ከጫት መቃም በኋላ የመጠጥ ይሁን ሌላም ሱስ

እንደየፍላጐት ይስተናገዳል፡፡ በዚህ አካባቢ ያለኝን የሁለት ሰዓት ቆይታ አጠናቅቄ ጉዞዬን ወደ ቤቴ አደረግኩኝ፡፡ በሁሉም ቦታ ይህ ተግባር የቀን ተቀን ሥራ መሆኑን መታዘብ ለማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ በመላ ሀገሪቱ ይህ እንደሚፈፀም ማን ሳያውቅ ይቀራል?

በእኛ አገር ጫትን ከወጣቶች እስከ አዛውንቶች ድረስ ሲያኝኩት እንደሚውሉ ይታወቃል፡፡ ከዚያ ባሻገርም ጫት በተከለከሉ በዩኒቨርሲቲና በሥራ ቦታዎች ሳይቀር በድብቅ መሆኑ ቀርቶ በግልፅ ይቃማል፡፡

መጥፎ ሱሶችን ታላላቅ ሰዎች ለታናናሾች ያስተላልፋሉ፤ ያለማምዳሉ። ለምሳሌ ወላጆችና

የቅርብ ዘመዶች ጫት ቃሚዎች ከሆኑ ከሚጥሉት የጫት ገራባ /ጠንካራ የጫት ቅጠል/ መቃምን ‹‹ሀ›› ብለው ይጀምራሉ፡፡ ስበውና መጥጠው በእግራቸው የሚረግጡትን የሲጋራ ቁራጭ አንስተው ሲጋራ ማጨስን ይለማመዳሉ፡፡ ቀስ በቀስም የመጥፎ ምግባር ኩረጃውን ይገፉበትና የመጥፎ ልማድ ቁራኛ ሆነው ያርፋሉ፡፡ በእንዲህ አይነቱ አሳዛኝ ክስተት ምክንያት ተበላሽተው የቀሩትን ቤት ይቁጠራቸው፡፡

ብዙዎች በለጋነታቸው የመጥፎ ሱስ ቁራኛ የሆኑት ከታላላቆቻቸው በመማር ነው፡፡ እንደዋዛ የጀመሩት የጫት፣ የሲጋራና የመጠጥ ሱስም ህሊናቸው ውስጥ ነግሶ ባርያው ያደረጋቸው በርካቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች ራሳቸውን በወጉና በሥርዓቱ ለመምራትና ስሜታቸውንም ለመግዛት ይሳናቸዋል፡፡ ሕይወታቸው እየተበላሸና እያስጠላ ይመጣል። አንደበታቸውን እንኳ መግራት የማይችሉ በርካቶች ናቸው፡፡

እነዚህ ሱሰኞች ሲናገሩ ቃላት የማይመርጡ፤ ከመናገራቸው በፊት ማሰብ ይቅርና ከተናገሩም በኋላ በመጥፎ ንግግራቸው የማይፀፀቱ ከመሆናቸው ባሻገር ለአካባቢያቸው ታዳጊ ወጣቶች መጥፎ አርአያ የሚሆኑ ናቸው፡፡

እነዚህ ሱሰኞች በተለያዩ መሥሪያ ቤቶች የሚሠሩ ቢሆኑ እንኳ የሚሠሩበትን መሥሪያ ቤት ማሰደባቸው አይቀርም፡፡ አንዳንዶችም በኃላፊነት የተረከቡትን ትልቅ ቦታ በሱሳቸው ምክንያት ከማስደፈራቸውም በላይ ለሙስናና ለአድሎአዊ አሠራር ተጋልጠው መገኘታቸው የአደባባይ ታሪክ ነው፡፡

የጫትና የሲጋራ እንዲሁም የመጠጥ ሱሰኛ የሕብረተሰብ ክፍሎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥራቸው እየተበራከተ አስጊ ሁኔታ ላይ መድረሱን መገንዘብ

ጫትና የወጣቱ ትውልድ...

ወደ ገጽ 15 ዞሯል

Page 15: 72 - MIDROCmidroc-ceo.com/sites/default/files/Newsletters/R_Issue72.pdfAddis Ababa, Ethiopia 1 ከሊቀመንበሩ ማኅደር Volume 14, Issue No. 72 July — August 2013 u¨

15

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 72 July — August 2013

Addis Ababa, Ethiopia

ሁሉ ተገቢውን ክህሎትና የዕውቀት ብቃት በቀጣይነት ማሻሻል እንዲችሉ ማድረግ እና የዩኒቨርስቲው የማኔጅመንት አወቃቀርና አመራር (University governance) የትምህርት ጥራት ላይ ያነጣጠረ እንዲሆን ማድረግ ላይ ከፍተኛ ሥራ ለመሥራት ዩኒቨርስቲው ተዘጋጅቷል። ስለሆነም ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ (HERQA)፣ ከግልና ከመንግሥት የትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር በሀገራችን እጅግ በጣም አሳሳቢ ለሆነው የትምህርት ጥራት ጉዳይ ከጐን ሆኖ ከንፈር መምጠጥ ሳይሆን "Quality House" የሚለውን መፈክሩን ተግባራዊ ለማድረግ ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ተግቶ ይሠራል፡፡ ጥራት የሌለው ለብ-ለብ ትምህርት ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ ስለሆነም ከፍተኛና ጠለቅ ያለ ትኩረት እንደሚያስፈልገው እናምናለን፤ አምነንም ውጤት ለማሳየትና ለማረጋገጥ ሥራ ጀምረናል፡፡

ሶስተኛው ዓብይ ትኩረታችን፤ ዩኒቨርስቲው በአንድ የትምህርት ዓይነት በከፍተኛ ደረጃ በሀገራችን እንዲታወቅ የማድረግ ዕቅዳችንን በሥራ ላይ ማዋል ነው፡፡ በሌላ አባባል በሥራ አመራር (Leadership) ትምህርት ዩኒቲ የ"Center of Excellence" ተቋም እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡ ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ በሥራ አመራር (Leadership) ትምህርት በምሳሌነት ሊጠቀስ የሚችል ማዕከል በመሆን ብዙ የሥራ አስኪያጆች (Managers) ሆኖም ግን እጅግ በጣም ቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ በተለያዩ የሥራ መስኮች የተሰማሩ መሪዎች (Leaders) ያሉባት ሀገራችንን ወቅታዊ ይዘት በመለወጥ ብዙ ሥራ መሪዎችና ፈጻሚዎች (CEOs) እንዲኖሩ ከማድረግ አኳያ ዩኒቨርስቲው ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ በመሥራት ገንቢ አስተዋጽኦ (Constructive Contribution) ለማድረግ ዕቅዱን ዘርግቷል፡፡ ለሀገር ዕድገት የሥራ መሪዎችና ፈጻሚዎች ዕውቀትና ክህሎት እጅግ አስፈላጊ መሆኑ ሊሠመርበት ይገባል፡፡

ከላይ የተጠቀሱትን ሶስት ዓብይ ትኩረቶቻችንን ሥራ ላይ ለማዋል፣ ለሀገራችን ዕድገት በተለያዩ የኢንቬስትመንትና የበጐ አድራጐት ሥራ ላይ የተሠማሩት ሊቀመንበራችን (ክቡር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ) በትምህርት ላይ ለሚደረገው ሥራ የሚሰጡት ማበረታቻ፣ ለዕቅዳችን ከፍተኛው ግብዓት በመሆን እንድንተጋ ያደረገን መሆኑን እየገለጽኩ፣ ለዚህ ተግባራቸው ሊቀመንበራችንን በዩኒቨርስቲው ማሕበረሰብ ስም ከልብ ማመስገን እወዳለሁ፡፡

የትምህርትን ጥቅም የሚያውቁ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በትምህርት የተጠቀሙ ሰዎች ናቸው፡፡ ትምህርት እንደማንም የፋብሪካ ውጤት የሚሸጥ፣ የሚለወጥና የሚሸመት አይደለም፡፡ ትምህርት የአንድ ግለሰብ ሕይወትን ለዓመታት የሚያገለግል፣ ጊዜ የማይለውጠውና ጥሎ የማይጠፋ ልዩ የስብዕና መገለጫ አጋርና ኃብት ነው፡፡ ትምህርት ከግለሰብ አልፎ የማሕበረሰብና የሀገር ልዩ ኃብት ነው፡፡ ለዚህም ነው ትምህርት የሕዝብ ኃብት (Public good) የሚባለው፡፡ በመሆኑም ዩኒቲ ዩኒቨርስቲና ሌሎችም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ በመማር ማስተማር ሂደቱ ብቁ ኢትዮጵያውያን፣ ዕውቀትና የሥራ ጥበብ ይዘው እንዲመረቁና ሀገር እንዲያገለግሉ የማድረግ ከፍተኛ ኃላፊነት ያለባቸው፡፡ ይህን ከፍተኛ ኃላፊነትና ተግባር ለመወጣት ትርፍ ላይ ከፍተኛ ትኩረት በማድረግ ጥራት የሌለው ትምህርት እንዳይሰጥ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ዩኒቲን ጨምሮ፣ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡

ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ በዚህ ዓመት ያቀረባቸው የዛሬዎቹ ተመራቂዎች በዩኒቨርስቲው የሚጠበቅባችሁን ግዴታዎችን በሚገባ አሟልታችሁ ለምረቃ በመብቃታቸው በዩኒቨርስቲው ሊቀመንበር፣ በዩኒቨርስቲው ሕብረተሰብና በራሴ ስም እንኳን ደስ አላችሁ ስል ለውጤታማነታቸሁ ምክንያት የሆኑትን አጋሮች ሁሉ ላደረጉት መልካም ተግባር በእናንተ በተመራቂዎች ስም ከፍተኛ ምስጋና በማቅረብ ነው፡፡

በቀጣይም የዛሬዎቹ ተመራቂዎች የወደፊት የዩኒቨርስቲው የአልሙናይ (Alumni) አባለት እንደመሆናችሁ ሁሉ፣ ከላይ ለግንዛቤ እንዲያመች የተጠቀሱትን ዓብይ የዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ትኩረቶችን፣ ለራሳችሁና ለሌሎችም እንዲገነዘቡት በማድረግ የወደፊት ቀጣይ ትምህርታችሁንና የዩኒቲ አምባሳደርነታችሁን በማጠናከር፣ ከዩኒቨርስቲያችሁ ጋር ለጋራ ጥቅምና ለሀገር ዕድገት እንድትጥሩ ከወዲሁ አስገነዝባለሁ፡፡

የሚቻለው በየመንደሩ ያሉ የጫት መቃሚያ ቤቶችን ብዛት በመመልከት ነው፡፡ በዚህ የጫት ሱስ መጠመድና ሱሱን ለማስተናገድ በመቃሚያ ቤት መገኘት ለአደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚነት በሠፊው እንደሚያጋልጥ ማየት ይቻላል፡፡ ሀሺሽ፣ ማሪዋናና ሌሎችም አደንዛዥ ዕፆች በስፋት ይስተናገዳሉ። እነዚህን ዕፆች መውሰድ የጀመረ ሰው ደግሞ ህይወቱ እስከመጨረሻው እንደሚበላሽ ብዙዎች ማሳያ ሆነዋል፡፡ በዚህ ሱስ ተጠምዶ መልካም የሆነ ሰው የለምና፡፡ ይህ ሱስ በመላ ሀገሪቱ ተስፋፍቷል፡፡ በዩኒቨርሲቲዎችና በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ሳይቀር ሰርጐ ገብቷል፡፡ ጫትና አደንዛዥ ዕፅ ሀገራዊ ችግር የመሆኑ ሁኔታ በብዙዎች ዘንድ ተዘንግቷል፡፡ ግን ለምን?

በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ሁኔታ የተንሰራፋው የጫት ንግድና የቃሚዎች ቁጥር ማደግ የቻለው ጫቱ በገፍ እየተመረተ ለገበያ በመቅረቡ ምክንያት ነው፡፡ በሀገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች በገፍ እየቀረበ በገፍ ይቃማል፡፡ የጫት ንግዱ ለሀገሪቱ የሚያስገባውን የውጭ ምንዛሪና የቃሚውን ሕብረተሰብ ህሊና ማደንዘዝ አስቀምጠን ብንመዝነው የጫት ሱሱ የሚያስከትለው ጉዳት ሚዛን ደፍቶ ይገኛል፡፡ ይህ የሕብረተሰብ ክፍል የነገ ሀገር ገንቢና የልማት ሥራ ከዋኝ፣ ለኢኮኖሚው አንቀሳቃሽ ኃይል በመሆኑ ዛሬ በጫት ሱስ የመጠመዱ ተግባር የነገውን ራዕይ ያመክናል፡፡ በተለይ ወጣቱን ትውልድ ወኔ አልባና የሀሳብ ወይም የህልም ዓለም ዜጋ እንደሚያደርግ መጠራጠር አያሻም፡፡

አገራችን የምርጥ ስፖርተኞች መፍለቂያ በመሆኗ በተደጋጋሚ ለረጅም ዓመታት በስፖርቱ መስክ ባንዲራዋ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብና የብዙ ወርቅ ሜዳሊያዎች ባለቤት እንድትሆን አስችሏታል፡፡ ይሁን እንጂ በአፍላ ጉልበት ላይ የሚገኘው ወጣቱ ትውልድ ሀይ ባይ በማጣቱ የምንናፍቀው ድል እየራቀ እንደሚሄድ ከወዲሁ አመላካች ሁኔታዎች ይታያሉ፡፡ ሮጠው የማይገቱ ጉልበቶች በጫት ሱስ ከተጠመዱ ቀድሞ የነበረው ጥሩው ታሪካችን ምን ደረጃ ላይ ሊቀመጥ እንደሚችል መገንዘብ አያዳግትም። ለስፖርታዊ እንቅስቃሴያችን መቀጨጭም አንዱ መንስኤ የወጣቶች በተለያዩ ሱሶች የመጠመዳቸው ችግር ነው።

በተለይም ይህ ሱስ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በሥራ ቦታ እየተዘወተረ መምጣቱ ሀገሪቱን በሥራ የላቀ እድገቷን ያረጋግጣል ተብሎ ተስፋ የተጣለበትን ሠራተኛ ዜጋና የነገውን አገር ተረካቢ ትውልድ እድገት ማቀጨጭ በመሆኑ በእሳት የመጫወት ያህል ተደርጐ ሊወሰድ ይገባል፡፡

ሱሱ የሥራ ባህልን በማጥፋት ሀገር ተረካቢውን ዜጋ መንታላና ተስፋ የቆረጠ ከማድረጉ ባሻገር ሞራሉ የላሸቀ፤ ለሥራ ተነሳሽነት የሌለው ፍሬ ቢስ ትውልድ ያደርገዋል፡፡

ለጉዳዩ ትኩረት ካልሰጡት ከሚመለከታቸው አካላት ባሻገር ያለነውና የችግሩን አሳሳቢነት የምንረዳው የሕብረተሰብ ክፍሎች የጫት ሱስ ጐጂነትን በሰከነ መንፈስ ቆም ብለን ካልተገነዘብንና መንግሥትም ከበፊቱ የተሻለ ትኩረት ካልሰጠ፤ ሱሰኝነት በሚያስከትለው ጉዳት በሱስ ያልተለከፉ ዜጐች ጭምር ሊጐዱ እንደሚችሉ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

በዚህ አደገኛ ሱስ እየተሳቡ ያሉ ሥራ አጥ የሆኑ ሰዎች፣ ታዳጊዎች፣ ተማሪዎች፣ ሴቶችና ሥራ ያላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች ቁጥራቸው እየጨመረ መምጣቱ የሀገሪቱ ዕጣ ፈንታ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ መድረሱን የሚያመለክት ነው፡፡

ችግሩ ሲከፋ በየቀያችን ልናስተውለው የምንችለው መረን የለቀቀ አጉራ ዘለልነት፣ ልቅ የሆነ ወሲባዊ ድርጊትና የቀን በቀን ዝርፊያ ልናስተናግድ የግድ ይሆናል፡፡ በዚህ ድርጊትም ‹‹ሳይቃጠል በቅጠል›› ባለማለታችን የዛን ጊዜ ላይ ቆመን የዛሬውን ጊዜ የምንናፍቅበት ወቅት ላይ እንደርሳለን፡፡

በማንኛውም ሁኔታ አሳሳቢ የሚሆነው የዛሬው ሮጦ የማይደክም ጉልበት በጫት ሱስ በመጠመዱና ሞራሉ የደቀቀ ትውልድ በማፍራታችን በሁሉም መስክ ባለድል ለመሆን የሚያስችለንን ትውልድ እንዳናጣ እሳት እየተቀጣጠለ እንዳለ ሁሉ ትውልዱን ለማዳን ውሃ ልንጨምርበት ይገባል፤ ‹‹በምን ዘዴ›› ስንል ደግሞ ከሱስ የፀዳ ዜጋን በመፍጠር ለትውልዱ ምቹ ሁኔታን ከማዘጋጀት ባሻገር ሱስ አስያዥ ለሆነው ጫትና አደንዛዥ ዕፅ ገደብ እንዲደረግለት መፍትሄ በማፈላለግ ሊሆን ይገባል፡፡

ጫትና የወጣቱ ትውልድ... የትምህርት ሥራችን ...ከገጽ 16 የዞረ

Page 16: 72 - MIDROCmidroc-ceo.com/sites/default/files/Newsletters/R_Issue72.pdfAddis Ababa, Ethiopia 1 ከሊቀመንበሩ ማኅደር Volume 14, Issue No. 72 July — August 2013 u¨

16

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 72 July — August 2013

Addis Ababa, Ethiopia

ሰዎች ቁጥራቸው ብዙ የሆኑ ውጤትን ለማብሰር የሚጠቀሙባቸው በዓላትና ዝግጅቶች አሏቸው፡፡ ይህን በሚመለከት ኢትዮጵያውያንም በዓል በማክበርና ልዩ ልዩ ድግስ በማዘጋጀት ብዙ አንታማም፡፡ ሆኖም ከምናከብራቸው በዓላት ሁሉ ከፍተኛውን ደረጃ መያዝ የሚገባው የወጣቶች ትምህርት የመጨረስ እና የመመረቅ ዝግጅት (Graduation) ሊሆን ይገባል፡፡ ይህ ስለሆነም በዛሬው ዕለት ይህን ደማቅ በዓል ለመካፈል ተገናኝተናል፡፡ ይህ በዓል የወላጆች፣ የመምህራንና የልዩ ልዩ አጋሮች ጥረትና ልፋት ተጨምሮበት ከፍተኛ የትምህርት አዝመራ የተሰበሰበበትና ውጤት የተገኘበት በዓል ነው፡፡

ስለሆነም በዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ለዓመታት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው በዛሬው ቀን ለመመረቅ ለበቁና ለዚህ ውጤት እንዲበቁ ከፍተኛ እርዳታ ላደረጉ ወላጆች፣ መምህራንና ሌሎች አጋሮች ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ፡፡

ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ መንግሥት በሰጠው የግል ትምህርት የሥራ መሥራት ፍቃድ መሠረት የተቋቋመ የመጀመሪያው የግል ዩኒቨርሲቲ ሲሆን ሥራ ከጀመረ ሁለት አስር ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ዩኒቨርስቲው የዛሬ አራት ዓመት በገጠመው አስጊ የፋይናንስ ችግር አገልግሎቱን እንዳያቋርጥ ሊቀመንበራችን ክቡር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ባደረጉት አፋጣኝ እርምጃ ችግሩን ያለፈ ታሪክ ማድረግ ተችሏል። በሚቀጥለው አስር ዓመት ዩኒቨርስቲው በአዲስ መስመር እንዲጓዝ ስትራቴጂ ተነድፎለት መጓዝ ከጀመረ አራተኛ ዓመቱን አስቆጥሯል፡፡ በእነዚህ ዓመታት ዩኒቨርሲቲው ወደ አዲስ መስመር የሚጓዝበትን አካሄድ የተሳካ ማድረግ እንዲቻል የመዋቅር፣ የተለያዩ የሥራና የአመራር ለውጦችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

ከ 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ደግሞ የቅርብና ሩቅ ስትራቴጂዎችን በመንደፍ ዩኒቨርስቲው በልዩ ትኩረትና ብርታት መንቀሳቀስ ይጀምራል፡፡ የዛሬ ተመራቂዎችና ጠቅላላ የዚህ በዓል ታዳሚዎች የዩኒቨርሲቲውን የጉዞ አቅጣጫ እንዲያውቁ ማድረግ ጥቅም እንዳለው በመረዳት መልዕክቴን ባጭሩ እንዳቀርብ ፍቃዳችሁን እንድትቸሩኝ እጠይቃለሁ፡፡

ከሊቀመንበራችን በተሰጠን ፍቃድ፣ ድጋፍና መመሪያ መሠረት የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ቀጣይ ሥራዎች በሶስት አብይ ተግባራት ላይ ያተኮሩ ይሆናሉ።

አንደኛው ዓብይ ትኩረታችን፤ ስለትምህርት አሰጣጥ በዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ የረዥም ጊዜ ዕቅድና ስትራቴጂን መቀየስ ሲሆን በዚህ መሠረት፤

1ኛ) ዩኒቨርስቲው በአንደኛ፣ በሁለተኛና በሶስተኛ ድግሪ (PhD) የማስተማር ተግባር ላይ ብቻ እንዲሠማራ ተደርጓል፡፡ ይህም ማለት በTVET ተግባር ላይ አይሠማራም ማለት ይሆናል፡፡

2ኛ) በዩኒቨርሲቲው የሚሰጡት የዲግሪ ትምህርት ዓይነቶች በሶስት የትምህርት መስኮች ወይም ዘርፎች ብቻ ለይ ያተኮረ እንዲሆን

በስትራቴጂያችን ላይ ሠፍሯል፡፡ እነዚህም፤

ሀ) የአንደኛው የትምህርት ዘርፍ ሚናና ሥራን እንደሚከተለው እገልጻለሁ፤

በማኔጅመንት የምንሰጠው ትምህርት ላይ የአመራር (Leadership) ትምህርት እንዲጨመር በማድረግ በሀገሪቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሊያደርግ የሚችል የማኔጅመንትና የሥራ አመራር ፋከልቲ (Management and Leadership Faculty) እንዲኖር ማድረግ ነው፡፡ በአመራር ሥራ የሚሰጠው ትምህርት በሥራ ላይ የሚገኙ የተለያዩ መሪዎችና የወደፊት ተስፋ የተጣለባቸው መሪዎችን በተለያየ የExecutive Program እንዲሳተፉ ማድረግን ይጨምራል።

ለ) ሁለተኛው የትምህርት ዘርፍ የምህንድስና ትምህርትን የሚመለከት ነው። በማዕድን፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና ኮምፒዩቲንግ፣ በአርክቴክቸርና ኧርባን ፕላኒንግ፣ በሜካኒካል ኢንጂነሪንግና በተመሳሳይ መስኮች ላይ የተጀመረው የኢንጂነሪንግ እና ቴክኖሎጂ ፋከልቲ ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና እንዲስፋፋ ማድረግ ይሆናል።

ሐ) ሶስተኛው የትምህርት ዘርፍ የጤና ነክ ትምህርቶችን የሚመለከት ነው። ራሱን የቻለ የሜዲካል ፋከልቲ እንዲኖር ማድረግ የሚያስችል ተግባር ማከናወንና የጤና ትምህርት አሰጣጥ ዘርፍ መፍጠር ይሆናል፡፡ ለዚህ ተግባር በአሁኑ ጊዜ የሰላም የነርሶች ኮሌጅን ከመቻሬ ከፍተኛ ክሊኒክና ፋርማሲ ጋር በማቀናጀት የተጀመረው ሥራ፤ በቅርቡ በሊቀመንበራችን በተደረገ ድጋፍና አመራር መሠረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል በማድረግ የሜዲካል ፋከልቲ ግዴታዎችን በማሟላት የፋከልቲውን መቋቋምና ሥራ መጀመር እውን ማድረግ ላይ ከፍተኛ ሥራ ተጀምሯል፡፡

በመጨረሻም በአጠቃላይ ትምህርት (General Education) ዘርፍ፣ ከመዋዕለ ሕጻናት እስከ 12ኛ ክፍል በተቀናጀ (Integrated) መልኩ ትምህርት እንዲሰጥ በማድረግ ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ወደ ዲግሪ ትምህርት የሚመጡ ተማሪዎችን የዕውቀት ይዘት ለማሻሻል በሚደረገው ሀገራዊ ጥረት ተሳትፎ ያደርጋል፡፡ ስለሆነም ዩኒቨርስቲው “ዩኒቲ አካዳሚ” በሚል ስያሜ በ2006 ዓ.ም. የአፀደ ሕጻናት እና ከ1 እስከ 4ኛ የመማሪያ ክፍሎችን የማዘጋጀት ተግባሩን አጠናቆ ትምህርቱን በመስከረም መስጠት ይጀምራል።

ከላይ የጠቀስኳቸው አንደኛው አብይ ትኩረታችን ሲሆን፣

ሁለተኛው ዓብይ ትኩረታችን፤ በሀገራችን የሚሰጥ የመማር ማስተማር ሂደት የትምህርት ጥራትን (Quality of education) ማዕከል ያደረገ እንዲሆን ለሚደረገው ሀገራዊ ጥረት በአወንታዊ መልኩ አስተዋጽኦ ማድረግ ይሆናል፡፡ የትምህርት ጥራትን ለማስፈን የሚያስችል ተግባርን ለማከናወን ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ተማሪዎች በቂና መጣኝ ዕውቀት እንዲኖራቸው ማድረግ፣ መምህራን ለመማር ማስተማሩ ቁልፍ ተዋንያን እንደመሆናቸው

mL:KT½ kcEF x@Gz!k!†tEV åðsR

ዶ/ር አረጋ ይርዳውDr. Arega Yirdaw

ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር፣ ሚድሮክ ኢትዮጵያChief Executive Officer, MIDROC Ethiopia u’í ¾T>�ÅM (Distributed at no Cost)

Address: Office of the Chief Executive Officer, MIDROC EthiopiaFax: +251-11-371-5988 / 372-4977P.O. Box: 5787, Addis Ababa EthiopiaE-mail: [email protected]: www.midroc-ethiotechgroup.com

የትምህርት ሥራችን ዩኒቨርሲቲውን የመሪዎች መፍለቂያ ያደርገዋል

ወደ ገጽ 15 ዞሯል

የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አረጋ ይርዳው በ30ኛው ዙር የተማሪዎች ምረቃ በዓል ላይ ያደረጉት ንግግር አንደሚከተለው ቀርቧል።