family book study guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ...

212
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical Church of Denver Family book study Guide

Upload: others

Post on 11-Aug-2020

28 views

Category:

Documents


5 download

TRANSCRIPT

Page 1: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር

የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ

Ethiopian Evangelical Church of Denver

Family book study Guide

Page 2: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

2

ማውጫ

ክፍል 1: ጠንካራና ጤናማ ትዳር - - - - - - - - - - - - - - - - - - 8

ክፍል 2: የክርስቲያናዊ ቤተሰብ የልጅ ዕድገት እና ተግባቦት - - -15

ክፍል 3: ክርስቲያናዊ የቤተሰብ አመራር፤ የልጅ አስተዳደግ እና

ተግሣጽ - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - 32

ክፍል 4: ቤተሰብ እና የቅድስና ሕይወት - - - - - - - - - - - - - - - 50

ክፍል 5: በፍቅር መታዘዝ - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - 64

ክፍል 6: በጋብቻ ከተዛመድናቸው ቤተሰቦቻችን ጋር በፍቅር

መኖር - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - 76

ክፍል 7: የኢትዮጵያውያን እና የአሜሪካ ባሕል ልዩነቶች

ተግዳሮቶችና የመፍትሔ ሓሳቦች - - - - - - - - - - - - 90

ክፍል 8: እንደ ባልና ሚስት አብሮ ማገልገል - - - - - - - - - - - 101

ክፍል 9: ጊዜ አጠቃቀም - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - -113

ክፍል 10: በትዳር ውስጥ ኀላፊነትን መወጣት - - - - - - - - - - 122

ክፍል 11: ኑሮ በአሜሪካ - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - 130

ክፍል 12: የማንበብ ባሕልን ማጎልበት - - - - - - - - - - - - - - - 142

ክፍል 13: የቤተሰብን ሙሉ ጤንነት መጠበቅ - - - - - - - - - - - -158

ክፍል 14: የገንዘብ አያያዝ በቤተሰብ ውስጥ - - - - - - - - - - 170

ክፍል 15: ባዶ ጎጆ - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - 187

ክፍል 16: የሥርዓተ ጾታ ትምህርት - - - - - - - - - - - - - - - - - 194

Page 3: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

3

መቅድም

የእግዚአብሔር ቤተሰቦች፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅርና ትሕትና

ሰላም እላችኋለሁ። በመጀመሪያ እግዚአብሔር በዋናነት የመሠረተው

ተቋም ቢኖር ቤተሰብን ነው። የቤተሰብ ጥንካሬ የህብረተሰብ፣ የህብረተሰብ

ጥንካሬ ደግሞ የአገር ጥንካሬ መለኪያ መሆኑ ግልጽ ነው። በተቃራኒው

ደግሞ የቤተሰብ ድክመት የህብረተሰብ፣ የአንድ ህብረተሰብ ድክመት ደግሞ

በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በአገር ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ማሳረፉ አይቀርም።

እግዚአብሔር ለቤተሰብ ትልቅ ስፍራ እንዳለው ለመረዳት በፍጥረት ብቻ

ሳይሆን በአዲስ ኪዳን ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመጀመሪያ

ተዓምራት ያደረገው በገሊላ ታዳሚ ሆኖ በተገኘበት ሠርግ ላይ መሆኑን

ስናይ እግዚአብሔር ለትዳር ያለውን ከፍ ያለ ቦታ ያሳያል። በዚያው ልክ

ሰይጣንም ይህንኑ ስለሚያውቅ ዓላማ አድርጎ ትዳርንና ቤተሰብን በብዙ

እየተዋጋ እንደሆነ እያየን ነው።

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስን ያማከለ ቤተሰብ በሚል

ርእስ ይህንን ጥናት ስታዘጋጅ በቀዳሚነት ለቤተ ክርስቲያናችን ቤተሰብ

ግንባታ ጥናት ሲሆን በተለያዩ ክፍለ አህጉራት ያሉትን የኢትዮጵያና ኤርትራ

ማህበረሰቦችን ታሳቢ በማድረግም ነው። ቤተ ክርስቲያናችን የጤናማ

ቤተሰብ ግንባታ ዋናው መሠረቱ እና ምሰሶው እንዲሁም ማዕከሉ ክርስቶስ

ነው ብላ ታምናለች።

ይህንን ጥናት ስናጠና ቤታችን ለብዙዎች ከሩቅ የሚታይ በተራራ ላይ ያለ

ቤት እንዲሆን ጸሎታችን ነው። ጨለማን ከመገሰጽ ብርሃንን ማብራት

Page 4: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

4

ይመረጣል። ብርሃን ሲበራ ጨለማው ለብርሃን ስፍራውን ይለቃል፣

ይጠፋልም። እኛ እግዚአብሔር እንደተናገረውና በቃሉ እንዳስተማረን

ብንኖር ብዙ በጨለማ ውስጥ ላሉትና በጠላት ተጽእኖ ውስጥ እየተቸገሩ

ላሉ ትዳሮችና ቤተሰቦች የክርስቶስ ምስክር መሆን እንችላለን።

በመጨረሻም ይህንን የጥናት መጽሐፍ በማዘጋጀት ሂደት በግል እና በቡድን

ሆናችሁ በጸሎት፣ በማስተባበር፣ በመጻፍ፣ ሐሳቡን በማዳበር፣ ግብዓት

በመስጠት አስተዋጽኦ ለነበራችሁ የቤተ ክርስቲያናችን ቤተሰቦች በሙሉ

ስላልተገደበ አገልግሎታችሁ እና ስለክርስቶስ ስላላችሁ ቅንዓት ጌታ

ይባርካችሁ እላለሁ። ይህንን የቤተሰብ ትምህርት ለምታጠኑ ቤተሰቦችም

የጥናት ፕሮግራማችሁ የበረከት፣ የመሻሻል፣ የፈውስ እና የመለወጥ

እንዲሆን ጸሎቴ ነው።

የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር፣ የመንፈስ ቅዱስም

ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን!!

መጋቢ እንደሻው ከልክሌ

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ዴንቬር፣ ኮሎራዶ

ሰኔ 2020

Page 5: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

5

ይህንን ጥናት የማጥኛ መመሪያ

❖ የአንድ የጥናት ቡድን አባል መሆናችን የግድ አስፈላጊ ነውን?

❖ እኔና ባለቤቴ ብቻችንን ብናጠናውስ?

ይህን ጥናት እንደ ባልና ሚስት ሁለታችሁ ብቻችሁን የምታጠኑት ከሆነ

ከሌሎች ወዳጆቻችሁና ጓደኞቻችሁ ጋር በኅብረት አብሮ ማሳለፋችሁንና

ከእነርሱም ልምድ የመማራችሁን ዕድል ያስቀርባችኋል። በእያንዳንዱ የጥናት

ክፍለ ጊዜ የሚነሱት ጥያቄዎች እንደ ባልና ሚስት እናንተን ማቀራረብ ብቻ

ሳይሆን ከሌሎች ባልና ሚስቶች ጋር አብራችሁ እያጠናችሁ ሳለ መልካምና

ገንቢ ኅብረት የምታገኙበትን ዕድል ይፈጥርላችኋል።

ስለዚህ ከ 4 እስክ 7 ጥንዶች ሆናችሁ ይህንን ጥናት በጋራ ብታጠኑ

ይመከራል።

❖ የባለ ትዳር ኅብረትን ለመምራት አስፈላጊው ነገር ምንድን ነው?

የዚህን ጥናት ቡድን መምራት ከምታስቡት በላይ ቀላል ነገር ነው።

ምክንያቱም የመሪው ሥራ ሁኔታዎችን ማመቻቸትና ተሳታፊዎች በጥያቄዎቹ

ላይ እንዲወያዩ መርዳት ነው። እናንተ የጥናቱን መጽሐፍ አታስተምሩም።

ነገር ግን ባሎችና ሚስቶች መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነቶችን እንዲረዱና

ከሕይወታቸው ጋር እንዲያዛምዱ ትረዱአቸዋላችሁ። ክርስቶስን ማእከል

ያደረገ ቤተሰብ የቡድን ጥናት ውስጥ የምናገኘው ልዩና አስደናቂ ነገር

ጥንዶች እራሳቸውን ማስተማር መቻላቸው ነው።

Page 6: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

6

በእጃችሁ የገባው ይህ የጥናቱ መመሪያ በቡድኑ ውስጥ እንዴት

እንደምትሳተፉና እንደምትመሩ በቂ መረጃ ይሰጣችኋል።

ይህ ጥናት በማንኛውም የትዳር ዘመን ላይ ላሉ በተለይም ከኢትዮጵያ

ውጪ ለሚኖሩ ባለ ትዳሮች የተዘጋጀ ሲሆን በውስጡ የተካተቱት ርእሶች

በየእለት ኑሮአችን የሚያጋጥሙንን ተግዳሮቶች እንደ ቤተሰብ እንዴት

እንደምንወጣው በቂ መመሪያ የሚሰጥ ነው። እስካሁን ከተጻፉት የቤተሰብ

ጥናት መጻሕፍት የሚለየው በውጪ ሃገር ለሚኖሩ ቤተሰቦች በውጪ

ሀገር በሚኖሩ ቤተሰቦች የተዘጋጀ በመሆኑ ነው። በተጨማሪም በቤተ

ክርስቲያናችን ውስጥ በሚገኙት ቤተሰቦች ላይ በተደረገው ጥናት በእነዚህ

ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ ተጨማሪ ትምህርት እንደሚያስፈልግ ተረጋግጧል።

ለአስጠኚዎች

በዚህ ጥናት ውስጥ ብዙ የንባብ ክፍሎች ስላሉ አስጠኚዎች ቀድመው

ቢያነቡ የትኛውን ክፍል በኅብረት ለማንበብና የትኛውን ደግሞ ባልና

ሚስት በቤታቸው እንዲያነቡ በመምረጥ የጥናቱን ጊዜ በበለጠ በውይይት

ለማሳለፍ ይረዳል። ይህ ትምህርት በጣም አስፈላጊ በመሆኑ ሁሉም ሰው

ክፍሉን ሁሉ በግል ወይም በኅብረት ማንበቡ ግን እጅግ የሚመከር ነው።

❖ ጥናቱ በትክክል ምን ያህል ጊዜ ይፈጃል?

Page 7: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

7

ክርስቶስን ማእከል ያደረገ ቤተሰብ ተከታታይ ጥናት አብዛኛውን ጊዜ

በመጽሐፉ ውስጥ እንደ ተካተቱት ክፍለ ጊዜያት መጠን በወር አንድ ጊዜ

በመገናኘት የሚጠና ሲሆን እያንዳንዱ የጥናት ክፍለ ጊዜ ባልና ሚስት ስለ

ፕሮጄክቶቻቸው የሚሰጡትን ሪፖርት በማካተት ከ60 እስከ 90 ደቂቃዎች

ሊጠይቁ ይችላሉ።

እንደ አስፈላጊነቱ ከጥናቱ በፊት ለሻይ ጊዜ 30 ደቂቃ ቢኖር ይመከራል።

❖ በቡድን ውስጥ ስለ ትዳራችን ማውራት አደገኛ አይሆንምን?

የቡድን ጥናት ጊዜው አስደሳች፣ መረጃ ሰጪና ከሥጋት የነጻ ሊሆን ይገባዋል።

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሦስት ዋነኛ መመሪያዎች እያንዳንዱ የቡድን አባል

ምቾቱ እንዲጠበቅና ከሌሎች ልምድ የመማር ዕድል እንዲያገኝ የሚረዱ

ናቸው።

1. የትዳር ጓደኛችሁን ደስ የማያሰኝ ወይም የሚያሸማቅቅ ምንም

ነገር አትናገሩ።

2. ለመመለስ የማትፈልጉት ጥያቄ ሲያጋጥማችሁ ይለፈኝ በሉ።

3. በተቻለ መጠን ከቡድን ጥናት ስብሰባዎቻችሁ በፊት በጥንድ

መስራት የሚገባችሁን ፕሮጄክት ወይንም ንባብ አሟሉ።

መልካም ጥናት፡፡

Page 8: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

1 ክፍል

ጠንካራና ጤናማ ትዳር (Strong and Healthy Couples)

ዓላማዎች ❖ የህብረተሰብ የቤተ ክርስተያን እና የአገር መሠረት የሆነው

ቤተሰብ ጠንካራና ጤናማ ሆኖ እንዲቀጥል፣

❖ ጋብቻ ለእግዚአብሔር ክብር በራሱ በጎ ፈቃድ የተመሠረተ

የመጀመሪያ ክቡር ተቋም መሆኑን ለማሳየት፣

❖ ጠንካራና ጤናማ ባለ ትዳሮች በቤተ ክርስትያን እንዲበዙና

መልካም ትውልድ እንዲኖር ለማገዝ፣

ግቦች ❖ ባልና ሚስት እግዚአብሔር በጋብቻ ውስጥ የሰጠውን በረከት

እንዲለማመዱና በደስታ እንዲኖሩ ማስቻል፣

❖ መላው ክርስቶስን ያማከለ ሕይወት በመኖር በውጭ ባሉት

ዘንድም መልካም ምስክርነት እንዲኖራቸው ለማድረግ፣

❖ ቤተሰቡ ሁሉ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዲወርሱ

ለማድረግ ነው።

ትርጉም

❖ ጤናማና ጠንካራ ትዳር ቤተሰብ ማለት በሁሉም ነገር ክርስቶስን

8 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 9: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

1 ክፍል

ማእከል አድርጎ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በመልካም ምሳሌነት

የሚኖር ማለት ነው።

ክርስቶስን ማእከል ያደረገ ቤተሰብ

“እግዚአብሔር አብን በእርሱ እያመሰገናችሁ በቃል ቢሆን

ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም

አድርጉት” (ቆላ. 3÷17)

ክርስቶስን ማእከል ያደረገ ቤተሰብ ማለት ጠንካራና ጤናማ ባለ ትዳር ሆኖ

መገኘት ነው። ጠንካራና ጤናማ ባለ ትዳር ወይም ቤተሰብ ማለት ምን

ማለት ነው? ጠንካራ ቤተሰብ ማለት በቃልም ሆነ በሥራ ክርስቶስን ማሳየት

ነው። ጤናማ ቤተሰብ ማለት ደግሞ በአንድነት የክርስቶስ ምስክር ሆኖ

መገኘት ነው።

1) ክርስቶስን ማእከል ያደረገ ጠንካራና ጤናማ ባለ ትዳር ቤተሰብ ሆኖ ለመገኘት የሚጠቅሙ 7ቱ ቁም ነገሮች፤

❖ እርስ በእርስ መዋደድ

❖ እርስ በእርስ ከልብ መመካከር

❖ አንዱ ሌላውን በትሕትና ማገልገል

❖ አንዱ የሌላውን ዋስትና ማረጋገጥ

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 9

Page 10: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

1 ክፍል

❖ ጤናማና ጠንካራ ትውልድ ማፍራት

❖ በጋራ ለእግዚአብሔር መገዛት (ኤፌ. 5፥21)

❖ አንዱ የሌላውን ስጦታ በመደገፍ በቤተ ክርስቲያን ማገልገል

የአንድ ቤተሰብ አስተማሪ ታሪክ

ክርስቶስን የሕይወቱና የቤቱ ማእከል ያደረገ ቤተሰብ እንዲህ ዓይነት ዓለማ

ዊነት የገዘፈበትና ችግር የወፈረበት ሁኔታ ውስጥ መግባት እንደሌለበት

ከሚከተለው ታሪክ ምን እንማራለን? በትዳር 8 ዓመት ቆይተን 2 ልጆች

ከወለድን በኋላ ትዳራችን ሊፈርስ ጫፍ ላይ ደርሷል። ጉዳዩ እንደዚህ ነው፤

ከተጋባን ከአራት ዓመት በኋላ ባለቤቴ እንዲህ ሲል አንድ አሳብ አመጣ።

ሓሳቡም ኑሮአችንን ለማሸነፍ ከእኔ ጋር በስምምነት ፍርድ ቤት ሄደን

ትዳራችንን ካፈረስን በኋላ እርሱ ከኢትዮጵያ በ20 ሺህ ዶላር ሌላ ሴት

አግብቶ መምጣት ነበር። በሓሳቡም መሠረት ኑሮአችን ይሻሻላል በሚል

ሰበብ ያለ ፍላጎቴ ተጭኖኝ ትዳራችን በፍርድ ቤት ፈረሰ።

እርሱም ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ እንዳለው ተደራድሮ በ20 ሺህ ዶላር

ተስማምቶ አንዲት ሴት ከኢትዮጵያ አግብቶ መጣ፤ ብሩንም አገኘን። እኔ

ግን በዚህ ሁሉ ደስተኛ አልነበርኩም። የሚያሳዝነው ከጥቂት ዓመታት

በኋላ ያመጣትን ሴት ፈቶ እንደ ገና ሌላ ሴት በ20 ሺህ ዶላር ከኢትዮጵያ

አመጣ ።

10 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 11: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

1 ክፍል

ትዳሬ ሊፈርስ ጫፍ የደረሰበት ዋና ምክንያት እንግዲህ ይህቺ የመጣችሁ

ሁለተኛዋ ሴት ነች። ይህቺ ሴት እንደ መጀመሪያይቱ ሴት ትንሽ ወራት

ቤታችን ተቀምጣ ራሷን ችላ አልወጣችም። መች ይህ ብቻ ከባለቤቴ ጋርም

ድብቅ የሆነ የፍቅር ግንኙነት እንዳላቸው ስጠራጠር እንደ ነበረው አንድ

ቀን እጅ ከፍንጅ በራሴው መኝታ ቤት ያዝኳቸው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ

ከቤቴ ብር ብላ እንደ ወጣች አልተመለሰችም። እርሱ ግን ጥፋቱን አምኖ

እግሬ ሥር ወድቆ ይቅርታ ጠየቀኝ፤ የልጆቼ አባትና የምወደው የድንግልና

ባሌ ነውና ይቅርታ አደረኩለት።

ነገር ግን እስከ አሁን ድረስ በውጪ ግንኙነት እንዳላቸው ሰዎች ይነግሩኛል።

እኔም አንዳንድ ምልክቶችን እያየሁ በእጅጉ እጠራጠራለሁ፤ ምክንያቱም

ከእኔ ጋራ የደባልነት ዓይነት ኑሮ እንጂ ብወደውም የባሌ ልብ ግን ውጪ

ነው፤ ከእኔ ጋር የለም። ግራ ተጋብቻለሁ፤ ኑሮአችንን ለማሻሻል ተብሎ

የተጀመረ ነገር ኑሮአችንን በጠበጠው፤ እንቅልፍ የለኝም፤ ምግብ መብላት

ያስጠላኛል። ቤቴ ፈርሶ ልጆቼ ተበትነው የአገር መሳቂያና መሳለቂያ ሆኜ

የጌታ ስም ከመሰደቡ በፊት ምከሩኝ።

❖ የእነዚህ ባልና ሚስት መሠረታዊ ችግሮች ምን ምን ናቸው?

❖ ከዚህ ታሪክ ለእኛ የሚጠቅመን ምን ትምህርት እንማራለን?

11 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

11

Page 12: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

1 ክፍል

ተወያዩበት

1) ክርስቶስን ማእከል ያደረገ ጠንካራና ጤናማ ቤተሰብ እንዲኖር የተጋቢዎቹ ኀላፊነት ምን ምን ሊሆኑ ይገባል?

❖ የእሁድ ስብከት ብቻውን ሁሉን ጥያቄያቸውን እንደማይመልስ

አውቀው በግልም ሆነ በጋራ የጋብቻ ትምህርት መማር፣

❖ ከጋብቻ ውጪ በዝሙት ወድቀው ሲገኙ ጌታን ከማሳዘናቸው

ባሻገር አራሚና አስተማሪ የሆነ ለንስሓ የሚያበቃ የሥነ ሥርዓት

እርምጃ ከቤተ ክርስቲያን እንደሚደረግባቸው ማወቅና መቀበል፣

❖ በቤት ለቤት የቤተሰብ ጥናት መታቀፍና ሌሎችም ባለ ትዳሮች

እንዲታቀፉ ማበረታታት፣

❖ አብረው እንዲጸልዩና አብረው እንዲሆኑ እርስ በእርሳቸው

መበረታታት፣

❖ በቁጣቸው ላይ ፀሀይ ሳይገባ እርስ በእርስ ይቅር መባባል፣

❖ በልጆቻቸው ፊት እንደ ተጣሉ ሁሉ ሲታረቁም በልጆቻቸው ፊት

መታረቅ ናቸው፣

2) ክርስቶስን ማእከል ያደረገ ጤናማ እና ጠንካራ ቤተሰብ ባለ ትዳሮች የሚያገኙአቸው ሽልማቶች ምን ምን ናቸው?

❖ ሙሉ ጤናማና ከጭንቀት ነጻ የሆነ ኑሮ መኖር፣

12 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 13: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

1 ክፍል

❖ ኑሮዬ ይበቃኛል በማለትና ጌታን በመምሰል ረክቶ መኖር 1ኛ

ጢሞ. 6፥6፣

❖ በውስጥም በውጪም ባሉት ዘንድ መልካም ምሳሌ

በመሆናቸው ምስጋና መቀበል፣

❖ በመክሊታቸው እንደሚገባ ስለ ነገዱ ከጌታ ዘንድ የክብር

ሽልማት ማግኘት ናቸው።

የመወያያ ጥያቄዎች

1. ቤተ ክርስቲያን የጋብቻ ትምህርት የምታስተምረው ለምንድን

ነው?

2. ክርስቶስን ማእከል ያደረገ ቤተሰብ ማለት ምን ማለት ነው?

3. ክርስቶስን ማእከል ያደረገ ጠንካራና ጤናማ ቤተሰብ ሆኖ

ለመገኘት የሚጠቅሙ ሰባቱ ቁም ነገሮች ምን ምንድን ናቸው?

4. ክርስቶስን ያማከለ ቤተሰብ በኑሮአቸው ሂደትም ሆነ በፍጻሜው

ከሚያገኟቸው ሽልማቶች ጥቂቶቹን ዘርዝር፡፡

5. ከዚህ ትምህርት ለእናንተ የቀሩላችሁን በየተራ ለጉባዔው

ተናገሩ፡፡

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 13

Page 14: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

1 ክፍል

የቤት ስራ

1. ክርስቶስን ማእከል ካደረገ ቤተሰብ የሚጠበቁ አምስት

ነገሮችን ዘርዝሩ።

2. ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስን ያማከሉ ባለ ትዳሮችና ቤተሰቦች

እንዲኖሯት ምን ታድርግ?

3. በዚህ ጥናት መካተት አለባቸው የምትሏቸውን ጠቃሚ ነጥቦች

ዘርዝሩ።

4. በግልም በጋራም ጌታን በቤተ ክርስቲያን የምታገለግሉባቸውን

የአገልግሎት ክፍሎች ምን ምን ናቸው? ለምን?

5. ባልና ሚስት፣ አንዳቸው የሌላቸውን ዋስትና የሚያረጋግጡት

እንዴት ነው?

14 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 15: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

የክርስቲያናዊ ቤተሰብ

የልጅ ዕድገት እና ተግባቦት

2 ክፍል

ዓላማዎች

❖ ክርስቲያናዊ የቤተሰብ ኅብረት እንዲኖር እና በመንፈሳዊ ሕይወት

የጠነከረ፣ ክርስቶስን ማእከሉ ያደረገ እና እግዚአብሔርን የሚፈራ

ጤናማ ቤተሰብ ለመገንባት የሚያስችሉ ጤናማ የተግባቦት

ዘዴዎችን እና ዘይቤዎችን ለማሳየት፣

❖ ጠንካራ ቤተሰብ እንዲኖርና ትክክለኛ ወይም ጤናማ ተግባቦት

ለቤተሰብ ጉልብትና ከልጆች አስተዳደግ ጋር ያለውን ዝምድና እና

አስፈላጊነቱን አጣምሮ ለማሳየት ነው።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 15

Page 16: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

2 ክፍል

መግቢያ

ክርስቶስን ያማከለ የቤተሰብ አመራር ዋነኛ እና አስፈላጊ እውቀት ነው።

የልጅ አስተዳደግ ወይም የቤተሰብ አመራር ጤናማ የሚሆነው ቀና የሆነ

የመግባቢያ ዘይቤ በቤተሰብ መካከል ወይም በወላጆችና በልጆች መካከል

ሲዳብር ነው። የቤተሰብ ተግባቦት እና የልጅ አስተዳደግ ለሕጻናትም ሆነ

ለታዳጊ ወጣቶች ታላቅ አስተዋጽዎ አለው።

በወላጅና በልጆች መካከል ያለ ተግባቦት

በወላጆችና በልጆች መካከል ግልጽና ክፍት የሆነ የመነጋገር እንዲሁም

የመወያየት ነጻነትና ልማድ ሊኖር ይገባል። ይህም ሁኔታ ወይም የውይይቱ

ድርበብ በዓይነት እና በሁኔታ ያልተወሰነ፣ ሓሳብን፣ ብሶትን፣ ስሜትና

ፍርሃትን ለመግለጽ ነጻነት እንዳለ በግልጽ ሲታወቅ ነው። ይህ እንዲሆን

በጥሞና ማድመጥ፣ በተረጋጋ መንፈስ በለሆሳስ መመለስ እጅግ አስፈላጊ

ነው። መግባባት እርግጠኛ ለመሆን ከሚነገሩት ቃላቶች ባለፈ የድምጽ

ለከት እና የሰውነት ቋንቋ እንዲሁም በቃላት ያልተገለጹ ምልክቶች ግንዛቤ

ሊሰጠው ያስፈልጋል። ግልጽና አግባብ ያለው ግንኙነት በቤተሰብ መካከል

ጠንካራ ግንኙነትን ይፈጥራል፤ ያዳብራልም። ከዚያም ባለፈ፣ መደማመጥ

እና አክብሮትን ያዳብራል። ተግባቦትን (Communication) በተመለከተ

በአንክሮ ሊታዩ ከሚገባቸው ዐበይት ሓሳቦች መከከል አንዱ ዕድገትን

ወይም ከዕድገት ጋር በመያያዝ የሚከሰቱ ባሕርያትን መረዳት ነው።

16 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 17: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

2 ክፍል

የመወያያ ጥያቄዎች ❖ በቤተሰብ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጎልበት መደረግ

ያለባቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?

❖ የልጆችን ዕድገት ወይም የዕድገት መጠን መረዳት ለምን

ይጠቅማል? የልጆች ዕድገት ደረጃዎች ምን ምን ናቸው?

ልጆች የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች ሟሟላት ቀላል አይደለም። ወላጆች

ስለ ልጆች ያላቸው መረዳት እና እውቀት በልጅ አስተዳደግ ላይ ከፍተኛ

አስተዋጽኦ አለው። ሆኖም፣ ጥያቄው ወላጅ ስለ አስተዳደግና ስለ ቤተሰብ

አመራር የሚማረው እንዴት ነው? የሚለው ነው። አብዛኛው ወላጅ ከራሱ

አስተዳደግ ይማራል ወይም ስለ አስተዳደግ እውቀት ይገበያል። አንዳንዶች

መጽሐፍ በማንበብ ወይም ትምህርት በመውሰድ ይማራሉ። ይህን ማድረግ

ትክክል ሆኖ ሳለ የተማርነው፣ ያየነው ሁሉ ትክክል ነው? ብለን መጠየቅ

መዘንጋት የለብንም።

በዚህ አጭር ፅሁፍ፣ ውጤታማ እንዲሁም ጤነኛ ቤተሰብ ወይም አስተዳደግ

ምን ይመስላል? በሚለው ሓሳብ ላይ ውይይት ማድረግ ጠቃሚ ነው።

በመጀመሪያ ግን አንዳንድ ዐበይት የሆኑ ሓሳቦችን እንመለከታለን።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 17

Page 18: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

2 ክፍል

የመወያያ ጥያቄዎች

❖ የዕድገት ዓይነቶችን ግለጹ።

❖ የዕድገት ዓይነቶች የሚዛመዱት እንዴት ነው?

❖ ከሁሉም የዕድገት ዓይነቶች ጋር የሚዛመደው የትኛው የዕድገት ዓይነት ነው?

❖ ልጆች በተወሰነ እድሜ እነዚህ የዕድገት ደረጃ ላይ መድረስ ባይችሉ ምን ለውጥ ሊያመጣ ይችላል?

እድገትን መረዳት

የልጆችን ዕድገት የተረዱ ወይም የሚያውቁ እና ዕድገትን በቀና መንገድ

መምራት የሚችሉ ወላጆች ውጤታማ ቤተሰብ እንዲሁም ልጆችን ማፍራት

ይችላሉ። እነዚህንም ውጤታማ ቤተሰብ ብለን ልንጠራቸው እንችላለን።

ዕድገትን መረዳት ዋነኛው ጥቅም ለልጆች ያለንን አመለካከት እንዲሁም

የሚጠበቅባቸውን የዕድገት መጠን ከግንዛቤ ማስገባት እንድንችል ነው።

ይህን በማድረግ እንደ ልጆቹ ዕድገት መጠን አስፈላጊውን አቅርቦት እና

እርዳታ ማወቅ እንዲቻል ነው።

ዕድገት ከማሕጸን የሚጀምር እስከ ጎልማሳነት የሚቀጥል ሂደት ነው።

ዕድገት በአካል፣ በጥንካሬና በእውቀት ማደግን ያካትታል።

18 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 19: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

2 ክፍል

ጥንካሬ ከዕድገት የሚመጣ ለውጥ ነው። እንደዚህ ዓይነቱ ጥንካሬ የሚለካው

በደረጃ ሲሆን፣ ዕድገት ለዚህ የዕድገት ለውጥ አስፈላጊ ነው።

ዕድገት የአካል ዕድገት፣ የአስተሳሰብ ዕድገት፣ የአእምሮ ዕድገት፣ ማኅበራዊ

ዕድገት እና መንፈሳዊ ዕድገት በማለት ተከፍሎ ይታያል። የአካል ወይም

የተፈጥሮ ዕድገት በቁመት፣ በክብደት፣ በውስጥና ውጪ ሕዋሳት የሚሆን

ለውጥ ነው። ይህ ዕድገት የአስተሳሰብ ብስለት ወይም ዕድገት፣ የእውቀት

ደረጃ፣ እንዲሁም የቋንቋ ችሎታን የሚያካትት ሲሆን በተጨማሪም

የአእምሮን መጎልበት አስታኮ ችግሮችን ለመፍታት ሓሳብ ማፍለቅ፣ አርቆ

የማሰብና አስተዋይነትን ያጠቃልላል። የአእምሮ መጎልበት መጎልበት

ስሜቶችን የመለየትና የማወቅ ዕድገትን ያሳያል። እንዲህ ዓይነቱ ዕድገት

ስሜቶችን መግለጽና ስሜትን መቆጣጠር እንዲሁም ለስሜቶች የሚደረጉ

ምላሾችን ያጠቃልላል። ማኅበራዊ ዕድገት ከሰዎች ጋር የመዛመድ ችሎታን

የሚያሳይ ነው። ህብረተሰባዊ ግንኙነትና መግባባት አስፈላጊ የዕድገት ደረጃ

ነው። እንደዚህ ዓይነቱ ዕድገት ከሰዎች ሁሉ ጋር የሚደረግን ግንኙነትና

መግባባትን ያካትታል። መንፈሳዊ ዕድገት የሰው ልጅ በሥጋ፣ በክርስትና

መንፈሳዊ ሕይወቱ፣ በጥበብ እና በሞገስ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያጎለበተ

የሚመጣው የቃሉ እውቀት እና የተገለጠ ሕይወቱን ጭምር ያካትታል።

ኢየሱስም ደግሞ በጥበብና በቁመት በሞገስም

በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ያድግ ነበር። ሉቃ. 2፥52

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 19

Page 20: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

2 ክፍል

ዕድገት የሚወስኑ ክስተቶች

የአካላዊ ዕድገት መጠንና ደረጃ የተለያየ ነው። ይህም የሚሆነው ዘር፣

አካባቢ፣ አመጋገብ፣ ሕመም ወይም አካላዊ እንቅስቃሴ በዕድገት ላይ

ተጽእኖ ሊኖረው ስለሚችል ነው። ወላጆች የልጆችን የዕድገት ደረጃ

ጠንቀቀው ሊያውቁ ይገባል። በዕድገት ላይ ተጽእኖ ሊያመጡ የሚችሉ

ነገሮችን በመረዳት ወላጆች የልጆችን የዕድገት ደረጃና መጠን መንከባከብ

ይችላሉ። ለምሳሌ፣ ለጤና ተስማሚ እና ተመጣጣኝ ምግብ በማዘጋጀት፣

መጻሕፍትን በማንበብ ዕድገትን ማጠናከር ይቻላል።

የቴክኖሎጂ ተጽእኖ በልጆች አስተዳደግ

ቴክኖሎጂ የሰውን ልጅ ሕይወት ያቀለለ መሣሪያ ነው። ብዙ መረጃዎችን በቀ

ላሉ ለማግኘትና ለመለዋወጥ ይጠቅማል። ነገር ግን በሥነ ምግባር ዕድገት

ላይ ትልቅ ተጽእኖ እያመጣ ነው። ብዙ ሰዎች ከሰው ይልቅ ስልካቸው ላይ

ጥገኛ ሆነዋል። ማኅበራዊ የትሥሥር መረቦች መረጃን ከአንድ ምንጭ ወደ

ሌላ በቅጽበት የሚያሰራጩ እንደ መሆናቸው መጠን የሚለቁት መረጃዎች

ትክክለኛ ወይም የሚያንጹ ብቻ ሳይሆኑ መልካምነት የጎደላቸው፣ ነውር

የሆኑም ጭምር ናቸው። በመሆኑም ሰዎች ለተጣራ፣ እውነተኛነት ላለው

መረጃ ብቻ ሳይሆን ለመንፈሳዊ ሕይወትም ጭምር አደጋ ለሚፈጥሩ

መረጃዎች ተጋልጠዋል። በተለይም ልጆችና ቤተሰቦች በስክሪን ገጽ ላይ

የሚያጠፉት ጊዜ መንፈሳዊና ሥነ ምግባራዊ ዕድገታቸውን የሚወስን ሆኖ

ይታያል።

20 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 21: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

2 ክፍል

የመወያያ ጥያቄዎች ❖ የወላጆች ልጆችን ሥነ ምግባር ማስተማር አስፈላጊነቱ ወይም

ጠቀሜታው ምንድን ነው?

❖ ቤተሰብ ተገቢውን የሥነ ልቦና ትኩረት ሲያጣ ወይም ሲያጎድል

በቤተሰብና ማህበረሰቡ ላይ ምን ሊያስከትል ይችላል?

ተወያ ዩበት፡፡

❖ መልካም ባሕርይ ወይም ሥነ ምግባር ያለው ሰው ምን ይመስላል?

ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ምሳሌ የሚሆን ሰው በመጥቀስ ሓሳቡን

ተወያዩ።

የሥነ ምግባር ዕድገት

የሥነ ምግባር ዕድገት ቀስ በቀስ የሚጎለብት፣ ትክክል የሆነውን ከተሳሳተው

የመለየት ችሎታ ነው። ወላጆች የሥነ ምግባር ዕድገት ለልጆቻቸው

ማስተማር የሚችሉት እንዴት ነው? በዚህ አጋጣሚ የማኅበራዊ ድረ

ገፆች እና ቴሌቪዥን በሥነ ምግባር ዕድገት ላይ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ

መነጋገር ጠቃሚ ነው። እውቀት፣ ስሜትን መግዛትና፣ ከሰው ጋር መግባባት

ወይም አብሮ መኖር ሥነ ምግባርን የማዳበር ችሎታ ለማሳደግ ከፍተኛ

አስተዋጽኦ አላቸው። በአካልና በአእምሮ ማደግ እንደሚያስፈልግ እንዲሁ

በሥነ ምግባር ማደግም እጅግ አስፈላጊ ነው።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 21

Page 22: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

2 ክፍል

የመወያያ ጥያቄ ❖ ልጆች ጥሩውንና መጥፎውን እንዴት ይለያሉ? ተቀባይነት ያለው

ሥነ ምግባርስ እንዴት ይማራሉ?

ልጆች በሕይወታቸው ለሚያደርጉት አስፈላጊ ውሳኔዎች ያላቸው ሥነ

ምግባር ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። እያንዳንዱ ቤተሰብ የራሱ የሆነ የሥነ

ምግባር መሥፈርት አለው። ሃይማኖት ወይም እምነት፣ መልካም ሥነ

ምግባርን ለማሳደግ እና ጥሩና መጥፎን ለመለየት ትልቅ ቦታ አለው።

በእምነት ላይ የተመሠረተ መልካም ሥነ ምግባር ልጆች እያደጉ እና እየበሰሉ

በሄዱ መጠን ለሕይወት ጉዞአቸው ጠንካራ መሠረት ነው።

መልካም የሆነ ሥነ ምግባር የባሕርይ መገለጫ አንደኛው መንገድ ነው።

ባሕርይ ደግሞ ለሕይወት አረማመድ እንዲሁም ውሳኔዎች መመሪያ ነው።

ትክክለኛ የሆነ ሥነ ምግባር የላቀ ሕይወት ለመምራት ያገለግላል።

በአብዛኛዎቹ ሰዎች ዘንድ ታማኝነት፣ አክብሮት፣ ፍትሐዊነት፣ ኀላፊነት፣

ተንከባካቢነት እና ጥሩ ዜግነት የጥሩ ሥነ ምግባርና መልካም ባሕርይ

መገለጫዎች ተደርገው ይወሰዳሉ።

22 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 23: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

2 ክፍል

የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣

ቸርነት፣ በጎነት፣ እምነት፣ የውሃት፣ ራስን መግዛት ነው።

እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም።

ገላ 5፥22-23

ልጆችን መልካም ሥነ ምግባር ማስተማር እና እንዲኖሩበት ማድረግ ቀላል

ወይም ትንሽ ኀላፊነት አይደለም። ሥነ ምግባር ቀለል ተደርጎ የሚያዝም

አይደለም፤ ምክንያቱም ትክክለኛ የሆነ ሥነ ምግባር በተለያየ መንገድ

ሊገመገም እና መሥፈርት ሊሰጠው ስለሚያዳግት ነው። በተጨማሪም

ባሕል እንዲሁም እምነት በሥነ ምግባር ላይ ተጽእኖ ስለሚያደርግ ይበልጥ

ትኩረት ሊሰጠው ያስፈልጋል። በቀላሉ የሚሆን ባይሆንም ልጆች ይህን

ዓይነት መሠረታዊ እውቀት ማሳደግ ይኖርባቸዋል።

የመወያያ ጥያቄዎች

❖ ወላጆች ልጆቻቸውን መልካም ሥነ ምግባር የሚያስተምሩት

እንዴት ነው?

❖ የወላጆች ምክርና ተግባር ሥነ ምግባርን ለመገንባት ምን ያህል

አስፈላጊ እንደ ሆነ ተወያዩ?

❖ የወላጆች ምክርና ድርጊት አብሮ ሳይሄድ ሲቀር ምን ሊፈጠር

ይችላል?

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 23

Page 24: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

2 ክፍል

የወላጆች ዓርኣያነት ለልጆች

ወላጆች ለልጆች ዋነኛ ዓርኣያ ናቸው። ወላጆች ባያስተውሉትም ልጆች

ወላጆቻቸውን ያስተውላሉ፤ በተለያየ መንገድ እንደ እነርሱም የመሆን

ፍላጎት አላቸው። ስለዚህም ወላጆች መልካም ዓርኣያ ለመሆን ራሳቸውን

ማስለመድ አለባቸው። አንዳንድ ጊዜ ልጆች የወላጆቻቸውን ባሕርይ

ያሳያሉ ወይም ያንጸባርቃሉ።

ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ድርጊቶች ወይም ባሕርይ በመመልከት ለልጆች

የሚያሳዩትን ዓርኣያነት ይገምግሙ፤

❖ ሁልጊዜ እውነተኛ ነዎት? ልጆችን እንዲዋሹልዎት ጠይቀው

ያውቃሉ?

❖ ሰዎችን ያማሉ?

❖ ለሌሎች አክብሮትን ያሳያሉ?

❖ ጤናማ አኗኗር ይለማመዳሉ?

❖ ለራስዎ ሕይወት አክብርዎት አለዎት?

❖ ጥሩና የሚወድዋቸው እንዲሁም የሚያከብርዋቸው ጓደኞች

አለዎት?

እንዲህ ዓይነት ባሕርያት በወላጆች ሲገለጡ ልጆችን ለማስተማር አመቺ እና

ውጤታማ መሆን ይቻላል። ልጆች በተለያየ መንገድ ባሕርያትን ይማራሉ፤

24 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 25: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

2 ክፍል

ተቀዳሚና ዋነኛ አስተምህሮዎች ከወላጆችና ከቤተሰብ ይጀምራል።

እንግዲህ እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን

የምትከተሉ ሁኑ፥ ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ

ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና

መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ

በፍቅር ተመላለሱ። ኤፌ. 5፥1

መልካምና ጠንካራ ሥነ ምግባር ልጆች እንዲኖራቸው መልካምና ጠንካራ

የሥነ ምግባር ምሳሌነት ከወላጆች ወይም ከአዋቂዎች ይጠበቃል።

የወላጆች ሥነ ምግባር የልጆቻቸውን ባሕርይ የመቅረጽ አቅም እና

ጉልበት አለው። ስለዚህም ወላጆች ጠንካራ ሥነ ምግባር ሊኖራቸው እና

ለልጆች ምሳሌ መሆናቸው እጅግ አስፈላጊ ነው። ወላጆች የሚናገሩ ብቻ

ሳይሆኑ የሚያደርጉ መሆን አለባቸው። በተለይም የመጀመሪያው ሰባት

ዓመታት ልጆችን መልካም ፈለግ ለማስያዝ ወላጆች ተቀዳሚ ኀላፊነት

አላቸው። ስለዚህም ጊዜ ወስዶ ከልጆች ጋር ስለ መልካም ሥነ ምግባር፣

ውሳኔዎችን በሚመለከት፣ ክፉንና መልካምን መለየትን በሚመለከት

መነጋገርና መመካከር ተገቢ ነው። ልጆች ስሜታዊነት ስለሚያጠቃቸው

አመዛዝኖ ትክክለኛ ውሳኔ መወሰንና መልካም ምግባርን መማር ማስተማር

ለጤናማ ዕድገት ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። ይህ ማለት ልጆች የተሳሳተ

ውሳኔ አይወስኑም ማለት አይደለም። አጋጣሚውን ግን ተጠቅሞ መልካም

ሥነ ምግባር ለማስተማር መጠቀም ተገቢ ነው። ምንም እንኳ ልጆች ወደ

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 25

Page 26: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

2 ክፍል

ጓደኞቻቸው የማድላት ባሕርይ ቢኖራቸውም በዋነኛነት የሕይወት መሪ

አድርገው የሚይዙት ወላጆችን እንደ መሆኑ መጠን ወላጆች ለልጆች ጥሩና

ትክክለኛ ዓርኣያ ለመሆን መጣር አስፈላጊና ጠቃሚ ነው።

ተግባቦት

ሳይሰማ ነገርን በሚመልስ ስንፍናና እፍረት ይሆንበታል።

ምሳሌ 18፥13

ጥሩ ወይም መልካም ወላጅ ለመሆን የሚጠቅሙ ምክሮች

1. ዓይን ለዓይን የመተያየት ጥቅም ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ዓይን ለዓይን የመተያየትን ጥቅም ቀለል አድርገው

ያዩታል። በርካታ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት፣ ልጆችን ዓይን ለዓይን

የመመልከት ጥቅም ከትክክለኛ እድገት ጋር የተያያዘ ነው።

2. በልጆች ልክ ዝቅ ብሎ መናገር ወይም መነጋገር

በልጆች ቁመት መጠን ዝቅ ብሎ ማናገር ጥቅሙ ንግግሩ የማስፈራራት

እንዳይመስልና አቅርቦቱም ተቀባይነት እንዲኖረው ነው።

26 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 27: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

2 ክፍል

3. በሰውነት የሚገለጽ የተቀባይነት ምልክት በአካል ወይም በሰውነት አቀማመጥ የሚተላለፉ መልእክቶች ልጆች

መደመጣቸውን ወይም ወላጆች ለመስማት ዝግጁ መሆን ወይም

አለመሆናቸውን ይገልጻል። ይህ ደግሞ ለመስማት እንዲሁም ለንግግር በር

ይከፍታል።

4. ፊት ላይ የሚታይ ገጽታ የፊት ገጽታ በልጆችና በወላጆች መካከል ለሚኖረው ግንኙነት ከፍተኛ

አስተዋጽኦ አለው። ቀና ወይም መልካም ገጽታን ማሳየት ልጆች ቀና

አመለካከት እንዲኖራቸውና ተገቢውንም ምላሽ እንዲሰጡ አስተዋጽኦ

ያደርጋል።

5. የጋራ ትኩረት በጥሞና ማዳመጥና በጊዜው ለሚደረገው ንግግር ወይም የሓሳብ ልውውጥ

የጋራ ትኩረት ሊኖር ይገባል።

የድምጽ ቃና እና የንግግር ዘይቤ አጠቃቀሞች

የድምጽ አጠቃቀምና የንግግር ዘይቤ ጥሩ ለሆነ መግባባት እና የንግግር

ፍላጎት በር ከፋች ነው።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 27

Page 28: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

2 ክፍል

❖ ምልክቶች በተለያየ መንገድ የሚገለጹ ምልክቶች ለመግባባትና ለንግግር በር ከፋች

ከሆኑት መንገዶች አንዱ ነው። ለምሳሌ፣ ራስን እያወዛወዙ ማዳመጥን

ወይም የሓሳቡ፣ የንግግሩ ተካፋይ መሆንን መግለጽ አንድ መንገድ ነው።

❖ ድምጽ እንዲሁም በድምጽ ብቻ የሚተላለፉ መልእክቶች ግንኙነትን ለማጠንከርና

መግባባትን ለማዳበር አስተዋጽኦ አለው።

❖ በወላጅና በልጅ መካከል ያለ የቦታ ቅርበት ወይም መቀራረብ (Proximity between parent and Child)

ልጆች አድገው የሚፈልጉትን የቦታ ጥበትና ሥፋት እስኪያበጁ ድረስ

ወላጅና ልጅ ተጠጋግቶ መነጋገር ጠቀሜታ አለው። ከልጆች ጋር የሚደረግን

ግንኙነቶች ቃላት አልባ የሆኑ ንግግሮችን ከቃላት ባላነሰ መንገድ ሊያጎለብቱ

ወይም ደግሞ ሊያዳክሙ ይችላሉ።

መግባባትን ለማሻሻል የሚጠቅሙ ዋና ዋና

አስተዋጽኦዎች

ወላጆች ከልጆች ጋር ያላቸውን የንግግር ወይም ጠቅላላ ግንኙነት

ለማጠናከር ማድረግ ከሚችሉት ነገሮች አንዱ የልጆች አመለካከት፣ ሓሳብ

28 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 29: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

2 ክፍል

እና ስሜት ተቀባይነት እንዳላቸው ወላጆች ማሳየት ሲችሉ ነው። ለመነጋገር

ጊዜ መውሰድ አንዱ መንገድ ሊሆን ይችላል። የየቀኑን ውሎ ከልጆች

ጋር የመነጋገር ዘይቤን ማጎልበት አስቸጋሪ የሆኑ ሁኔታዎችን መነጋገር

በሚያስፈልግበት ጊዜ አዳጋች አይሆንም። ልጆች ያላቸውን ማንኛውንም

ስሜት እንዲገልጹ ማበረታታት ለማስተማርም እድል ይከፍታል።

ከልጆች ጋር በሚነጋገሩበት ጊዜ ማዳመጥ ልጆች ለመግለጽ ወይም ለመናገር የሚፈልጉት ነገር ሲኖር መደመጣቸውን

ማወቃቸው እጅግ አስፈላጊ ነው።

ምሳሌዎች እና ጠቃሚ ጥቆማዎች

❖ ልጆች ያላቸውን ሓሳብ ገልጠው እንዲናገሩ ማበረታታት፣

ሳያቋርጡ ማዳመጥ፣

❖ ቃል አልባ የሆኑ ገለጻዎችን ማጤን፣

❖ መደመጣቸውን እንዲረዱ ማድረግ፤ የተናገሩትን ወይም

ያደመጡትን በጥቅሉ መግለጽ፣

❖ አለማቋረጥ እና ለማረም አለመቸኮል ወይም በግምት ሐሳባቸው

ምን እንደ ሆነ ለመግለጽ አለመሞከር፣

❖ መፍትሔ ለመስጠት አለመቸኮል፣

❖ ስሜቶቻቸውን እንዲገልጹ ነጻነት መስጠት፣

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 29

Page 30: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

2 ክፍል

❖ ወላጆች ጥሩ አዳማጮች ሲሆኑ ልጆቻቸውን

አዳማጭነት ያስተምራሉ።

ልጆች ጥሩ አዳማጭ እንዲሆኑ ማበረታታት

ልጆች ብዙ ጊዜ ጥሩ አዳማጭ ለመሆን መማር ወይም እገዛ ይፈልጋሉ።

እንደዚሁም ሌሎች ሲነጋገሩ ማዳመጥ እንዳለባቸው አስታዋሽም ያሻቸዋል።

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ልጆች ተናጋሪ ብቻ ሳይሆን አዳማጭም እንዲሆኑ

ጠቃሚ አስተዋጽኦዎች ይመልከቱ።

❖ ልጆች ተናግረው እንዲጨርሱ መፍቀድ ከዚያ መልስ መስጠት።

ይህንን በማድረግ ልጆችን መስማት ወይም ማዳመጥ ማስተማር

ይቻላል።

❖ ልጆች ሊረዱት የሚችሉትን ሓሳብና ቋንቋ መጠቀም።

❖ የሚሰጡ ትእዛዛት እና መመሪያዎችን ቀላልና ግልጽ ማድረግ።

❖ ትችትን ማስወገድና ጥፋተኝነት እንዲሰማቸው አለማድረግ።

❖ መልካም ዓርኣያ መሆን፡፡

30 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 31: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

2 ክፍል

ማጠቃለያ

ልጆችን የምንመለከትበት መነጽር ዕድገታቸውን ተከትሎ መቀየር

እንዳለበት ከሞላ ጎደል አይተናል። ከልጅ ጋር የምናደርጋቸው ተግባቦቶች

ቀሪ ዘመናቸውን የሚቀርጹ መሆናቸውን ማወቅ ዋናው የትምህርቱ አካል

ነው። ልጆች ሲያድጉ የምንጠቀማቸው የተግባቦት ዘዴዎች፣ የምንሰጣቸው

ክብር እና ፍቅር ሁሉ በሕይወታቸው ታትሞ የሚቀር ነው። ስለዚህ

ልጆቻችንን ስናሳድግ እንዴት ነው የምንግባባው የሚለው ጉዳይ በትኩረት

ተይዞ ቤተሰብ ሊሰራው የሚገባው ጉዳይ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 31

Page 32: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

3 ክርስቲያናዊ የቤተሰብ አመራር፤ ክፍል የልጅ አስተዳደግ እና ተግሣጽ

ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው በሸመገለም ጊዜ

ከእርሱ ፈቀቅ አይልም። ምሳ 22፥6

ተግሣጽን የሚጠብቅ በሕይወት መንገድ ይሄዳል፤

ዘለፋን የሚተው ግን ይስታል። ምሳ 10፥17

ዓላማዎች

❖ የዚህ ትምህርት ዋና ዓላማ የቅጣትን አስፈላጊነት ማስረዳት፣

❖ ቅጣትን፣ ተግሣጽን ለይቶ ለማሳየት እና አቀጣጥንና ልጆችን

አግባብ ባለውና መጽሐፍ ቅዱሳዊ በሆነ መልኩ እንዴት መቅጣት

እንደሚገባን ለማሳወቅ ነው።

32 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 33: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

3 ክፍል

መግቢያ ውጤታማ በሆነ መንገድ ልጆችን በተግሣጽ ማሳደግ አስፈላጊና ዋነኛ ጉዳይ

ነው። ሆኖም ተግሣጽ እና ቅጣት አንድ አይደሉም። ቅጣት ለሆነና

ለተፈጸመ ድርጊት የሚሰጥ ምላሽ ነው። ተግሣጽ ደግሞ ልጆች ራሳቸውን

በመግዛት በትክክለኛው መንገድ እንዲራመዱ የሚያስችል የማስተማርያ እና

የመምከርያ ዘዴ ወይም ሥልት ነው።

ተግሣጽ የሚያተኩረው ማስተማር ወይም መመሪያ መስጠት ላይ ሲሆን

ክፉንና ደጉን ለመለየት፣ ሌሎችን ማክበር፣ ተቀባይነት ያለውን ሥነ ምግባር

ለይቶ ማወቅና በዚያውም እውቀት ራስን መግራት፣ ስሜትን በመግዛት

ማደግና መጎልበትን የማስተማሪያ መንገድ ነው።

ተግሣጽ በቀላሉ የሚወሰድ፣ በዘልማድም የሚደረግ ሳይሆን በእውቀት እና

በማስተዋል እየተጣራ ተግባራዊ የሚደረግ ሥልት ነው። ልጆችን በተግሣጽ

ማሳደግ የተወሳሰበ ክስተት ሊሆን ይችላል። በተጨማሪ ልጆችን በመገሠጽ

ጊዜ ወላጆች የሚያሳዩት ሁኔት ወይም ባሕርይ ወደ ፊት ልጆች የሚኖራቸው

ባሕርይ ላይ ተጽእኖ ይኖረዋል።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 33

Page 34: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

3 ክፍል

ወላጆች ልጆችን በሚገስጹበት ጊዜ ሊኖራቸው የሚገባው ቅድመ መረዳት እና ጥንቃቄ

1. በልጆች ተደጋጋሚ ክርክር ምክንያት ወላዋይነትን

አለማሳየት

ግልፍተኛ በመሆን እና ጠበኝነትን በማብዛት ተግሣጽን ባልተቀበሉ ጊዜ

ወላጆች የሚረቱ ወይም ተስፋ የሚቆርጡ ከሆነ ልጆች የሚገሠጹበትን

ባሕርይ ይለማመዳሉ። ወላጆች በውሳኔ ጽኑ እና የማያወላውሉ ሲሆኑ

ልጆች ተግሣጽን ለመታገል፣ ወላጆችንም ለማዳከም የሚያደርጉትን

ጥረት ይቀይራል። ተግሣጽ እና ቅጣት ያለማወላወል የሚወሰድ እርምጃ

መሆን አለበት። ይህ መርሆ ወላጆችና ጠባቂዎች እንዲሁም ዘመዶችን ሁሉ

ይመለከታል። ልጆች የተሰጣቸውን ወሰን ለማለፍ የተግሣጽን ወሰን

ይደራደራሉ። ለመገሰጽ ማወላወል ካለ ልጆች የሚያስገስጻቸውን ባሕርይ

መለማመድ ወይም መደጋገም ይማራሉ።

34 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 35: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

3 ክፍል

2. መረጋጋት ልጆችን በሚገስጹበት ወይም በሚቀጡበት ጊዜ ወላጆች በተረጋጋ መንፈስ

መሆናቸውን ማጤን አለባቸው። መጮህ ወይም መጠን ያጣ ቁጣን

ማስወገድ ያስፈልጋል። ይህን ማድረግ ለልጆች ጩኸትን እና ቁጣን

ያስተምራል። በረጋ መንፈስ አስፈላጊውን ተግሣጽ ወይም ቅጣት መስጠት

ካልተቻለ ጥቂት ጊዜ በመውሰድ መንፈስን ማረጋጋት እጅግ አስፈላጊ ነው።

መጠን ካጣ ቁጣና ጩኸት ይጠብቃል።

3. የበዛ ትችት ከመጠን ካለፈ ትችት መጠበቅ ወይም መከላከል አስፈላጊ ነው። ጥፋቶችን

ያለ ትችት መግለጥ፣ አስፈላጊውን ተግሣጽ ወይም ቅጣት ማስተላለፍ እና

ልጆችን ማስተማር፣ መምከር የተሻለ መንገድ ነው።

4. ስህተት ላይ ብቻ ማተኮር በጠፋው ወይም በተበላሸው ነገር ላይ ብቻ የበዛ ትኩረት ማድረግ ለተግሣጽ

ወይም ለሚሰጠው ማስተካከያ ክብደት ማጣት መነሻ ምክንያት ይሆናል።

ልጆችን በመገሰጽ ጊዜ መደረግ እና መሆን ያለባቸው ነገሮች

❖ በጥሞና ማዳመጥ

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 35

Page 36: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

3 ክፍል

❖ ሳታቋርጧቸው ልጆች እንዲናገሩ እና ሓሳባችውን እንዲገልጹ

መፍቀድ

❖ ከጩኸት ወይም ልክ ካጣ ቁጣ መቆጠብ

የመወያያ ጥያቄዎች

❖ በተግሣጽ እና ቅጣት መካከል ያሉ ልዩነቶች ምንድን ናቸው?

❖ ቅጣት በደል (abuse) የሚሆነው መቼ ነው?

❖ ተግሣጽ በደል የሚሆነው መቼ ነው?

❖ ትክክለኛ መመሪያ ምንድን ነው?

አስተማሪ ምሳሌዎች

የቡድን አባላት ያላቸውን አመለካከት እንዲያካፍሉ በማድረግ ከዚህ በታች

የተዘረዘረውን ጥናት ተወያዩ።

1. የሦስት ዓመት ልጅ ሱሪውን አረጠበ። አባቱ ተቆጥቶ ሙሉ ቀን

የቆሽሸውን ልብስ ለብሶ እንዲውል አደረገው። እንዲህ ያደረገው ልጁ

ይህን ቅጣት በማስታወስ ደግሞ ሱሪውን እንዳያቆሽሽ በማሰብ ነው።

2. የሦስት ዓመት ልጅ መኪና መንገድ ውስጥ ሮጦ ገባ። ወላጆቹ

ሮጠው ከያዙት በኋላ መኪና መንገድ ውስጥ ስለ መሮጥ የተነገረውን

እያስታወሱ ልጁን መምታት ቀጠሉ።

36 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 37: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

3 ክፍል

3. ሁለት በመዋለ ሕጻናት የሚማሩ ልጆች በመጫወቻ ሲጫወቱ ከቆዩ

በኋላ አንደኛው መጫወቻውን ከሌላኛው ነጥቆ ሮጠ። ወላጅ ልጆቹን

በአንድነት በማምጣት መጫወቻውን ነጥቆ መሮጡ ትክክል እንዳልሆነ

በማስረዳት መጫወቻውን እንዲመልስ ጠየቀ። ሁለቱም ልጆች በተራ

እንዲጫወቱ ጠየቃቸው፤ ወላጅ እየጠበቃቸው ወደ ጨዋታቸው

ተመለሱ።

4. የአምስት ዓመት ልጅ ውጪ ሄዶ ለመጫወት የነበረው እቅድ

በመለወጡ አብዝቶ ያለቅሳል። የልጁ እናት ዝናብ እንደ ሆነና ውጪ

ለመጫወት እንደማያመች በማስረዳት ውጪ የማያስወጣ ጨዋታ

እንዲጫወት ጠየቀችው።

5. የሦስተኛ ክፍል ተማሪ ፈተና በወደቀች ጊዜ ወላጆቿ ከጓደኞችዋ ጋር

እንዳትጫወት አጥብቀው በመከልከል ቀጧት።

6. አንድ የአስራ ሦስት ዓመት ልጅ ቤትሰቦቹን ሳያስፈቅድ ከትምህርት

ሰዓት በኋላ ከጓደኞቹ ጋር ለመዝናናት ሄዶ ከሁለት ሰዓታት ቆይታ

በኋላ ወደ ቤት መጣ። ይህንን የተረዱ ቤተሰቦቹ ለአንድ ሳምንት

ስልኩን በመንጠቅ እንዲቀጣ አደረጉት።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 37

Page 38: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

3 ክፍል

ስንፍና በሕጻን ልብ ታስሮአል፤ የተግሣጽ በትር ግን

ከእርሱ ያርቃታል። ምሳሌ 22፥10

ልጆች ለምን መጥፎ ባሕርይ ያሳያሉ?

የመወያያ ጥያቄዎች

❖ ለውጤታማ ተግሣጽ እርስዎ ምን ያደርጋሉ?

❖ መማታት አንድና ብቸኛ የሆን የተግሣጽ መንገድ አይደለም።

እንዲህ ዓይነቱ ተግሣጽ ደግሞ ለሕጻናት ተገቢ አይደለም።

መማታትን የማያካትት መልካም ምግባርን የማስተማርና

ውጤታማ ተግሣጽ ስልቶችን ተወያዩ።

❖ ልክ ያጣ ቅጣት የልጆችን ባሕርይ አያስተካክልም። አደጋ ወይም

በደል (abuse) ሊያስከትሉ ይችላሉ ተብለው ሊታዩ የሚገባቸው

የሥነ ሥርዐት እርምጃ ዓይነቶችን ወይም ዘዴዎችን ተወያዩ።

አግባብ የሌለው ተግሣጽ ወይም ቅጣት የሚከተሉትን ያካትታል።

❖ ጥፊ፣ መምታት፣ መራገጥ፣ መገፍተር፣ የልጅ እጅ መጠምዘዝ፣

ሆን ብሎ ጉዳት ማድረስ፣ ማቃጠል ወይም መናከስ፣ ጩኸት፣

መሳለቅ፣ ማስፈራራት፣ አዘውትሮ መስደብ፣ በተለይ ደግሞ ሕጻን

38 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 39: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

3 ክፍል

ልጅን መቅጣት፣ ፍቅር ወይም ይቅርታን መከልከል፣ ማሰቃየት፣

እንቅልፍ፣ ምግብ፣ ልብስና፣ መጠለያ መከልከል፣ ልጅን ከቤት

ማስወጣት፣ ለረዥም ጊዜ በቁጣ ልጆችን ማስጨነቅ ወይም

መጋፈጥ፣ ወዘተ. ናቸው።

ተግሣጽ በደል ወይም ጉዳት የሚሆነው እንዴት ወይም መቼ ነው?

ልጆች ማድረግ ያለባቸውንና ማድረግ የሌለባቸው ነገሮች እንዲያውቁ

ሥርዓት መማር አለባቸው። ጥፋትን ባጠፉ ጊዜ ወይም ሥርዓትን ሲያፈርሱ

ተገቢ የሆነ ቅጣት በአንድ ቦታ ከ5-10 ደቂቃ በዝምታ እንዲቀመጡ ማድረግ

በቂ ሊሆን ይችላል። ሌላው አማራጭ ተጨማሪ ጥቅሞችን ለተወሰነ ጊዜ

በመያዝ ተግሣጽን በአግባቡ መፈጸም ይቻላል።

የመወያያ ጥያቄዎች

❖ የቡድን አባላትን ለሁለት በመክፈል ልጆችን በመምታት ስለ

መቅጣትያላቸውን አመለካከት ይነጋገሩ፤ ሓሳባቸውንም

ያካፍሉ።

❖ መጽሐፍ ቅዱስ ልጅን ሥርዓት ስለ ማስተማር ምን ይላል?

❖ ተግሣጽ፣ ቅጣት ወይስ በደል?

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 39

Page 40: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

3 ክፍል

ልጅን ለመቅጣት ወይም ለመገሰጽ መወሰድ ያለባቸው ቅድመ ዝግጅቶች

❖ ራስን ማረጋጋት

❖ ለራስ ጊዜ መውሰድ

❖ ራርቶ ጽኑም መሆን

❖ ምርጫ መስጠት

❖ ማካካሻ ወይም ማስተካከያ ማድረግ

❖ ግጭትን መከላከል

❖ አስቀድሞ ቅጣት ሊያስከትሉ የሚያስችሉ ነገሮች ማሳወቅ

❖ የቅጣቱን ዓይነትና ግነት ማስገንዘብ

የመወያያ ጥያቄዎች

❖ በተግሣጽና በበደል መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

❖ ተግሣጽ በወላጆች እና ልጆችን በሚንከባከቡ መካከል ልዩነት

አለው?

❖ በኮሎራዶ ሕግ መሠረት በልጆች ላይ ጉዳት ወይም በደል ማድረስ

የሚያስከትለው ምንድን ነው?

40 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 41: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

ወላጆች እንዲያውቋቸውና እንዲረዱአቸው የሚገባ ቃላቶች

መረጃ፣

3 ክፍል

Abandonment ትቶ መሄድ

Child Abuse በልጆች ላይ የሚደርስ ጥቃት

ወይም በደል

Child Endangerment ልጆችን በአደጋ ላይ መጣል

Neglect ቸልተኝነት

❖ ልጆችን ለአደጋ ወይም ለጉዳት ማጋለጥ ማለት ምን ማለት ነው?

❖ በደል ማድረስ ምን ማለት ነው?

የልጆች አስተዳደግ የተለያየ በመሆኑ ወላጆች በተለያየ መንገድ ልጆቻቸውን

ሥርዓት እንዲሁም ተግሣጽን ያስተምራሉ። ማንኛውም ወላጅ ልጆችን

በአካልም ይሁን በአእምሮ ጉዳት ማድረስ አይፈልግም። ሆኖም ቅጣትና

በደል ከመመሳሰሉ የተነሳ ለመለየት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። ቅጣት ወደ

በደልነት እንዳይደርስ የተግሣጽን ጽንሰ-ሓሳብ በሚገባ መረዳት አስፈላጊ

ነው። እንደሚታወቀው ልጅን መገሰጽ የልጅን አካሄድ እና ባሕርይ ሊያቀና

እንዲችል ተመልክተናል። ልጆች የህብረተሰብን ሕግ እንዲያውቁና እንዲ

ከተሉ ተግሣጽ አንደኛው የማስተማሪያ መንገድ ነው። ልጆች መጠን እና

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 41

Page 42: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

3 ክፍል

ልክን ተምረው ክፉና ደጉን እንዲያውቁ ማድረግ ተገቢ ነው። ልጅን አለመ

ገሰጽ ጉዳት እንጂ ጠቀሜታ የለውም።

ተግሣጽ ልጅን ለማስተማር የተፈለገውን ከግብ ማድረስ ሲኖርበት ልጆችን

የሚጎዳ ግን በፍጹም መሆን የለበትም። በአንዳንድ ሁኔታዎች ተግሣጽ

ጉዳት ሊያደርስ ይችላል። እንደዚህ በሚሆንበት ጊዜ በልጆች ላይ በደል

ወደመሆን ሊደርስ ይችላል። የልጆች ጥቃት ልጆችን ለመቆጣጠር እና

ወደሚፈለገው ባሕርይ ለማድረስ፣ እንዲሁም ልጆችም ከወላጆች ጋር እንዲ

ስማሙ ከመፈለግ ሊመነጭ ይችላል። ይሁን እንጂ ወላጆች ፈቃዳቸው

እንዲሞላ ያደርጉ ይሆናል እንጂ በኃይልና በማስገደድ ልጆች የሚማሩት

ነገር አይኖርም። ልጆች ላይ የሚደርስ ጥቃት አንዳንዴ ቁጣን ለማብረድ

ከመፈለግም ሊመነጭ ይችላል።

የመወያያ ጥያቄዎች

❖ በኮሎራዶ ሕግ መሠረት በልጆች ወይም በሕጻናት ላይ የሚደርስ

ጥቃት ወይም በደል ትርጉም፣ አንድ ሰው ልጅን በአደገኛ ወይም

ቸልተኛ በሆነ ሁኔታ ውስጥ በማስገባት በልጆች ላይ በደል

ሲያደርስ ወይም ሲፈጽም፣ የአካል ጉዳት ወይም ወደ ሞት

የሚያደርስ ማንኛውም መንገድ፣ የኮሎራዶ ሕግ እንደ እነዚህ

ያሉ ድርጊቶችን ጥቃት ወይም በደል ብለው ይጠራሉ።

❖ ይህ በደል ነውን?

42 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 43: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

3 ክፍል

❖ ሕግ ወላጆች ለልጆች አስፈላጊውን እንክብካቤ እና ጥበቃ

እንዲያደርጉ በኀላፊነት ይጠይቃል። ልጆች በወላጆቻቸው

እንክብካቤና ኀላፊነት ሥር እያሉ ጉዳት ላይ ቢወድቁ በሕግ

ተጠያቂም ሊሆኑ ይችላሉ።

❖ ልጆችን ለአደጋ ማጋለጥ ምን ማለት ነው?

❖ ልጆች ላይ የሚደርስ ጥቃት ምን ይመስላል?

❖ አደጋ ላይ መጣል፣ በደል ወይም ጉዳት?

ከዚህ በታች የተገለጹትን ሁኔታዎች በማንበብ ከሁለቱ ሓሳቦች የትኛው

ሊሆን እንደሚችል በመግለጽ ተነጋገሩበት።

❖ የሰባት ወር ልጅ ለብቻው ለአንድ ሰዓት ከግማሽ ቤት ውስጥ

መተው፣

❖ የአንድ ዓመት ልጅ በፀሀይ መኪና ውስጥ ትቶ ወደ ሱቅ ሮጥ

ብሎ መግባት፣

❖ የሦስት ዓመት ልጅ ያለ መኪና መቀመጫ ማስቀመጥ፣

❖ አባት ወይም እናት እቃ የተሰበረበትን የአምስት ዓመት ልጅ

በመምታት መቅጣት፣

❖ ሌሎች ሁኔታዎችን ጭምር በመነጋገር ልዩነቶችን ተነጋገሩ፣

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 43

Page 44: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

3 ክፍል

ልጆችን አደጋ ላይ የመጣል ምሳሌዎች

❖ ልጅን ያለ ጠባቂ መተው፣

❖ ግድ የለሽነት፣

❖ ልጆችን ለዕፅ ማጋለጥ፣

❖ ሕጻናት አስካሪ መጠጥ አካባቢ እንዲውሉ ወይም እንዲገኙ

ማድረግ፣

የልጆች ላይ ጥቃት ምሳሌዎች ወይም ዓይነቶች

❖ አካላዊ፣

❖ ወሲባዊ ግንኙነት፣

❖ ስሜታዊ፣

❖ የቃላት ወይም ንግግራዊ እንዲሁም ቸልተኛነት፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች

❖ በልጆች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ወይም በደልን ለመከላከል

ሊወሰዱ የሚገቡ ጥንቃቄዎችን ተነጋገሩ።

❖ ከላይ የተጠቀሱትን የተለያየ በልጆች ላይ የሚደርሱ በደሎችን

ወይም ግድ የለሽነቶችን ምሳሌ በመስጠት ተነጋገሩ፡፡

44 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 45: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

3 ክፍል

❖ እንዲህ ዓይነቱ ድርጊቶች ሊያስክትሉ የሚችሉ ችግሮች

ምንድን ናቸው?

→ ዘላቂ የሆነ የአካል ጉዳት

→ የአእምሮ ዘገምተኝነት

→ በሌሎች ላይ እምነት ማጣት

→ ጸረ ማኅበራዊ ባሕርይ

→ ጠበኝነት

→ ሞት

→ ሌሎችን የማጥቃት ዝንባሌ

→ አናሳ የአእምሮ እና የስሜት ዕድገት

→ ለመጠጥና ለዕፆች መጋለጥ

→ የጤና ጠንቅ

በተጨማሪ እንዲህ ዓይነቶቹ ችግሮች ሌላ ሊያስከትሉ የሚችሉ ነገሮች

በልጅነት ዕድሜ የሚደርሱ ጥቃቶች ዘለቄታ ያለው ጥፋት ሊያመጡ

ይችላሉ። እንዲህ ዓይነቱ ችግር ብዙ ጊዜ በማይስተዋሉ ሁኔታዎች ሊከሰቱ

እንደሚችሉ መገንዘብ አስፈላጊ ነው።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 45

Page 46: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

3 ክፍል

ለምሳሌ፤ ትችት፣ ማሽሟጠጥ፣ ችላ ማለት ወይም ቦታ አለመስጠት

የመሳሰሉት ከግንዛቤ መግባት አለበት።

ለማጠቃለል፣ እንዲህ ዓይነቱ ጉዳይ በቀላሉ የሚታለፍ እንዳልሆነ ግልጽ

ነው። ከባድና ዘላቂ ችግር ሊያደርሱ እንደሚችሉ አስታውሶ ጥንቃቄ

ማድረግ አስፈላጊ ነው።

ልጆችን ለመገሰጽ እጅ ከመሰንዘር በፊት ሊወሰዱ የሚችሉ አማራጮች

❖ ራስን ማቆም፣ መለስ ማለት፣ ራስን ማረጋጋት

❖ ትንፋሽን መቆጣጠር

❖ ከራስ ጋር በመማከር ስሜትን ለማብረድ መሞከር

❖ ንዴትን ለማብረድ ሌላ አማራጭ መፈልግ

❖ ወጣ ብሎ ከሁኔታው ዞር ማለት

❖ በግለት ከመገሰጽ ወይም ሌላ እርምጃ ከመውሰድ

ሁኔታውን ማብረድ

አዎንታዊ መመሪያ ሓሳቦች

1. ልጆችን በቀና መንገድ ለመምራት አዎንታዊነት ያላቸው መመሪያዎች

ላይ የበለጠ ማተኮር ጠቃሚ ነው።

2. ልጆች እንዲገልጹት የሚፈለገውን ባሕርይ ገልጾ ማሳየት።

46 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 47: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

3 ክፍል

3. አዎንታዊነትን የሚያንጸባርቁ ባሕርያትን ማበረታታት፤ ሁኔታዎችንም

አመቺ ማድረግ።

4. በተጨማሪም አሉታዊ የሆኑ ተጻራሪ ባሕርያትን የሚያስከትሉ

ሁኔታዎችን ማስወገድ።

5. ልጆች አግባብ የሌለው ባሕርይ በሚያሳዩበት ጊዜ ከሁኔታው ዘወር

ማድረግ፣ እንዲረጋጉ ማድረግ እና ያሳዩትን ተገቢ ያልሆኑ ባሕርያት

እንዴት መለወጥ እንደሚችሉ መምከር።

6. ተቀባይነት ያላቸው ባሕርያትን ገልጾ በማስተማር የተሻለም ምርጫ

እንዲያደርጉ እገዛ ማድረግ እና አማራጭ ማሳየት።

7. አዎንታዊነት ባለው አቀራረብ እና ተቀባይነት ባለው መንገድ መልካም

ባሕርያትን በፍቅር ማጎልበት።

ጠቃሚ ምክሮች

❖ በአንድ በኩል ከመጠን በላይ የተጋነነ ግሣጼ፣ በሌላ በኩል ደግሞ

የተፈጸመውን ከባድ ጥፋት ቀለል አድርጎ ማየት ጉዳት ያስከትላል።

❖ ያሉትን የቤተሰብ ሕግ በግልጽ ማሳወቅ አስፈላጊ ነው።

❖ አንድ ነገር ከማድረግ ወይም እርምጃ ከመውሰድ በፊት አጥርቶ

ማዳመጥ ተገቢ ነው።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 47

Page 48: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

3 ክፍል

❖ ለጥፋቱ የሚሰጠው ተግሣጽ ከጥፋቱ ጋር ተመጣጣኝ መሆኑ

አስፈላጊ ነው።

❖ የተናገሩትን ማድረግና መፈጸም ወላዋይነትን ያስወግዳል።

❖ ከሁሉ በላይ ማመስገንን እና ለበጎ ነግሮች ጊዜ ሰጥቶ ማበረታታት

ለሌላው ግንኙነት ገንቢነት ጠቀሜታ አለው።

❖ ሥርዓትና ደንብ ያለበት አኗኗር ወጣቶች ሥርዓትና ደንብ ያለው ኑሮ

እንዲኖሩ ከማገዙም በላይ የረጅም ጊዜ መመሪያም ነው። ትኩረት

መስጠት ፍቅርንና በራስ መተማመንን ያጎለብታል።

❖ በቁጣ ወይም ንዴት ጊዜ ጥፋቶችን ለመነጋገር እና መፍትሔ ለመፈለግ

መጣር በእሳት ላይ ቤንዚን እንደ መጨመር ነው።

❖ ከአቅም በላይ ለሆኑ ሁኔታዎች እርዳታ ወይም ምክር መጠየቅ ነገሮችን

በጊዜው ለማስተናገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው።

48 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 49: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

3 ክፍል

ማጠቃለያ

ልጆችን በመልካም ሥነ ምግባር ማሳደግ ምን ጥቅም እንደሚያስገኝ

በዝርዝር አይተናል። እንደ ክርስቲያን ቤተሰብ ልጆች በቃሉ እውቀትና

በዚህ ዓለም እወቀት እየታነጹ ለትውልዱ፣ ለራሳቸው በረከት እንዲሆኑ

ቤተሰብ ትልቅ ሚና ይጫወታል። ሥነ ምግባርን ለመገንባት የሚፈጸሙ

ማናቸውም ድርጊቶች ደግሞ መሠረታቸው ፍቅር መሆን ይኖርበታል። ልጅ

መልካም እንዲሆን መመኘት የመውደድ መግለጫ ነው። በዚህ ጥናት

መግቢያ ክፍል ላይ እንደ ተጠቀሰው “ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው

በሸመገለም ጊዜ ከዚያ ፈቀቅ አይልም” የሚለውን መልእክት በመፈጸም

በመልካሙ መንገድ ለመምራት እንትጋ።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 49

Page 50: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

4 ክፍል

ቤተሰብ እና የቅድስና ሕይወት

ዳሩ ግን እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለ ተጻፈ

የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተም ደግሞ በኑሮአችሁ

ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ። 1ኛ ጴጥ. 1፥15-16

ዓላማዎች

❖ በወላጆችና በታዳጊ ወጣት ልጆቻቸው መካከል ያለውን ሰፊ

ክፍተት በማጥበብ ልጆች ከወላጆቻቸው ተገቢውን የሥነ-ጾታዊ

ትምህርት ድጋፍና ምክር እንዲያገኙ መርዳት።

❖ ታዳጊ ወጣት ልጆችን ከክርስቶስ የቅድስና ሕይወት ከሚያጎድ

ላቸው ዓለማዊ፣ ሥጋዊና ሰይጣናዊ ተግዳሮቶችና ወጥመዶች

እንዲያመልጡ ማገዝ።

❖ ታዳጊ ወጣቶች ክርስቶስን ማእከል ወዳደረገ እውነተኛ የቅድስና

ሕይወት እንዲመጡና ለትውልዳቸው ምሳሌ ሆነው

እግዚአብሔርን እንዲያከብሩ መምራት።

50 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 51: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

4 ክፍል

መግቢያ ክርስቶስን ማእከል ያደረገ ቤተሰብ መጽሐፍ ቅዱስን፣ የእግዚአብሔር ቃልን

የሕይወት መሠረት ካደረገ ቤተሰብ ይወለዳል። ቅድስና የዘመናችን በተለይም

የተተኪው ትውልድ ትልቅ ፈተና ነው። ሌላውም ጉዳዩን ያከበደው በዘመን

ቆይታ ቅድስናንና ወሲባዊ ንጽሕናን በተመለከተ ዓለማዊ አስተሳሰቦችና

ልምምዶች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ዘልቀው መግባታቸው ሲሆን ብቸኛው

መፍትሔ ደግሞ ወደ ሕያው ቃሉ መመለስ ብቻ ነው። በዚህ ክፍል ስለ

ቅድስና ተግዳሮቶችና መወሰድ ስላለባቸው እርምጃዎች መጽሐፍ ቅዱስን

ትኩረት በማድረግ በጋራ እናጠናለን፡፡

የመሪ ርእስ ፍቺዎች (Definitions)

ቅድስና (Holiness) ማለት ሁለንተናን (መንፈስ፣ ነፍስንና ሥጋን) ከዓለም፣

ከሥጋና ከሰይጣን አሠራር በማራቅ ራስን ለእግዚአብሔር ብቻ መለየት

ማለት ነው።

የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ መንፈሳ

ችሁንም ነፍሳችሁንም ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስ

ቶስ በመጣ ጊዜ ያለነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ።

1ኛ ተሰ. 5፥23

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 51

Page 52: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

4 ክፍል

የመወያያ ጥያቄዎች

❖ መጽሐፍ ቅዱሳዊና መሠረታዊ የቅድስና ዓይነቶች የትኞቹ

ናቸው?

❖ በዘመናችን በቤተክርስቲያንና በምእመኖቻቸው ስለ

ቅድስና ሕይወት ያለው ግንዛቤ እና ትኩረት ምን ይመስላል?

ወሲባዊ ንጽሕና (Sexual Purity) ማለት ከጋብቻ ውጪ ማንኛውም

(በሓሳብ ምኞት፣ በቃል እና በአካል) ከሚደረግ ያልተገባና ያልተፈቀደ

ወሲባዊ ንክኪ መራቅ ወይም መጠበቅ ማለት ነው።

ለቅዱሳን እንደሚገባ ግን ዝሙትና ርኩሰት ሁሉ ወይም

መመኘት በእናንተ ዘንድ ከቶ አይሰማ። ኤፌ 5፥3

የውይይት ጥያቄዎች

❖ ብዙ ወላጆች በተቃራኒ ጾታና ወሲባዊ ጉዳዮች ዙርያ ከልጆቻቸው ጋር

በሚጠበቀው መልኩ ውይይት ወይም ጭራሹኑ ግልጽ ውይይት

እንደማያደርጉ ታውቋል። ይህ የሆነበት ምክንያት ምንድን ነው?

❖ ይህን ችግር ለመቅረፍ ወላጆች ሊወስዱ የሚገባቸው ተገቢ

እርምጃዎች ምንድን ናቸው?

52 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 53: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

4 ክፍል

ማሳሰቢያ፤ ቅድስና ብዙ ትርጉም ስለሚኖረው በአለባበስና ወሲባዊ ቅድስና

ዙሪያ ላይ ብቻ አተኩሩ።

ቅድመ ጋብቻ መጠናናት (Courtship) ማለት አንድ ያላገባ ወጣት ወንድና

አንዲት ያላገባች ወጣት ሴት መጋባትን ብቻ ዓላማ በማድረግ ትክክለኛው

የሕይወት ዘመን የትዳር ተጣማሪ መሆናቸውን የሚፈትኑበት ደግሞም

የሚያረጋግጡበት እስከ ጋብቻ ድረስ የሚቆይ የተቃራኒ ጾታ የፍቅር

ግንኙነት ነው።

ሰውዮውም ትክ ብሎ ይመለከታት ነበር እግዚአብሔር

መንገዱን አቅንቶለት እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ

ለማወቅ ዝም አለ። ዘፍ. 24፥21

መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነታ (Truth)

ከላይ ባነሳናቸው ሦስቱ ርእሶች (ቅድስና፣ ወሲባዊ ንጽሕና፣ የቅድመ ጋብቻ

መጠናናት) ዓለም ማለትም ከክርስቶስ ውጭ የሆነው ማኅበረሰብ የራሱ

የሆኑ ትርጉሞችና ልምምዶች እንዳሉት መዘንጋት የለብንም። ትልቁ ፈተና

ግን እነዚህ ዓለማዊ ትርጉሞች፣ አመለካከቶችና ልምምዶች ቀስ በቀስ የቤተ

ክርስቲያን ወሰን በማለፍ የክርስቲያኖችም መሆናቸው ነው። መፍትሔውም

ያለማመቻመች እና ወደ ሕያው የእግዚአብሔር ቃል መመለስ ነው።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 53

Page 54: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

4 ክፍል

ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ በዓለም

ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት

ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት

ስላልሆነ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ

ውስጥ የለም። 1ኛዮሐ. 2፥15 -16

የመወያያ ጥያቄዎች

❖ ቅድስና፣ ወሲባዊ ንጽሕና እና በቅድመ ጋብቻ መጠናናትን

በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚያስተምረን ተጨማሪ

ጥቅሶችን በማየት ተወያዩ።

❖ ቤተ ክርስቲያን ወደ ዓለም ሳትሄድ ዓለም (ዓለማዊነት) ቤተ

ክርስቲያን ውስጥ የገባችባቸውን የቅድስና፣ የወሲባዊ ንጽሕና እና

የቅድመ ጋብቻ መጠናናት አመለካከትና ልምምዶች ምንድን ናቸው?

ተወያዩበት።

የቅድስና እና የወሲባዊ ንጽሕና ተግዳሮቶች

ችግርን ማወቅ የመፍትሔ ግማሽ ደረጃ ነው የሚባለው እውነትነት አለው።

በዚህ ርእስ ሥር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እና ክርስቶስን

ማእከል ያላደረጉ የቅድስና፣ የወሲባዊ ንጽሕና እና የቅድመ ጋብቻ መጠናናት

(በዓለም ዴቲንግ (Dating) የሚባለውን) ችግሮችን እንመለከታለን።

54 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 55: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

4 ክፍል

የመወያያ ጥያቄዎች

❖ በታዳጊ ክርስቲያን ወጣቶች ሕይወት የሚታዩ የቅድስና ተግዳሮቶች

ለምሳሌ የአለባበስ፣ የወሲባዊ ንጽሕና እና የቅድመ ጋብቻ መጠናናት

(በዓለም ዴቲንግ የሚባለው) መሠረታዊ ችግሮች ምንድን ናቸው?

❖ ይህም ማለት በእነዚህ ጉዳዮች ዙሪያ መጽሐፍ ቅዱሳዊና ክርስቲያናዊ

ያልሆኑ አመለካከቶችና ልምምዶችን ምን እንደ ሆኑ መለየትና ማወቅ

ነው።

❖ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚታዩ ያልተገቡ የአለባበስ ዓይነቶች፣

ሰውነትን የሚያጋልጡ አልባሳት የመልበስ ዝንባሌዎች በብዛት

ይታያሉ።

❖ ታዳጊ ወጣቶች ስልኮቻቸውን በመጠቀም በኢንተርኔትና በዩቲውብ

የሚያዩአቸው ወሲባዊ ድርጊቶችን የሚያሳዩ ምስሎችንና ፊልሞችን

መመልከት /ፖርኖግራፊ/።

❖ ከዓለም በቀጥታ በተወሰደው የዴቲንግ (Dating) እና “ቦይ ፍሬንድ”

(Boyfriend) እና “ገርል ፍሬንድ” (Girlfriend) የፍቅር ግንኙነት ያለ

ትክክለኛ የጋብቻ ዓላማና ዝግጅት መጀመር።

❖ የፍቅር ግንኙነት ከጀመሩት “ቦይ ፍሬንድ” ወይም “ገርል ፍሬንድ” ጋር

“በቻት” የፍቅርና የወሲብ ቃላት ልውውጥ።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 55

Page 56: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

4 ክፍል

❖ አካላዊና ወሲባዊ ንክኪ፣ ከንፈር ለከንፈር መሳሳም

/የመዳራት/ እንዲሁም በዝሙት ኀጢአት ውስጥ መውደቅ።

በእነዚህ እና ተያያዥ ችግሮች ያልተገባውንና ትክክለኛ ያልሆነውን የፍቅር

ግንኙነት በመጀመር ከቅድስና መጓደል እና በኀጢአት ውስጥ በመኖር

በሚፈጠሩ የተለያዩ የግብረ ገብና መንፈሳዊ ውድቀቶች ሳቢያ መጽሐፍ

ቅዱሳዊ ወደ ሆነው ቅዱስ ጋብቻ በጊዜውና በበረከት አለመግባት ያጋጥማል።

የቅድስና፣ ወሲባዊ ንጽሕና እና

የቅድመ ጋብቻ መጠናናት ችግሮች መፍትሔ

የመወያያ ጥያቄዎች 1. በትምህርት ቤት ከሚሰጠው የጾታ ትምህርት በፊት ወላጆች ቅድስና

ተኮር የሆነውን የሥነ ጾታ እና ወሲብ ትምህርት በአንደኛ ደረጃ

ትምህርት ቤት ማስጨበጥ ይጠበቅባቸዋል። ከተሞክሮአችሁ ተወያዩ።

2. ወላጆች በሥነ ጾታ፣ በወሲባዊና በተቃራኒ ጾታ የፍቅር ግንኙነት

ጉዳዮች ዙሪያ ከልጆቻቸው ጋር በነጻነት፣ በግልጽነትና በውጤታማነት

ለመወያየት ምን ዓይነት ሁኔታዎችንና ዘዴዎችን ሊጠቀሙ ይችላሉ?

ከተሞክሮአችሁ ተወያዩ።

3. ቀጣዩን አጭር ታሪክ በጥሞና በማንበብ ተወያዩ።

56 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 57: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

ሜሪ እና የወንድ ጓደኛዋ (“ቦይ ፍሬንዷ”)

4 ክፍል

“የሚድል ስኩል” ተማሪና 14 ዓመት ታዳጊ ልጅ ናት፤ ቤተ ክርስቲያን

በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት (Bibile study) ፕሮግራም ትሳተፋለች። እናቷና

አባቷ ጌታን የሚወዱና ቤተ ክርስቲያን ንቁ ተሳትፎ ያላቸው የተወደዱና

የተከበሩ ወላጆች ናቸው። ሜሪ ጆኒ ከሚባል የትምህርት ቤት ጓደኛዋ ጋር

የፍቅር ግንኙነት (ዴቲንግ፤ Dating) ጀምራ ቀጥሎም የጆኒ “ገርል ፍሬንድ”

ሆና ለመቀጠል ወስናለች። ይህ በእንዲህ እንዳለ የሜሪ እናት ወ/ሮ ሳራ

ድንገት በእጃቸው በገባው የልጃቸው የሜሪ ስልክ የተጻጻፈቻቸውን የፍቅር

መልእክቶችና ተቃቅፈው ሲሳሳሙ የሚያሳዩ ፎቶዎችን ከተመለከቱ በኋላ

በእጅጉ አዝነዋል። ለባለቤታቸው ለአቶ መሐሪ ለመናገር ቢያስቡም አቶ

መሐሪ በዚህ ጉዳይ ፊት የማይሰጡና የሚቆጡ መሆናቸውን ስለሚያውቁ

ነገሩን በልባቸው ይዘው ማብሰልሰል ቀጥለዋል።

ልጃቸውን ሜሪን ለማናገር ቢያስቡም እንግዲህ ያለነው ኢትዮጵያ አይደል

አሜሪካ ነው። የዚህ አገር ልጆች ገና በልጅነት ነው ፍቅር የሚጀምሩት ብለው

በማሰብ ለማናገርም ሆነ ተወያይቶ ለማሳመን የሚችሉ አልመሰላቸውም።

ስለዚህ ጉዳዩን በልባቸው ይዘው ማብሰልሰልና መጨነቅ ቀጥለዋል።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 57

Page 58: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

4 ክፍል

በዚህ ታሪክ መሠረት የሚከተሉትን ጥያቄዎች በመወያየት መልሱ

❖ የሜሪ እናት ወ/ሮ ሳራ ምን እንዲያደርጉ ትመክራላችሁ? (ጉዳዩን

የራስ በማድረግ መልሱ)

❖ “ዴቲንግ፣” “ገርል ፍሬንድ” እና “ቦይ ፍሬንድ” የፍቅር ግንኙነት

ክርስቲያናዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው ብላችሁ ታምናላችሁ?

❖ “ዴቲንግ፣” “ገርል ፍሬንድ” እና “ቦይ ፍሬንድ” ከእጮኝነት ጋር

አንድ ዓይነት ነው ወይስ ይለያያል?

የቅድስና፣ ወሲባዊ ንጽሕና እና የቅድመ ጋብቻ መጠናናት ፈተናዎች እና መፍትሔዎች

❖ በወሲባዊና የፍቅር ግንኙነት ዙሪያ ለመወያየት የሚያስችል

የወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ውጤታማና ጤነኛ ግንኙነት

መፍጠር፤

❖ ከዕድሜያቸው ቀድሞ ጾታዊ ወሬዎችና ውይይቶችን

አለማድረግ፤ - ስውር ጥያቄዎችን በመጠየቅ ያሉበትን የእውቀት

ደረጃ በየጊዜው

❖ መፈተሽ፤

❖ የግል፣ የልጅነት የሆኑ አስተማሪና አስቂኝ የፍቅር ገጠመኛችንን

ቀስ በቀስ እያነሱ ማላመድ እና ሓሳብ እንዲሰጡ እና ድፍረት

እንዲኖራቸው መርዳት፤

58 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 59: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

4 ክፍል

❖ በፊልም፣ በቴሌቪዥን ከጓደኞቻቸው የሚመጡትን የተለያዩ

የፍቅር ታሪኮችን በማስታከክ ውይይት ለመጀመር መጠቀም፤

❖ በሓሳብም እንኳን ከልጆቻችሁ ጋር ባትስማሙ በትዕግስት

ማዳመጥና ማስጨረስ፤ በሐሳባቸው ጣልቃ ገብቶ አለማቋረጥ።

❖ በተቃራኒ ጾታ የፍቅርና የወሲብ ግንኙነት ዙሪያ ተገቢውንና በቂ

መጽሐፍ ቅዱሳዊና ሥነ ጾታዊ እውቀት መያዝና ማዳበር።

ከጋብቻ ውጭ /በፊት/ የሆነ በልብ ፈቃድ እና

በራስ ፍላጎት የሚፈጸም

1. የወሲብ ምኞት (Lust) (ማቴ. 5፥28፤ 1ኛዮሐ. 2፥15-16፤ 2ኛጴጥ.

2፥9-10፤ 2ኛጢሞ. 2፥22) 2. አካላዊ ንኪኪ፣ ከንፈር ለከንፈር መሳሳም (መዳራት) (1ኛጴጥ. 4፥3፤

ሮሜ 16፥16)

3. የግብረ ሥጋ ግንኙነት፣ ወሲብ (ዝሙት) 1ኛቆሮ. 6፥18፤ 2ኛቆሮ.

12፥21፤ ገላ. 5፥19፤ ቆላ. 3፥5)

እነዚህ ከላይ የጠቀስናቸው ኀጢአት መሆናቸውን ማወቅና ለልጆች

ከመጽሐፍ ቅዱስ እያሳዩ ማስተማር፣ መምከር እንዲሁም ጥቅሶቹን

በቃላቸው እንዲያጠኑ እና እንዲይዙት ማድረግ ያስፈልጋል።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 59

Page 60: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

4 ክፍል

የዓለምን “ዴቲንግ፣” “ገርል ፍሬንድ” እና የመጽሐፍ ቅዱሱን (Courting) መለየትና ማስተማር።

በተለምዶ በዓለም “ዴቲንግ፣” “ቦይ ፍሬንድ” እና “ገርል ፍሬንድ” የሚል

ቃል ተግባርና ልምምድ በቤተ ክርስቲያን ሙሉ በሙሉ እየገባና እየተለመደ

ይገኛል። ነገር ግን ይህ ቃልና ልምምድ መጽሐፍ ቅዱሳዊም፣ ክርስቲያናዊም

ያልሆነ የዓለማውያን አመለካከትና ልምምድ ሲሆን ሰይጣን ትውልዱን

ከቅድስና ሕይወት ለማውጣት የሚጠቀምበት ረቂቅ የሆነ የዘመናችን

አሠራር ነው። እንዴት?

“ዴቲንግ፣” “ቦይ ፍሬንድ” ወይም “ገርል ፍሬንድ” የፍቅር ግንኙነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነውን?

መሠረታዊ ነጥቦች መሠረታዊው ጉዳይ “ዴቲንግ፣” “ቦይና ገርል ፍሬንድ” ከሚለው ቃል ጋር

ሳይሆን ጉዳዩ በቃላቶቹ ውስጥ ያለው ትርጉምና ሓሳብ ላይ ነው ። ይህም

ሆኖ ትክክለኛውን ቃል ለትክክለኛው ትርጉም መጠቀም የቋንቋ ሥርዓት

ነው። ለምሳሌ፣ “ውሃውን በላሁኝ” እንደማንል “ዴቲንግ፣” “ቦይ ፍሬንድ”

እና “ገርል ፍሬንድ” የሚሉ ቃላቶችንም ሆነ ሃሳቦችን በመጽሐፍ ቅዱሳችን

ውስጥ የማናገኛቸው በክርስቶስ ያልዳነው ማኅበረሰብ ቃላትና ሓሳቦች

ናቸው።

በመጽሐፍ ቅዱሳችን ከጋብቻ በፊት ያለውን የቅድመ ጋብቻ መጠናናት

60 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 61: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

4 ክፍል

ግንኙነትን በትክክል የሚወክለው ቃል ኮርቲንግ (Courting) ሲሆን

ዘፍጥረት 24 በቂ ምሳሌ ይሆነናል። ይህም ግንኙነት ሲጸና ቢትሮትድ (Be-

trothed) ወይም ፊያንሴ (fiance) እጮኛ የሚለውን ቃል እንደምንጠቀም

ያሳየናል። ዘዳ. 22፥ 25

“የዴቲንግ፣” “ቦይ ፍሬንድ፣” “ገርል ፍሬንድ” እና “የኮርቲንግ ፊያንሴ” መሠረታዊ ልዩነቶች

ዴቲንግ (Dating) ኮርቲንግ (Courting)/ Christian

dating

1 ለመዝናናት የጋብቻ ዓላማ

የለውም Recreational & for

fun

ጋብቻን ዓላማ ያደረገ ነው Intentional

for marriage

2

ሁለንተናዊ ዝግጅትንና ጊዜን

አይጠይቅም

ሁለንተናዊ ዝግጅትንና ጊዜን

ያስከብራል/ ይጠብቃል።

3 ሥጋዊ ወይም ግላዊ ፍላጎትን

ይከተላል

የእግዚአብሔርን ፈቃድ ይጠብቃል።

4 ከወላጆች እውቅና ውጭ

በድብቅና በሚስጥር የሚደረግ

ነው። Secrete

በኅብረተሰቡ ዘንድ እውቅና እና ክብር

ያለው ነው። Public

5

ተጠያቂነት የለውም። (No

commitment)

ተጠያቂነት ያለው ነው። (have

commitment)

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 61

Page 62: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

4 ክፍል

ዴቲንግ (Dating)

ኮርቲንግ (Courting)/ Christian

dating

6 ከጋብቻ በፊት መሳሳም፣

አካላዊ፣ ወሲባዊ፣ ንክኪና

ወሲብ ይፈቅዳል።

ከጋብቻ በፊት መሳሳም፣ ወሲባዊ ንክኪ

እና ወሲብ አይፈቀድም።

7

ከአንድ በላይ የፍቅር ጓደኛን

ይፈቅዳል።

በአንድ ጊዜ አንድ የፍቅር አጋርን

ይፈልጋል።

8

ዓለማዊ ነው። (World)

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው። (Word)

9

በሂደት የማይዘልቅ ግንኙነት፤

ፍጻሜው በሃዘንና በጉዳት

የሚቋጭ። (End up

with devastation and

destruction)

ፍጻሜው ያማረ እና ደስተኛ ግንኙነትን

ይፈጥራል። ግንኙነቱ ባይቀጥል እንኳን

በሰላምና በመከባበር የሚቋጭ። (End

up with respect)

10

በግንኙነቱ ውስጥ ያሉ ሰዎች

በተለምዶ የወንድ ጓደኛ እና

የሴት ጓደኛ በማለት ይጠራሉ።

(Traditionally the couples

are identified as boyfriend

and girlfriend)

በግንኙነቱ ውስጥ ያሉ ጥንዶች

እጮኛሞች በመባል ይጠራሉ።

(Biblically the couples are named

as fiancé)

62 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 63: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

4 ክፍል

ማጠቃለያ

ጋብቻ ለአቅመ አዳም በደረሱ ወንድና ሴት መካከል የሚፈጸም የዕድሜ

ልክ ጾታዊ ጥምረት እና ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠ ስጦታና በረከት

ነው። ክርስቲያን ታዳጊ ወጣቶች ወደዚህ ወደ ተቀደሰው ጾታዊ ውህደት

እስኪመጡ ድረስ ራሳቸውን በቅድስና እና እግዚአብሔርን በመፍራት

ከማንኛውም ከጋብቻ በፊት ከሚደረግ ወሲባዊ ንክኪ ራሳቸውን ማራቅና

መጠበቅ ይገባቸዋል። ይህም የሰዎች ሓሳብና መላምት ሳይሆን በየትኛውም

ዘመን እና ሥፍራ መሆንና መከበር ያለበት የሕያው እግዚአብሔር ቃል

ትምህርትና በክርስቶስ አምነው የዳኑ የክርስትያኖች አስተምህሮ ነው።

ስለዚህ ቤተሰብ የልጆችን ዕድገት ዑደት ተከትሎ የሚመጣውን ለውጥ

በመልካም እንዲሻገሩት መርዳት ይጠበቅበታል። በዚህ ሂደት ውስጥ

በዋናነት የልጆችን መንፈሳዊ ጥንካሬና እውቀት ማጎልበት እንደሚያስፈልግ

በመረዳት ወላጆች ልጆችን በማገዝ መትጋት ይኖርባቸዋል።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 63

Page 64: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

5 ክፍል

በፍቅር መታዘዝ

ዓላማዎች ❖ የፍቅርን ትርጉም መረዳት፡፡

❖ መታዘዝ ማለት ምን ማለት ነው የሚለውን በአግባቡ ለመገንዘብና

ለመተግበር፡፡

❖ በፍቅር መታዘዝ እንዴት ይቻላል የሚለወን ከመጽሃፍ ቅዱስ ቃል

ጋር በማዛመድ ለመማር ናቸው፡፡

64 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 65: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

5 ክፍል

መግቢያ

ፍቅር

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉሙ ራስን ለሌላ አሳልፎ መስጠት ነው። ፍቅር ለሌላ

ሰው መራራት፣ ሌላውን እንደ ራስ መመልከት ነው።

መታዘዝ

ለሥልጣን ቃል አዎንታዊ ምላሽን ተግባራዊ በሆነ መልኩ መፈጸም ነው።

ቤተሰብ

ቤተሰብ ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ በደም የሚዛመዱ ወላጆችና ልጆች በጋራ

የሚኖሩበት ኅብረት ነው። ቤተሰብ ሰዎች በአንድ ጣራ ሥር ተሰባስበው

የሚኖሩበት በግልጥነት አንዳቸው ለሌላው የልባቸውን የሚካፍሉበት

ኅብረት ነው። ቤተሰብ እግዚአብሔር የደነገገውና የመሠረተው ተቋም ነው።

የቤተሰብ መሠረት

የቤተሰብ መሠረቱ እግዚአብሔር ሲሆን ይህም መሠረት በፍቅር ላይ የቆመ

ነው። ቤተሰብ የፍቅር ውበት የሚገለጥበት ተቋም ነው። ጌታ ኢየሱስ

በዮሐንስ 15፥12 ላይ ሲናገር “እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በእርሳችሁ

ትዋደዱ ዘንድ ትእዛዜ ይህች ናት” ብሏል። ይህን ትእዛዝ ከመፈጸማችን

በፊት ማወቅና መረዳት ያለብን ጌታ ምን ያህል እንደወደደን ነው። ይህ

ከገባን የሚቀጥለው ጥያቄ፣ ሚስቴን ባሌን ልጆቼን ኢየሱስ እንደሚለው

እየወደድኳቸው ነው ወይ የሚል ሊሆን ይገባል።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 65

Page 66: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

5 ክፍል

የመወያያ ጥያቄዎች

❖ የእግዚአብሔር ቃል ስለ ፍቅር ምን ይላል?

❖ ፍቅርን እናንተ እንዴት ትረዱታላችሁ?

❖ የማያምኑ ሰዎች እንዴት ይረዱታል?

የእግዚአብሔር ቃል ስለ ፍቅር ባሕርያት የሚናገረውን ከ1ኛ ቆሮንቶስ 13፥4-

8 መመልከት ይቻላል፤ ፍቅር ይታገሳል፣ ቸርነት ያደርጋል፣ አይቀናም፣

አይመካም፣ አይታበይም፣ የማይገባውን አያደርግም፣ የራሱን አይፈልግም፣

አይበሳጭም፣ በደልን አይቆጥርም፣ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል፣ ስለ ዓመጻ

ደስ አይለውም፣ ሁሉን ይታገሳል፣ ሁለን ያምናል፣ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፣

በሁሉ ይጸናል እና ዘወትር አይወድቅም።

ስለዚህ ይህንን ሕይወት ለመለማመድ እግዚአብሔር የሰጠን ተቋም

መጀመሪያ ቤተሰብ ነው። በቤተሰብ ውስጥ ይህንን ከተለማመድን ይህንን

ፍቅር ወደ ሌላ ይዘን መሄድ እንችላለን። ፍቅር በስሜት ይገለጥ እንጂ

ከስሜት በላይ ነው። ፍቅር የቃል ኪዳን ሕይወት ነው። ፍቅር ትጋትን

ይጠይቃል። ፍቅር ይገባኛል የማይል ነገር ግን ለሌላው ደስታ የሚሰራ ነው።

ሐዋርያው ጳውሎስም ባሎች ሚስቶቻቸውን ልክ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ

ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሊወዷቸው እንደሚገባ ያሳስባል (ኤፌ. 5፥25)።

ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን የወደዳት ራሱን አሳልፎ በመስጠት ነው። ትልቁ

66 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 67: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

5 ክፍል

ጥያቄ፣ ምን ያህል ራሳችንን ለባላችን ወይም ለሚስታችን እንዲሁም ካሉን

ለልጆቻችን አሳልፈን ለመስጠት ተዘጋጅተናል የሚል ነው።

የመወያያ ጥያቄዎች

❖ የእግዚአብሔር ቃል ስለ መታዘዝ ምን ይላል?

❖ መታዘዝን ቀላል የሚያደርገው ምንድን ነው?

የእግዚአብሔር ቃል መታዘዝን እንደ ሕይወት ዘይቤ ይቆጥራል። እግዚአ

ብሔር ፍጥረትን ያዋቀረው በመታዘዝ ላይ ነው። መታዘዝ የሌለበት

መንፈሳዊነት ሊኖር አይችልም። ስለዚህ ቤተሰብ መታዘዝን የምንለማመድበት

ተቋም ነው። በቤተሰብ ውስጥ የማይገለጥ መታዘዝ እውነተኛና ልባዊ ሊሆን

አይችልም። በኤርምያስ ላይ እንደ ተጠቀሰው “ለአባታችሁ ለኢዮናዳብ

ትዕዛዝ ታዝዛችኋልና … ስለዚህ በፊቴ የሚቆም ሰው ከሬካብ ልጅ

ከኢዮናዳብ ወገን ለዘላለም አይታጣም” አለ (ኤር. 35፥18)። በዚህ ዓውድ

የኢዮናዳብ ልጆች የታዘዙት ለአባታቸው ቢሆንም እንኳ የተደሰተውና

ምላሽ የሰጠው ግን እግዚአብሔር ነው። ሐዋርያው ጳውሎስም፣ “ልጆች

ሆይ ይህ ለጌታ ደስ የሚያሰኝ ነውና በሁሉ ለወላጆቻችሁ ታዘዙ” ይላል

(ቆላ. 3፥20)። እግዚአብሔር መታዘዝን እንደ ሕይወት ምርጫ ሳይሆን

ትእዛዝ አድርጎ ሰጥቶናል። ስለዚህ መታዘዝን መማር ይጠበቅብናል። በሌላ

ሥፍራ “መታዘዝ ከመሥዋዕት ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ

ይበልጣል” ይላል (1ኛ ሳሙ. 15፥22)።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 67

Page 68: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

5 ክፍል

ፍቅርና መታዘዝ በቤተሰብ ውስጥ

የመወያያ ጥያቄ

❖ ፍቅርና መታዘዝን የሚያያይዛቸው ምንድን ነው?

እውነተኛ ፍቅር ወደ መታዘዝ ይመራናል። እግዚአብሔርን መውደድ

የሚገለጠው በመታዘዝ ነው። ፍቅር ቅርርብንና ትሥሥርን ይፈጥራል።

ስለዚህ የምንታዘዘው የቅርበታችንን እና የፍቅራችንን ያክል ነው። ስለዚህ

ቤተሰብ የፍቅር እና የመታዘዝ ውበት የሚገለጥበት ተቋም ነው። መታዘዝ

እግዚአብሔር ለሁላችንም የሰጠን ኀላፊነት ስለሆነ ይህንን ደግሞ

ለመለማመድ ያዘጋጀልን ሥፍራ ቤተሰብ ነው። የመታዘዝ ምሳሌያችን ጌታ

ኢየሱስ ነው፤

ከእነርሱም ጋር ወርዶ ወደ ናዝሬት መጣ ይታዘዝ

ላቸውም ነበር” (ሉቃ. 2፥51)፤ “እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ

ጠበቅሁ በፍቅሩም እንደምንኖር ትእዛዜን

ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ (ዮሐ. 13፥10)።

በእነዚህ ክፍለ ምንባባት እንደምንመለከተው ኢየሱስ ይታዘዝ ነበር። እርሱ

መታዘዝን ከተቀበለው መከራ እንደተማረ እንመለከታለን። ስለዚህ ለጌታ

ፍቅርና መታዘዝ የማይነጣጠሉ አንድ ላይ የተገመዱ እንደሆኑ

እንመለከታለን። ኢየሱስ ለአባቱ መታዘዙ በፍቅሩ ለመኖር እንዳስቻለው

ሁሉ በፍቅሩ መኖሩ ደግሞ ለመታዘዝ እንዲችል አደረገው።

68 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 69: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

5 ክፍል

ቤተሰብን በፍቅርና በመታዘዝ ላይ መገንባት የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን

የሕልውና ጉዳይ ነው። ፍቅር የሌለው ቤተሰብ ሊቆም እንደማይችል

ሁሉ መታዘዝ የሌለበትም ቤተሰብ የተቃወሰ ነው። እንግዲያው የቤተሰብ

የደስታው ምንጭ ፍቅርና መታዘዝ መሆኑን ከተረዳን ተቀምጠን ደስታን

ከመጠበቅ ይልቅ ደስታን የሚፈጥረውን እውነተኛ ፍቅር ወደ መለማመድ

መምጣት አለብን።

ስለዚህ “ፍቅር የራሱን አይፈልግም” እንደሚል ከእኔነት ወጥተን ለቤተሰብ

ደስታ መኖር ወደ ምንችልበት የሕይወት ዘይቤ ውስጥ ያስገባናል። ዘወትር

ፍቅርና መታዘዝ በተገቢው መንገድ በቤተሰብ መካከል ይገለጥ ዘንድ

መሥራት እንዳለብን ማመን አለብን። ያልዘራነውን አናጭድም የዘራነውን

ደግሞ በእጥፍ እናጭዳለን። ስለዚህ ስናፈቅር እና ስንታዘዝ ብዙ ፍቅር እና

መታዘዝ እናጭዳለን።

የፍቅር እና የመታዘዝ ተግዳሮቶች

የመወያያ ጥያቄዎች

❖ በቤተሰብ ላይ ያነጣጠሩ ተግዳሮቶች ምንድን ናቸው?

❖ እኔነት በፍቅርና በመታዘዝ ላይ የሚያስከትላቸው ችግሮች

ምንድ ናቸው ?

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 69

Page 70: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

5 ክፍል

1. እኔነት

እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት

ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ” ፊልጵ. 2፥4።

እኔነት በነገሰበት ቤተሰብ ውስጥ ፍቅርና መታዘዝ ይቀዘቅዛል። አንዱ ከሌላው

እንደሚሻል ሲቆጥር ኅብረቱ ይናጋል። እኔነት ዝቅ ማለትን ስለማይወድ

ሁሌም በሰው ላይ መሰልጠንን ይፈልጋል። ይህ ደግሞ ከጌታችን የተማርነው

አይደለም። እርሱ አምላክ ሆኖ ሳለ ራሱን ባዶ አደረገ፤ የባሪያን መልክ ያዘ

የአገልጋይነት፣ የታዘዘበትን ማንነት ተላበሰ። ስለዚህ የክርስቲያን ቤተሰብ

አንዱ ሌላውን በፍቃዱ የሚያፈቅርበት፣ የሚታዘዝበትና የሚያገለግልበት

ዓውድ ሊሆን ይገባል። ዘወትር ልንጠይቅ የሚገባው ትልቁ ጥያቄ ቤተሰቤን

እንዴት ላገለግል እሻለሁ? የሚል መሆን አለበት።

ለመሆኑ በየዕለቱ ለትዳር ጓደኛችንና ለቤተሰባቸን የምናደርገው መሥዋዕትን

የሚጠይቅ ነገር ምንድን ነው? ጊዜያችንን ሰጥተን፣ ፍላጎታችንን ገትተን

ወዘተ. ቤተሰብ እኛ የምንፈልገውን ነገር የምናደርግበት ተቋም ሳይሆን

እግዚአብሔር ለቤተሰብ በደነገገው ሥርዓት መሠረት በመመላለስ የክርስቶስ

ምስክር ለመሆን ነው።

2. ከሌላው መጠበቅ /Expectation/

ከሌላው መጠበቅ ፍቅርና መታዘዝን ያጨናግፋል። የእኛ ድርሻ የትዳር

ጓደኛችንንና ቤተሰባችንን በማፍቀርና በመታዝዝ ማገልገል ነው። ነገር ግን

70 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 71: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

5 ክፍል

ይገባናል ብለን መጠባበቅ ከጀመርን፣ “ይህን አድርጌአለሁና ይህ ሊደረግልኝ

ይገባል” ማለት ከጀመርን የነበረውን ፍቅርና መታዘዝ እየገደልን እንሄዳለን።

እኛ ለቤተሰባችን የምንታዘዘው በምላሹ ይታዘዙልናል ብለን ሳይሆን

ስለምንወዳቸው ብቻ መሆን አለበት። የእነርሱ ምላሽ ምንም ይሁን ምን

የእኛ ድርሻ በትክክለኛው መንገድ እነርሱን ማገልገልና መታዘዝ ነው።

መጠባበቅ /Expectation/ ለፍቅርና ለመታዘዝ ትልቅ እንቅፋት ነው።

ትልቁ ችግር የሰውን ፍላጎት መረዳትና ማወቅ ስለማንችል ብንጥርም እንኳ

ልናውቅ እንደማንችል ልንረዳ ይገባል። የጠበቅነውን ስናጣ የማንፈለግ፣

የማንወደድ ትኩረት የማይሰጠን ስለሚመስለን ተስፋ እንቆርጣለን፤ ይህ

ደግሞ መራርነትን በሕይወታችን ውስጥ እንዲበቅል በር ይከፍታል።

ለዚህ ትልቁ ምሳሌያችን ጌታ ኢየሱስ ነው። በዮሐንስ 13፥1-17 ላይ ጌታ የደቀ

መዛሙርቱን እግር እንዳጠበ እንመለከታለን። ነገር ግን ኢየሱሰ ከጥቂት ጊዜ

በኋላ ሁሉም ትተውት እንደሚሄዱ ያውቅ ነበር። በተለይ ይሁዳ በገንዘብ

ፍቅር በመነደፉ ምክንያት አሳልፎ ሊሰጠው እንዳለ ያውቃል። ጌታ ግን

እነርሱ በሚያስተናግዱበት መንገድ ሊያስተናግዳቸው አልፈለገም። ምንም

እንኳ እነርሱ ትተውት የሚሄዱ ቢሆኑም፣ ይሁዳም የሚሸጠው ቢሆንም

እንኳን እርሱ ግን ማድረግ የሚገባውን አደረገ፤ “የወደዳቸውን እስከ

መጨረሻ ወደዳቸው” ይላል። የእነርሱ ምላሽ እንደሚጠበቀው ባይሆንም

እንኳ ኢየሱስ በእነርሱ ሁኔታ ሳይሆን የራሱን መልካምነት ብቻ ይገልጥ

ነበር።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 71

Page 72: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

5 ክፍል

እንደ ቤተሰብ ፍቅራችን ይፈተናል። ቤተሰብ ውስጥ አስቸጋሪ ሰው ሊኖር

ይችላል። ልክ ደቀ መዛሙርቱ መካከል ይሁዳ እንዳለ ሁሉ ቤተሰብም

ያስፈለገው ለዚህ ነው። የማይወደደውን ለመውደድ፣ የሚያስቸግረውን

በመታዘዝ ከክርስቶስ የተማርነውን በተግባር ለመግለጥ የምንችልበት

ዓውድ ለመፍጠር ቤተሰብ ያስፈልጋል።

3. በቤተሰብ ላይ ተደጋፊ መሆን

ሁሌም ቢሆን መደገፊያችን እግዚአብሔር መሆኑን ማወቅ አለብን።

ቤተሰብን ከተደገፍን ግን አንድ ቀን የጠበቅነውን ማድረግ ካልቻሉ ተስፋ

እንቆርጣለን። ይህ ደግሞ በመካከላችን ላለው ፍቅር እንቅፋት ይፈጥራል።

ጌታ ኢየሱስ ለዚህ ምሳሌያችን ነው። እርሱ ዘወትር የሚኖረው በአባቱ ላይ

በመደገፍ ነበር። “ነገር ግን ኢየሱስ ሰዎችን ሁሉ ያውቅ ነበር፤ ስለ ሰውም

ማንም ሊመሰክር አያስፈልገውም ነበርና አይተማመንባቸውም ነበረ፤

ራሱ በሰው ያለውን ያውቅ ነበረና” ይላል (ዮሐ. 2፥25)። ይህን እውነት

መረዳት ለቤተሰብ በጣም ጠቃሚ ነው። የቤተሰብ ፍቅር ይጠብቃል፤ እኛ

እንደ ቤተሰብ ውስን እውቀት ያለን፣ ሌላው ቀርቶ ራሳችንን እንኳን በቅጡ

አናውቀውም። እንግዲያውስ ሌላውን ከመደገፍ ይልቅ ሁላችንን ወደ

ተሸከመ እግዚአብሔር ልንመለከት ይገባል።

ኢየሱስ በደቀ መዛሙርቱ የተመለከተው ሽሽት አላስበረገገውም። ጴጥሮስ

“አላውቀውም” ቢል እንኳ ጌታ ለጴጥሮስ የነበረውን ፍቅር አላቀዘቀዘውም።

72 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 73: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

5 ክፍል

ስለ ጴጥሮስ፣ ስለ ይሁዳ ፣እና ስለ እኛ በመስቀሉ ላይ ሞተ። ዘወትር

ቤተሰባችንን የማፍቀርና የመታዘዝ ኀላፊነት እንጂ በእነርሱ ላይ የመደገፍ

መብት አልተሰጠንም። ቤተሰብ ዘወትር የእኛን ፍላጎት ሊያሟላ ሳይችል

ሲቀር መታዘዛችንና ፍቅራችን ስለተደረገልን ነገር ሳይሆን ቤተሰብ ስለሆነ

ብቻ መሆን አለበት።

የመወያያ ጥያቄ

❖ ባሕላችን ፍቅርንና መታዘዝን የሚረዳው እንዴት ነው?

4. የባሕል ተጽእኖ

በባሕላችን መታዘዝ ከፍርሃት የመነጨ እንጂ ከፍቅር የተነሳ አይደለም።

ሚስት ባሏን ትፈራለች። ልጆች በተለይ አባታቸውን ይፈራሉ። ስለዚህ

መታዘዙ እርሱን ለማስደሰት እንጂ ከልብ የመነጨ አይደለም። ይህ ዓይነቱ

መታዘዝ ደግሞ በጣም ክፍተትን በመፍጠር በቤተሰብ መካከል ፍቅር ጎልቶ

እንዳይወጣ እንቅፋት ይፈጥራል። እኛም ድኅረ ዘመናዊ የምንባለው እንኳ

ልጆቻችን እኛን እንዲፈሩን ለማድረግ ብዙ እንጥራለን። መታዘዝ ከቅጣት

ጋር የተያያዘ በመሆኑ የፍቅር መታዘዝ ጉድለት በቤተሰቡ ውስጥ ይታያል።

በዚህም ምክንያት መታዘዙ በማንነታችን ላይ ለውጥ አያመጣም።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 73

Page 74: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

5 ክፍል

ማጠቃለያ

ኢየሱስ የመታዘዝ ምሳሌያችን ነው። አባቱ እንደሚወደው ስለሚያውቅ

ኢየሱስ የሚታዘዘው ከፍቅር የመነጨ መታዘዝን ነበር። ይህን ያደረገው

ለእግዚአብሔር አብ ብቻም ሳይሆን ለማሪያምና ለዮሴፍም ጭምር ነበር።

በባሕላችን ፍቅር የድብቅ ነገር ጉዳይ እንጂ የአደባባይ አይደለም። ስለዚህ

ፍቅርን መግለጥ በንግግርም ሆነ በድርጊት ብዙ አልተለመደም። ስለዚህ

አብዛኛው ነገር የሚከናወነው ከፍርሃት በመነጨ መታዘዝ ነው። ሚስት

ለባሏ ፍቅርን መግለጽ ይከብዳታል፤ ይህንን አልፋ ካደረገች ማኅበረሰቡ

እንደ ዓይን አውጣ ይቆጥራታል። ባልም ሚስቱን አንድታገለግለው እንጂ

ከዚያ ያለፈ ነገር ብዙ አያስብም። ምንም እንኳ አሁን አሁን እየተሻሻለ

ቢሄድም ችግሩ ግን ሙሉ በሙሉ ገና አልተቀረፈም። ስለዚህ የክርስቶስን

ምሳሌ በመከተል በፍቅር እንታዘዝ። ሐዋርያው ጳውሎስ፣ “እግዚአብሔር

አብን በእርሱ እያመሰገናችሁ በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታደርጉትን

ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት” ብሏል (ቆላ. 3፥17)።

74 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 75: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

5 ክፍል

የቤት ሥራ

1. በፍቅርና በመታዘዝ የተገነባ ሕይወት መገለጫው ምንድን ነው?

2. በቤተሰብ መካከል ፍቅርና መታዘዝ እንዲያድግ ምን ማድረግ

አለብን?

3. ማፍቀርና መታዘዝን ቀላል የሚያደርገው ምንድን ነው?

4. ከእኛ የተለየ ባሕርይና ጠባይ ያለውን ሰው እንዴት መውደድና

መታዘዝ ይቻላል?

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 75

Page 76: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

6 ክፍል

በጋብቻ ከተዛመድናቸው ቤተሰቦቻችን ጋር

በፍቅር መኖር

ዓላማዎች

❖ አጥኚዎች በሠፊ ቤተሰብ ውስጥ እንዴት በሰላም መኖር

እንዳለባቸው ይማራሉ።

❖ በቤተሰብ/ቤተዘመድ መካከል ሊፈጠሩ የሚችሉ ተግዳሮቶችን

ለይተው ያውቃሉ።

❖ ጤናማ ገደብ ማበጀት (setting healthy boundary) ምን

ማለት እንደሆነ ይረዳሉ።

መግቢያ

ቤተሰብ/ቤተዘመድ ሲባል እነ ማንን ያጠቃልላል? ቤተሰብ ማለት የሚስት

እናትና አባት፣ ወንድምና እህት እንዲሁም የባል እናትና አባት፣ ወንድ ምና እህ

ት ናቸው። እንደ ባሕላችን አያቶች፣ አጐቶች፣ አክስቶች እና ልጆቻቸውንም

76 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 77: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

6 ክፍል

ይጨምራል። ይህም ማለት አንድ ወንድና አንዲት ሴት በጋብቻ ሲተሳሰሩ

እነርሱ እና ቤተሰቦቻቸው የጋብቻ ዝምድና ይመሠርታሉ ማለት ነው።

ሚስት ባል ስታገባ ከባሏ ቤተሰቦች ጋር እንደ ተቆራኘች ልታውቅ ይገባል፤

ባልም እንደዚሁ። በሮሜ 12፥18 ላይ ሲናገር፣ “ቢቻላችሁስ በእናንተ

በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ” ይላል። ስለዚህ በሰላም፣ በፍቅርና

በመከባበር መኖር የክርስቲያናዊ ቤተሰብ መታወቂያ አንዱ መንገድ ሊሆን

ይገባል።

የጥናቱ ይዘት

ከእነዚህ የቤተሰብ አባላት ጋር በደም ከመተሳሰራችን በላይ የሕይወታችን

ክፍል በመሆናቸው በቀላሉ ልንርቃቸው (ልናስወግዳቸው) አንችልም።

የማንነታችን መሠረቶች ወላጅና አሳዳጊዎች ናቸውና። ከቅርብ ቤተሰብ ጋር

ተስማምቶ እና ተቻችሎ መኖር ለባለ ትዳሮቹ ዘለቄታዊ የትዳር ስኬት

አዎንታዊ ተጽእኖ አለው። በጣም የቅርብ ቤተሰብ ብለን የምንጠራቸው፤

የባል እናት (አማት)፣ የባል አባት (አማች)፣ የሚስት እናትና አባት፣ የግራ

ቀኝ እህቶች (አይቶች) እና ወንድሞች፣ (ዋርሳዎች) ናቸው። በማንኛውም

ነገር የችግር ወይም የደስታ ተካፋይ የሚሆኑት እነዚሁ ቤተሰቦች ናቸው።

ታድያ የተወለዱበትን ቀየ፣ ያደጉበትን መንደር ትቶ ባይተዋር ሆኖ

በሚኖሩበት የስደት አገር የቅርብ ቤተሰብ ማግኘት ከፍተኛ መታደል ነው።

ኑሮን ለማስተካከል ቤተሰብን ለመርዳት ደፋ ቀና ሲባል ሁሉም በየፊናው

ሲባክን በቤት ውስጥ ጓዳንና ልጆችን የሚመለከት፣ በደስታ ጊዜ ደስታን

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 77

Page 78: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

6 ክፍል

የሚካፈል፣ በሕመም የሚያስታምም፣ በወሊድ ጊዜ የሚያርስ፣ ልጆችን

በመንከባከብ፣ ምግብ በማብሰል እና በመሳሰሉት የቅርብ እና እምነት

የሚጣልበት የራስ የሆነ ቤተሰብ ከጎን ሲሆን ትልቅ በረከት ነው። ከዚህ

በተጨማሪ ልጆች በሠፊ ቤተሰብ መካከል ሲያድጉ ባሕል፣ ቋንቋ፣ ፍቅር፣

ታሪክ እንዲሁም ማንነታቸውን እንዲያውቁ ይረዳቸዋል።

የመወያያ ጥያቄዎች

❖ በቅርብ የሚኖሩ የቤተሰብ አባል የሌላት ባለ ትዳር በአካባቢው

ከሚኖሩ የባሏ ቤተሰቦች ጋር ጥሩ መግባባት ቢኖራት ምን ያህል

ልትጠቀም ትችላለች ብላችሁ ታስባላችሁ?

❖ በአማቾችና በምራት መካከል ጤናማ ግንኙነት እንዳይኖር

የሚያደርጉ ነገሮች ምንድን ናቸው?

❖ የባሕርይ ልዩነት ሰዎችን ሊያስማማ የማይችልባቸውን ሁኔታዎች

በመጥቀስ ተወያዩ።

በአማቾች፣ በልጆቻቸውና በባለቤቶቻቸው

መካከል የሚፈጠሩ ችግሮች

❖ የትምህርት፣ የዕድሜ እና የአመለካከት ልዩነት

❖ አንድ ሰው ከተናገረበት ዓውድ ውጭ በራስ መንገድ ነገሮችን

መተርጐም

78 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 79: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

6 ክፍል

❖ የጋራ ፍላጐት ያለመኖር

❖ የስሜት መጐዳት

❖ ተገቢውን አክብሮት ያለመስጠት

❖ አለመተሳሰብ

❖ ጣልቃ ገብነት (በማይመለከታቸው ጉዳይ ጣልቃ ገብቶ ሓሳብ

መስጠት፣ ወዘተ.)

❖ የወጪ መጨመር (ገንዘብ)

❖ በአማትና በምራት መካከል ያለ ውድድር

❖ ስለ ሁኔታዎች አስቀድሞ አለመወያየት

❖ የራስ የሆነ በቂ ጊዜ እና ቦታ እንደ ልብ አለማግኘት

❖ ሚዛን በጎደለ ሁኔታ ለራስ ቤተሰብ መሟገት

ተቆጡ ኀጢአትንም አታድርጉ፤ በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ

አይግባ፤ ለዲያቢሎስም ፈንታ አትስጡት ። ኤፌ. 4፥26

ከላይ ከተጠቀሱት ችግሮች መካከል ጥቂቶቹን እንመልከት

ሀ) የትምህርት፣ የዕድሜ እና የአመለካከት ልዩነት

ሁሉም እናቶች ወይም አባቶች የተማሩ ላይሆኑ ይችላሉ፤ ቢማሩም

በየጊዜው በፍጥነት ከሚለዋወጠው ቴክኖሎጂ ጋር አብሮ የሚያስኬድ

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 79

Page 80: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

6 ክፍል

በቂ እውቀት ላይኖራቸው ይችላል። ይህ ደግሞ ዘመናዊውን አኗኗር፣ የጊዜ

አጠቃቀም፣ ከሰዎች ጋር በሚያደርጉት ውይይት የአመለካከትና የመረዳት

ልዩነትን ይፈጥራል።

❖ ይህን በተመለከተ ትምህርት ሊሆን ይችላል የምትሉትን ተሞክሮ

(ልምምድ) ለጥናት ቡድን አካፍሉ።

ለ) አንድ ሰው ከተናገረበት ዓውድ ውጭ በራስ መንገድ

ነገሮችን መረዳት ወይም መተርጐም

አንድ እናት የልጃቸውን ሚስት ለመጀመሪያ ጊዜ ሲተዋወቋት፣ “ፎቶ ላይ

ሳይሽ ቀጠን ያልሽ መስሎኝ ነበር በአካል ሳይሽ ግን ሞላ ያለ ሰውነት ነው

ያለሽ” ቢሏት ሚስት የሰደቧት ያህል ሊሰማት ይችላል። እናት ግን በሳቸው

አመለካከት ውፍረት የመልካም ኑሮ ውጤት መሆኑን ነው የሚያውቁት፣

መተቸታቸው ሳይሆን ማድነቃቸው ነበር።

❖ የምታውቁት ተመሳሳይ ገጠመኝ ካለ ተወያዩበት፡፡

ሐ) የጋራ ፍላጐት ያለመኖር

ለምሳሌ፤ እናት ሕጻናት ልጆችን ለማሳደግ እንዲረዱ ከአገር ቤት መጥተው

አብረው ይኖራሉ። ባልና ሚስት ከሥራ ወደ ቤት የሚገቡበት ሰዓት

ይለያያል፤ ሚስት ከሥራ ስትመለስ ደክሟት ስለምትመጣ በቀጥታ ወደ

80 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 81: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

6 ክፍል

መኝታ ክፍሏ በመግባት ባሏ እስኪመጣ ትተኛለች። እናት ደግሞ እነርሱ

እቤት ገብተው አብረዋቸው ቡና ጠጥተው ልጆቹን ሰጥተው ለማረፍ

ይጓጓሉ። ታድያ የሁለቱ ፍላጎት አለመጣጣም ቅሬታ ሊፈጥር ይችላል።

መ) የስሜት መጐዳት አንዳንድ ምራቶች ከአክብሮት ይሁን ከፍርሃት የባሎቻቸውን እናቶች

የሚያነጋግሩት በተወሰነ ነገር ዙሪያ ላይ ብቻ ነው። ለምሳሌ፣ ቤትን እና

ልጆችን በተመለከተ ብቻ፤ ይህ ደግሞ እናቶች ራሳቸውን እንደ ቤተሰብ

አካል ከመቁጠር ይልቅ “የተፈለግሁት ልጆች ለማሳደግ ብቻ ነው” ብለው

እንዲያስቡ ያደርጋቸውና ይጐዳሉ። አማቾችም እንዲሁ ለልጃቸው ባለቤት

ስሜት ባለመጠንቀቅና ለልጃቸው በማድላት የልጃቸውን ባለቤት ስሜት

የሚጎዳ ንግግር ሊናገሩ ይችላሉ።

ረ) ተገቢውን አክብሮት ያለመስጠት

ልጆች ላሳደጓቸው ወላጆች የሚገባቸውን አክብሮትና እንክብካቤ

አለመስጠት። እንዲሁም ወላጆች ልጆቻቸው ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን

የሚመሩ አዋቂዎች መሆናቸውን በመዘንጋት እንደ ልጅነት ጊዜ

በማየት በልጆቻቸው ሕይወት ፈላጭ ቆራጭ በመሆን ለልጆቻቸውና

ለባለቤቶቻቸው ተገቢውን አክብሮት አለመስጠት።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 81

Page 82: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

6 ክፍል

ሰ) እናት ወይም አባት አእምሯቸው የሚታደስበትን መንገድ

ያለመፈለግ

እናት ወይም አባት አብረው የሚኖሩ ቢሆን ለእነርሱም በዕድሜ

ከሚመስሏቸው በሓሳብ ከሚግቧቧቸው ሰዎች ጋር ጊዜያቸውን

እንዲያሳልፉ አለማመቻቸት።

ጤናማ ግንኙነት እንዲኖር ምን መደረግ አለበት?

የመፍትሔ ሀሳቦች፡- 4. ጤናማ ግንኙነት ለመፍጠር ጤናማ ገደብ (healthy

boundary) ማበጀት ተገቢ ነው።

እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ከፈጠረ በኋላ በገነት እንዲኖር ሲያስቀምጠው

በገደብ ነበር። “እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፤

ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው

ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህ” (ዘፍ. 2፥16-17)።

ገደብ (boundary) ምንድን ነው? ገደብ ማለት ለግንኙነታችን አካላዊ፣

ስሜታዊ እና ሥነ ምግባራዊ ወሰን ማበጀት ወይም መፍጠር ማለት ነው።

ገደብ መነሻና መቆሚያችንን ማወቅ ማለት ነው። ገደብ ማለት አጥር ሠርቶ

አንደራረስ ማለት ሳይሆን የሁለትዮሽ ትስስብ እና ተግባቦት መፍጠር

82 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 83: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

6 ክፍል

ማለት ነው። ይህም እግዚአብሔር የሰጠንን ኀላፊነት መወጣት እና ለእርሱ

ያለንን ታማኝነት የምንገልጽበት መንገድ ነው።

የገደብ ጥቅም ምንድን ነው? የእግዚአብሔርን ዓላማ በሕይወታችን መፈጸም ያስችለናል፤ “የመንፈስ ፍሬ

ግን ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግስት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ እምነት፣ የውሃት፣

ራስን መግዛት ነው” (ገላ. 5፥22)።

❖ ሌሎችን አልፈን እንዳንጐዳ፣ እንዳናስቀይም ወይም መጠቀሚያ

እንዳናደርጋቸው ይረዳል።

❖ የራሳችንን ሕይወት በመኖር፣ ኀላፊነት መውሰድ እና ሌሎችም

የራሳቸውን እንዲኖሩ ነጻነት እንድንሰጥ ይረዳናል።

❖ መስመር እንዳንዘል ወይም እንዳንስት ማስጠንቀቂያ፣ የት መቆም

እንዳለብን ያስጠነቅቃል።

❖ መርዘኛና ጐጅ ከሆነ ግንኙነት እንድንታቀብ ይረዳናል።

❖ በእግዚአብሔር ቃል በተመሠረተ ማንነት በሃቅ መኖር ያስችላል።

❖ በዕለታዊ ሕይወታችን ከላይ የተጠቀሱትን ዝርዝር ሓሳቦች እንዴት

መተግበር እንደሚገባ ምሳሌ በመስጠት ተወያዩ።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 83

Page 84: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

6 ክፍል

እንደ እግዚአብሔር ቃል የማይኖር ሰው ጤነኛ ገደብ ምን ማለት እንደ ሆነ

አያስተውልም። ስለዚህ በመጀመሪያ ገደብ ማድረግ የሚገባን ለምን ዓላማ

መሆን እንዳለበት ማወቅ ይገባል። ገደብ ሰዎችን ሆን ብሎ ለማራቅ፣

አትድረሱብኝ አልደርስባችሁም በሚል መርህ የተደረገ ገደብ፣ ጥላቻ፣

ራስ ወዳድነት፣ ትምክተኝነት፣ በራስ ያለመተማመን ወይም እኔ ከሌላው

እሻላለሁ ለማለት ሊሆን አይገባም። ይህን ማድረግ ከአንድ ክርስቲያናዊ

ቤተሰብ የሚጠበቅ አይደለምና።

ገደብ ማበጀት የሚገባው መቼ ነው?

ሰዎች ያለ አግባብ ሊጠቀሙብን ሲፈልጉ

❖ እንደ ክርስቲያን ከእኛ እርዳታ የሚፈልጉ ቤተሰቦቻችንን

መርዳት ተገቢና የሚጠበቅብንም ነው። ነገር ግን ሊጠቀሙብን

የፈለጉበት ምክንያት ከራስ ወዳድነት የመነጨ ከሆነ ገደብ ማበጀት

ተገቢ ነው።

❖ የባል ወይም የሚስት ወንድም ወይም እህት በቅርብ ቢኖሩ፣

ሠርተው ራሳቸውን ማስተዳደር ሲገባቸው በተለያየ ጊዜ ከእናንተ

እርዳታ በመጠየቅ ኑሮአችሁን የሚያቃውሱ ከሆነ ገደብ

ሊደረግባቸው ይገባል።

❖ ግጭቶችን ለማስወገድ ሳይቻል ሲቀር፣ በልዩነት ተስማምቶ

84 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 85: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

6 ክፍል

ለመቀጠል መነጋገር እና ተከባብሮ ለመኖር እምነታችንን

በተመለከተ ተገቢ ያልሆነ አስተያየት ወይም ትችት ሲሰነዝሩ።

❖ አማኝ ያልሆኑ ቤተሰቦች ስለ እምነታችን ወይም ስለ ማኅበራዊ

ግንኙነታችን ገንቢ ያልሆነ አስተያየት ሲሰጡ።

5. ጤናማ ግንኙነት እንዲኖር ሌላው ልናደርግ የሚገባን፣ በመካከል

አለመግባባት ሲፈጠር በውይይትና በመከባበር የተፈጠረውን ችግር

መፍታት ነው።

አብዛኛውን ጊዜ ግጭት ሊፈጥሩ የሚችሉ ነገሮችን ቁጭ ብሎ ከመወያየት

ይልቅ የራስን ግምት (assumption) በመውሰድ አንዱ ችግር ሳይፈታ

ሌላው ይደረብና አንድ ቀን እሳትና ነዳጅ በኃይል እንደሚነድ፣ ለማጥፋትም

እንደሚያዳግት እንዲሁ ከባድ ግጭት ይፈጠራል። ስለዚህ ችግሮችን

ከወዲሁ እንደ አመቺነቱ ምናልባት ሚስት ከራሷ ቤተሰቦች፣ ባልም

እንደዚሁ ችግሮችን በመከባበርና በመስማማት ሊፈቱ ይገባል።

6. ባልና ሚስት አንድ አቋም በመያዝ፣ ለቤተሰብ ጣልቃ ገብነት ቦታ

አለመክፈት።

ይህን ማድረግ የሚቻለው ሚስት ባሏን ለቤተሰቦቿ አሳልፋ ባለመስጠት፣

ይልቁን በቤተሰብና በባሏ መካከል ግድግዳ በመሆን ባልን አግባብ ካልሆነ

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 85

Page 86: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

6 ክፍል

ከቤተሰቦቿ ከሚሰነዘር ትችት በመጋረድ ነው። ባልም ሚስቱን ከቤተሰቦቹ

የንቀት ወይም የጥላቻ ንግግር ሊጠብቃት ይገባዋል። ቤተሰቦችም የሁለቱን

መተሳሰር ሲያዩ ከማይገባ ንግግርና ትችት ይቆጠባሉ፤ “ስለዚህ አንድ ሥጋ

ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም። እግዚአብሔር ያጣመረውን

እንግዲህ ሰው አይለየው“ (ማቴ. 19፥6) ።

አስተማሪ ምሳሌ ምርትነሽ በአሜሪካን አገር ለረጅም ዓመታት ኖራለች። ልጇ ሳሙኤል እና

ባለቤቱ ራሔል በሌላ ከተማ ይኖራሉ። ምርትነሽም በየጊዜው እየሄደች

ትጠይቃቸዋለች። ራሔል በጣም ግልጽ፣ ከሰው ጀርባ የማትናገር፣ ሥር ዓት

ያላት ሴት ነች። ከአማቷ ጋር ጥሩ አቀራረብ አላት። ይህን የሚያ የው

ሳሙኤል በመገረም “አንዳንዴ የእሷ እናት ትመስይኛለሽ” ይላታል።

ምርትነሽ የልጇንና የሚስቱን ጥብቅ መቀራረብ ስለምታውቅ በጣም

ትጠነቀቅላታለች። የራሳቸው የብቻ ጊዜ እንዲኖራቸው፣ ወጥተው ቡና

እንዲጠጡ፣ የሚጐበኝ ቦታዎችን እንዲያዩ ትገፋፋቸዋለች። ምርትነሽ

ልጇ ሳሙኤልና ባለቤቱ ራሔል ልጅ ባለመውለዳቸው ቅር ቢላትም በዚህ

ጉዳይ ላይ ምንም ተናግራ አታውቅም። አንድ ቀን ራሔል ስለ አንድ ጓደኛዋ

አከታትላ መውለድ በመገረም ስታወራት ምርትነሽ ሳታስበው ስለ ራሔል

አለመውለድ የማይገባ ቃል ተናገረቻት። በጊዜው የሚያስቀይም መሆኑን

አላሰበችበትም ነበር።

ቀን ቀንን እየወለደ ሲሄድ ራሔል እንደ ቀድሞው አትደውልም፤ መልእክትም

86 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 87: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

6 ክፍል

አትመልስም። ሥራ በዝቶባት ይሆናል በማለት ምርትነሽም ዝም አለች።

አንድ ቀን ልጇ ሲደውል፣ “ምነው ራሔል ጠፋች? ደውላልኝ አታውቅም አለ

ችው። “አይ አልገባሽም እንዴ? ያኔ እኮ በወሬ መካከል በተናገርሽው ንግግር

ተቀይማሻለች አላት።” ምርትነሽ ደነገጠችና “እንዴ! እኔ ብዙ የሚያስቀይም

አልመሰለኝም ነበር፤ ታዲያ ለምን እንዲህ ትይኛለሽ አትለኝም ነበር?

ከሆነም ይቅርታ እጠይቃታለሁ” አለች። ወዲያውኑ “ያስቀይምሻል ብዬ

አላሰብኩም ነበር” በማለት ሁኔታውን በመዘርዘር አስረዳቻት። ራሔልም

በእሷ በኩል የተሰማትን ገልጻ ይቅርታዋን ተቀበለቻት፤ እንደ ገና ወደ

ቀድሞ ግንኙነታቸው ተመለሱ። የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ ልጅ ሲወለድ

ለማረስ በሄደችበትና አብራቸው በቆየችባቸው ቀናት ምርትነሽ በቤት

ውስጥ የሚሠሩ ነገሮችን ከመሥራት ውጭ ልጅ በማጠብ እና በማጸዳዳት

እንድትረዳት ራሔል አትፈቅድም ነበር። “ይህ የኔ እና የባሌ ጉዳይ ነው፣ አንቺ

ድርሻሽን በመወጣት ልጆችሽን አሳድገሽ ለዚህ አድርሰሻል፤ አሁን የልጅ

ልጆችሽን አቅፈሽ እንድትስሚ ብቻ ነው የምፈልገው” ትላታለች። ምርትነሽ

ስለ ራሔል ስትናገር “እኔ መልካም ሰው ሆኜ ወይም ከሌሎች አማቶች

ተሽዬ አይደለም። ባሏን ከወደደች የእርሱ የሆኑትን ቤተሰቦቹን መውደድ

ግዴታዋ እንደ ሆነ፣ እርሱም የእርሷን ቤተሰብ መውደድ እንደሚገባ

ስለምታምን እንጂ” ትላለች። ምንም ተራርቀው ቢኖሩም፣ ራሔል ልጆቿ

የባልዋን እና የእርሷን ቤተሰቦች እንዲያውቁ በተመቻት ጊዜ ሁሉ በቫይበር

(Viber) ታገናኛቸዋለች፤ በስም እየጠራች ታስተዋውቃቸዋለች። ግድግዳ

ላይ በተለጠፈ የዓለም ካርታ ላይ ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን ቦታ ለይታ

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 87

Page 88: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

6 ክፍል

በማሳየት ታስተምራቸዋለች። ልጆቿ ሩቅ ካሉ ቤተሰቦቻቸው ጋር ፍቅር

እንዲመሰርቱ ድልድይ ትሠራለች። ምርትነሽን ለመጠየቅ ሲመጡ እንደ

እንግዳ ሳይሆን እንደ ቤቷ ወጥ ቤት ገብታ ሰርታ ታቀራርባለች።

የመወያያ ጥያቄዎች

❖ ከምርትነሽ እና ከምራቷ ራሔል ምን ትማራላችሁ?

❖ በመጽሐፈ ሩት ውስጥ የተጻፈውን ታሪክ ስታስቡ ሩት

ለአማቷ ለኑሃሚን የነበራትን ፍቅር እና ታዛዥነት

እንዴት ገለጸች?

❖ ኑሃሚን ከምራትነት ባለፈ እንደ እናት ሩትን በመምከር

ምን ያህል እንደረዳቻት እና ይህ መልካም ግንኙነታቸው

የሁለቱንም ሕይወት እንዴት እንደ ለወጠ ተወያዩ።

ማጠቃለያ

እግዚአብሔር ዓላማውን በሕይወታችን ለመተግበር በገደብ እንድንኖር

ይፈልጋል። ገደብን ጤናማ እና ጤናማ ባልሆነ መንገድ ልንጠቀምበት

ስለምንችል ጥንቃቄ እና ማስተዋል ማድረግ ተገቢ ይሆናል። ገደብ

በተገቢው ሁኔታ ከተጠቀምንበት ሰዎችን ጠቅመን እኛም የምንጠቀምበት

ሥልት ነው። ለማይገባ ነገር ተባባሪ እንዳንሆን፣ ቃላችንን አጥፈን

ውሸት እንዳይሆንብን፣ እሺ ለምንላቸው ነገሮች ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ

ነው። ክርስቶስን መምሰል ማለት በሚገባው ቦታ አዎ ወይም አይደለም

ማለት መቻል መሆኑን መዘንጋት የለብንም። እግዚአብሔርን በመፍራት

88 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 89: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

6 ክፍል

የሚመሰረት ግንኙነት እርስ በእርስ ለመዋደድ ይጠቅማል (ኤፌ. 4፥15)።

የቤት ሥራ

❖ እናት ወይም አባት አብረዋችሁ የሚኖሩ ከሆነ ያለ

ቅሬታ በፍቅር አብረዋችሁ እንዲቆዩ ምን ማድረግ

እንደሚገባችሁ የተማራችሁትን ተወያዩ።

❖ ከቤተሰባችሁ ጋር ጤናማ ገደብ ማበጀት

የሚያስፈልግባቸውን ቦታዎች ተወያዩ።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 89

Page 90: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

7 ክፍል

የኢትዮጵያውያን እና የአሜሪካ ባሕል ልዩነቶች

ተግዳሮቶችና የመፍትሔ ሓሳቦች

ዓላማዎች

❖ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የባሕል ልዩነቶች መጠቆም።

❖ ሁለቱ አገራት የሚመሳሰሉበት ነገሮችን ማየት።

❖ ከባሕሎች ሁሉ በላይ የሆነውን የእግዚአብሔርን ሓሳብ

መረዳት።

መግቢያ

የትውልድ መንደራችንን ተሰናብተን (የ)እናት አገራችንን ለቀን፣ ታላቁን አህ

ጉር አቋርጠን፣ ውቂያኖሱን ተሻግረን ከሩቅ የመጣን ሕዝቦች ብንሆንም

ያደግንበት ባሕልና ወግ ግን በውስጣችን ሰርፆ አብሮን በመጓዝ ወደ

አሜሪካን አገር ፈልሷል። አሜሪካ የብዙ ሕዝቦች ጥርቅም እንደ መሆኗ

የብዙ ባሕሎችም ስብስብ ናት። በመሆኑም የራሷ ባሕል (ባሕሎች)

ባሏት በአሜሪካን አገር ባሕላችንን ጠብቀን ከአገሩም ባሕል ጋር ተዛምደን

(ትምህርት ቀስመን) በብልሃት እንዴት መኖር እንደምንችል በዚህ ጥናት

እንወያያለን።

90 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 91: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

የመወያያ ጥያቄዎች

7 ክፍል

❖ አሜሪካን አገር መቼ መጣችሁ?

❖ እስኪ ለአንድ አፍታ አሜሪካን አገር የመጣችሁበትን ወራቶች አስቡ።

❖ በእርግጠኝነት ወደ አእምሮአችሁ ብዙ ትዝታዎች ይመጣሉ።

አስቂኝና አናዳጅ ገጠመኞች አሏችሁ? የተገረማችሁበት

ወይንም ያፈራችሁበት ልምምዶችስ ይኖሯችሁ ይሆን? ግር

የተሰኛችሁበት ግራ ያጋቡዋችሁ ሁኔታዎችስ አሏችሁ?

❖ እስኪ አብሮዋችሁ በተጓዘዉ ባሕል እና በፈለሳችሁበት አገር

ባሕል መካከል ከገጠማችሁ ልዩነቶች ዉስጥ አንዳንዶቹን

አካፍሉን።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 91

Page 92: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

7 ክፍል

❖ እንግዲህ ሁላችንም ከገጠመን የሕይወት ልምምድ

ተካፍለናል። እስኪ ደግሞ በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ

ውይይታችንን በሥፋት እንቀጥል።

✓ ባሕል ስንል ምን ማለታችን ነው?

✓ ባሕል የሚያካትታቸው ወይም የሚዳስሳቸው ነገሮችስ

ምንድን ናቸው?

ኢትዮጵያ በዓለም ታሪክ ውስጥ ጥንታዊ ባሕሎች ካሏቸው አገሮች ጎራ

የምትመደብ ስትሆን በታሪክ እና በባሕሏ በአፍሪካ የቀዳሚነቱን ሚና

ትይዛለች። ባሕላችን የታሪካችን ክፍል እንደ መሆኑ ከትውልድ ወደ

ትውልድ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ካደግንበት ኅብረተሰብ ከአካባቢያችንና

ከታሪካችን የቀሰምነው እና ያቀድነው የአኗኗር ዘይቤ እና ሥልት ነው።

❖ አብሮ ማእድ ቁረስ

❖ እንግዳን መቀበል

❖ ታላላቆቻችንን ማክበር

❖ ቤተሰብን ማገዝ

❖ ሚስጥርን መጠበቅ የመሳሰሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

በአንጻሩ በፍልሰት መኖሪያችን ያደረግናት አሜሪካ ከጥንት ነዋሪዎችዋ በቀር

የጥቂት መቶ ዓመታት ታሪክ ብቻ ያላት የብዙ ሕዝቦች መኖሪያ መድበል

92 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 93: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

7 ክፍል

በመሆን የብዙ ባሕሎች መነሐሪያ አገር ናት። የዚህቸን አገር ታሪክ ጠንቅቆ

ማወቅ ባሕሏንም በቅጡ መረዳት ምርጫችን ብቻ ሳይሆን ግዴታችንም

ጭምር ነው። መኖሪያችን አድርገናታል፤ ልጆቻችንም የሚያድጉባት እና

የሚኖሩባት፣ ወልደው የሚከብሩባት ምድር ሆናለች። አሜሪካ ምንም የብዙ

ባሕሎች ጥርቅም ብትሆንም ጎልቶ የሚታይ የኑሮ ዘይቤ አላት።

❖ ለራስ ብዙ ማሰብ

❖ ለብቻ መብላት

❖ ለብቻ መኖር

❖ ሁሉም እኩል ነው በሚል እሳቤ ለታላላቆች ብዙ የተለየ ክብርን

አለመስጠት

❖ እንግዳን በቀጠሮ ብቻ ማስተናገድ

❖ ሓሳብን በግልጽ መናገር የመሳሰሉት ናቸው።

ከእነዚህ ቀጥለን እነዚህ ሁለት የተለያዩ ታሪኮች እና ባሕሎች ያሏቸው

አገሮች በተለያዩ አሕጉራት ወይም ክፍለ-ዓለማት የሚኖሩ እና ልዩ ልዩ ቋንቋ

የሚናገሩ ሕዝቦች ምን ምን ሊያቀራርባቸው ይችላል?

❖ መሠረታዊ የባሕል ልዩነቶቻቸውስ ምንድን ናቸው?

❖ የእኛ የኢትዮጵያውያኑ ባሕል ለአሜሪካ አኗኗር ምን

ያህልስ አዘጋጅቶን ይሆን?

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 93

Page 94: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

7 ክፍል

❖ ከአሜሪካ ህብረተሰብ ጋር ተቀላቅለን ስንኖር የአኗኗር ሥልታችንስ

ምን መምሰል ይኖርበት ይሆን?

ሃይማኖት፣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና ዓለም-አቀፋዊነት (ግሎባላ

ይዜሽን) የፈጠሯቸዉ የባሕል ቅርርቦሽ።

✓ ኢትዮጵያውያን በታሪካቸውም ሆነ በባሕላቸው ጥልቅ

የሆነ የሃይማኖተኝነት ስሜት ይንጸባረቅባቸዋል። ለረጅም

ዘመንም ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ስትባል ኖራለች።

በተመሳሳይ ሁኔታም ለአዲሲቷ አሜሪካ ምሥረታ ሃይማኖት

ቁልፍ ሚና መጫወቷን ከታሪክ እንማራለን።

የመወያያ ጥያቄዎች

ለእምነት ዋጋ ከሚሰጥ ባሕል መምጣታችንስ በአሜሪካን አገር ላለው

ኑሮአቸን አስተዋጽኦ አድርጎ ይሆን?

❖ ኢትዮጵያና አሜሪካ የቆየ ታሪካዊ ወዳጅነት ያለቸው

አገሮች በመሆናቸው አሜሪካውያን ለኢትዮጵያውያን

አክብሮት አላቸው። ከዚህም የተነሳ የኢትዮጵያ ከፍተኛ

የትምህርት ተቋማት የተስፋፉት በአሜሪካውያን ነበር።

ይህም ለወጣት ኢትዮጵያውያን ወደ አሜሪካን አገር

ለከፍትኛ ትምህርት መምጣትና የባሕል ግንኙነት መፈጠር

ምክንያት ሆኗል።

94 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 95: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

7 ክፍል

❖ ይህ ታሪካዊ ግንኙነት ኢትዮጵያውያንን በአሜሪካን አገር ላለው

ኑሮ አዘጋጅቷቸው ይሆን?

❖ በቀዝቃዛው የዓለም ጦርነት ወቅት አሜሪካ የማስታወቂያና

የሕዝብ ግንኙነት ማእከሎችን በየቦታው ከፍታ ነበር። በአዲስ

አበባ የአሜሪካ ቤተ-መጻሕፍትም የባሕል ማእከል ስለ

ነበር በእነዚህ ማእከሎች በአስተማሪዎችና በሚስዮናውያን

አማካይነት አሜሪካ ራሷን በሚገባ አስተዋውቃለች።

❖ አሜሪካ የዓለምን ገበያ በመቆጣጠር ምርቶቿን በሙሉ በዓለም

ውስጥ አሰራጭታለች። በመሆኑም በተዘዋዋሪ መንገድ በየሲኒማ

ቤቱ፣ በምርቱ እና በሙዚቃው የአሜሪካንን ባሕል ተምረናል።

❖ ስለ አሜሪካን ሕዝብ እና አኗኗር መጠነኛ የሆነ ግንዛቤ

ማግኘታችን በአሜሪካን አገር መጥተን ለምንኖረው ኑሮ

አዘጋጅቶን ይሆን?

❖ አሜሪካ እንደ ተወራልን (በርቀት እንደሳልናት) አግኝተናት

ይሆን?

❖ እዚህ አገር ተወልደው ከሚያድጉት ልጆቻችን ጋር በአንድ ጣሪያ

ሥር ሁለት ባሕሎችን ማስታረቅ የሚቻለው እንዴት ነው?

ዲሞክራሲ፣ ፓለቲካና የኢኮኖሚ ፍልስፍና ልዩነቶች የፈጠሯቸው የባሕል

መናጋቶች ባሕል ከታሪካችን ከምንኖርበት መልክዓ-ምድር እንዲሁም

ከአብራኩ ከተገኘንበት ህብረተሰብ ጋር የተዛመደ ነው። ባሕል የመንፈሳዊ

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 95

Page 96: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

7 ክፍል

ሕይወታችንን፣ ፍልስፍናችንን፣ ስለ ዓለም ያለንን አስተያየት እና ስለ ማኅበ

ራዊ ኑሮ ያለንን ግንዛቤ ሁሉ የሚያጠቃልል ነው። ባሕል የማይነካው የኑሮ

ዘርፍ የለም። እንግዲህ ከልጅነት ጀምሮ ያደግንበትን ይህንኑ ባሕላችንን

ይዘን ነው ወደ አገረ-አሜሪካ የፈለስ ነው።

❖ ወደ አሜሪካን አገር በመጣችሁበት የመጀመሪያ

ዓመታት የገጠማችሁ የባሕል ግጭቶች (Cultural

shock) ምን ምን ነበሩ?

ልዩ ልዩ የባሕል መናጋቶች (ነውጦች) 1. በአሜሪካን ለረጅም ዓመታት የሰፈነው ዲሞክራሲያዊ ባሕል

ለኢትዮጵያውያን እንግዳ ነው።

❖ የኢትዮጵያውያንን ባሕል በጥልቀት የቀረጸው ፊዊዳላዊ

ሥርዓት ከዚያም ወታደራዊ አምባገነንት ነበር። ይህ

በኢትዮጵያውያን ሥነ-ልቦና ላይ የፈጠረው ተጽዕኖ

ቀላል አልነበረም። ይህንን ሁኔታ በአሜሪካን አገር

ከዳበረው የነጻነት ባሕል ጋር እንዴት ታነጻጽሩታላችሁ?

2. የአሜሪካ ህብረተሰብ ለሰዓት (ለጊዜ) የተለየ አመለካከት ያለው ሲሆን

ኑሮውንም በዕቅድና በጥድፊያ የሚመራ ነዉ።

❖ ኢትዮጵያውያን በባሕላችን ከጊዜ ይልቅ ለሰው ቅድሚያን

96 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 97: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

7 ክፍል

ይሰጣሉ፤ ይህንንም በማድረጋቸው አክብሮታቸውን ይገልጣሉ።

አሜሪካውያን ደግሞ ለጊዜ ቅድሚያን በመስጠት ያላቸውን

አክብሮት ያንጸባርቃሉ። ይህ ተቃራኒ ተሞክሮ የባሕል

መናጋትን ይፈጥራል። ይህንን እንዴት እናዛምደዋለን?

3. የአሜሪካ ህብረተሰብ ግለኝነት-ተኮር እና በቃላት የመናገር ልምድ

(low context culture) ሲሆን ኢትዮጵያውያን ግን ለማኅበራዊ ኑሮ

ቅድሚያን ይሰጣሉ (high context culture)።

❖ የአሜሪካ ህብረተሰብ ቅድሚያ የሚሰጠው የግል

ኑሮውን ለማስተካከል ነው።

❖ የማኅበራዊ ኑሮም የሚታሰበው የግል ኑሮ ከተስተካከለ

በኋላ ብቻ ነው። ኢትዮጵያውያኑ ግን ለማኅበራዊ ኑሮ

ቅድሚያን ይሰጣሉ። በዚህ ምክንያት ለልዩ ልዩ ፈተና

ይጋበዛሉ። ይሉኝታ በጣም የሚያጠቃው ህብረተሰብ

ስለሆነ ከሌሎች እነርሱ እንደሚያስቡት ስለሚጠብቅ

ብዙ አላስፈላጊ ግጭቶችንም ያስነሳል። ይህንን እንዴት

ታዩታላችሁ?

4. የአሜሪካን ህብረተሰብ ኑሮውን በዕቅድ የመምራት እና በአቅሙ ልክ

የመኖር ባሕል አዳብሯል። ኢትዮጵያውያኑ ግን በዕቅድ የመኖር ባሕል

አላዳበሩም እንዲሁም በውስጣቸው ያለውን የማንነት ጥያቄ ከአቅም

በላይ በሆነ አኗኗር ዝም ለማሰኘት ሲጥሩ ይስተዋላል። ይህንን እንዴት

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 97

Page 98: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

7 ክፍል

ታዩታላችሁ? በዓላማ እና በጥበብ መኖር ለአንድ ቤተሰብ በጣም

አስፈላጊ የሕይወት መርህ ነው።

እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው

ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ።

ኤፌ. 5፥15

እናንተ የምድር ጨዉ ናችሁ ... እናንተ የዓለም ብርሃን

ናችሁ። ማቴ. 5፥13-14

ሰዉ ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ቢያጎድል ምን

ይጠቅመዋል? ማቴ. 16፥26

ሕይወት ትርጉም፣ ዓላማ እና ግብ አለው። ይህንን የሕይወት ትርጉም፣

ዓላማና ግብ ከኢትዮጵያዊም ሆነ ከአሜሪካዊ ባሕሎች ዉስጥ ልናገኝ

አንችልም። እነዚህ የሕይወት እሴቶች መቀዳት ያለባቸው የሕይወታችን

ባለቤት ከሆነው አምላክ ብቻ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስን የሕይወታችን ጌታ

ማድረግ ማለት ከሕይወት ትርጉም፣ ዓላማና ግብ ጋር መገናኘት ማለት

ነው። ክርስቲያን ሆኖ ያለ ዓላማ መኖር አሳዛኝ እና አደገኛ ልምምድ ነው።

98 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 99: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

7 ክፍል

ማጠቃለያ

በማጠቃለያም እዚህ አገር ተወልደው በሚያድጉ ልጆች እና እዚያ አድገው

በመጡ መካከል የአስተሳሰብ ልዩነቶች አሉ። በተለይ ይህ ሁኔታ በአንድ

ቤት ውስጥ ሲኖሩ አለመግባባትን በቤተሰብ ውስጥ ሊያመጣ ይችላል።

ስለዚህ እንደ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ቃል የሚለንን በመታዘዝ እና

በመኖር የእግዚአብሔር ባሕል በሆነው በፍቅር እና በትሕትና አብረን

እንኑር።

እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ

እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ ሕግም ነቢያትም

ይህ ነውና። ማቴ. 7፥12

የቤት ሥራ

1. በሕይወታችሁ ቅድሚያ የሰጣችሁት እና ጎልቶ የሚታየው

ያደጋችሁበት ባሕል፣ የፈለስንበት ባሕል ወይስ ዳግም ልደት

ያገኘንበት የሕይወት ሥርዓት ነው?

2. እንደ ክርስቲያን አዲስ የኑሮ ሥልት፣ አዲስ የኑሮ ፍልስፍና

መገንባት ይጠበቅብናል። ይህንን ስናደርግ ብቻ ነው የምድር

ጨው እና የዓለም ብርሃን ሆነን መገኘት የምንችለው። ይህንን

ባናደርግ የሚጠብቀን ምን ይሆን?

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 99

Page 100: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

7 ክፍል

3. የኑሮ ጥድፊያና ውጥረት በሞላባት በአሜሪካን አገር ኑሮአችንን

በተረጋጋ መንፈስ እና በሰከነ አእምሮ እንዴት መምራት ይቻላል?

4. ለልጆቻችን ወይም ለተተኪው ትውልድ የምናስተላልፈው ሃብት

ወይም ባሕል ምን ይሆን?

100 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 101: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

እንደ ባልና ሚስት አብሮ ማገልገል

8 ክፍል

ዓላማዎች ❖ እግዚአብሔር ለባልና ለሚስት አንድነት ያለውን ሥፍራ

ለመመልከት፣

❖ የባልና የሚስት አብሮ የማገልገል ኀላፊነት ለማመልከት ነው፡፡

መግቢያ

በቀጥታ ወደ ባልና ሚስት አብሮ የማገልገል አስፈላጊነት ከመሄዳችን በፊት

እግዚአብሔር ለሰዎች ልጆች፣ እንዲሁም ለባልና ለሚስት ያለውን ትልቁን

ዓላማ ከማየት እንጀምራለን። ትክክለኛ ኑሮ የሚጀምረው ከትክክለኛ

መረዳት ነው። ይሄ አባባል ብቻ ሳይሆን ትክክለኛ ነገር ነው። የአንድ

ግለሰብ፣ የአንድ ቤተሰብ ወይም የአንድ ኅብረተሰብ ኑሮ የሚንጸባረቀው

በግንዛቤው ነው። ባልና ሚስት የእግዚአብሔርን ሓሳብ አውቀው ወደዚያ

ለማደግ ቢኖሩ ዛሬ ከሚታየው ብዙ ችግር ይጠበቃሉ። እግዚአብሔር

የሰው ልጆች ፈጣሪ፣ የትዳርም መሥራች እርሱ ስለ ሆነ ለባልና ሚስት

እግዚአብሔር ያለውን ዓላማ ከማየት መጀመሩ ጠቃሚ ነው። ይሄ ጠቃሚ

የሚሆንበት ምክንያት ነገሮች የተፈጠሩበት ወይም የተሰሩበት ዓላማ ላይ

መዋላቸውንና፣ ከዓላማው ወጣ ማለታቸውን የምናውቀው የመጀመሪያውን

መነሻቸውን ስናውቅ ነው። እኛ እንደ ክርስቲያን ቤተሰብ መጽሐፍ ቅዱስ

የእግዚአብሔር ቃል ነው ብለን እናምናለን። መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 101

Page 102: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

8 ክፍል

ቃል ነው ብለን ካመንን የሰው ልጆች እንዲሁም የትዳር የመጀመሪያው

ዓላማ ለማወቅ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ መሄድ ይኖርብናል። ዓላማ የሚለውን

ሓሳብ ለመግለጽ የስፖርት ምሳሌ እንጠቀም።

በአገራችን የሚታወቀው የስፖርት ጨዋታ የእግር ኳስ ነው። በዚህ በአሜ

ሪካን አገር ደግሞ “Foot Ball” ነው። ሁለቱንም ጨዋታዎች ሌሎችንም

ስፖርቶች ስናይ ብዙ የሚያመሳስላቸው ነገሮች አሉ። ሁለቱም አስራ አንድ

ተጫዋቾች በአንድ ጊዜ ሜዳ ላይ መኖራቸው ነው። እንዲሁም አጥቂዎች

መድረስ የሚፈልጉበት ቦታ በእግር ኳስ የግብ ክልል ወይም በ Foot Ball

ደግሞ End zone አለ። ተከላካይ ከሆኑ የተቃራኒው ቡድኖች ወደዚያ

እንዳይደርሱባቸው ይከላከላሉ። አጥቂዎች ከሆኑ ደግሞ ወደ ተቃራኒው

ቡድን የግብ ሥፍራ የግብ ክልል ወይንም (End zone) ለመድረስ

ይደክማሉ። ይሄ የስፖርት ምሳሌ ከትዳራችን ጋር የሚያመሳስለው ጎን

አለው። ያለ ግብ ጨዋታው ጨዋታ እንደማይመስል ሁሉ ያለ ዓላማ ደግሞ

ትዳር ሊደራ አይችልም።

የመግቢያ ጥያቄዎች

1. ተጫዋቾች ከወደቁ በኋላ ተነስተው እንዲቀጥሉ የሚያደርጋቸው

ነገር ምንድን ነው?

2. ግብ (ጎል) የሌለው ጨዋታ ከትዳር ሕይወት ጋር ግንኙነት

አለው ብለው ያስባሉ?

102 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 103: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

8 ክፍል

ትዳርንም እንዲሁ እግዚአብሔር ሲመሰርተው በዓላማ ነው። ዓላማው

ከገባን ወደ ግቡ ለመድረስ ኀላፊነታችንን ለመወጣት እንጥራለን። ወድቀንም

ቢሆን ተነስተን ለመሮጥ አቅም ይኖረናል።

የባልና ሚስት አንድነት

“እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳ

ሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥

እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚን

ቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ። እግዚአብሔርም ሰውን

በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤

ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። እግዚአብሔርም ባረካ

ቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም

ሙሉአት፥ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች

በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።”

(ዘፍ. 1፥26-28)

እግዚአብሔር መጀመሪያ አዳምን በመቀጠልም ሔዋንን እንደ ፈጠራት

እንመለከታለን። የእግዚአብሔርን ቃል ስንመለከት እግዚአብሔር ወንድና

ሴት አድርጎ ፈጠራቸው የሚለው ሓሳብ በአንድ መልኩ የመጀመሪያ ባልና

ሚስትን (አንድነት) ሲያመለክት በሌላ በኩል አዳምና ሔዋን የሰዎች ልጆች

ዘር የመጀመሪያዎቹ ስለ ሆኑ ምድርን ይግዙ በማለት ኀላፊነታቸውን

ያመለክታል።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

103

Page 104: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

8 ክፍል

በዚህ ክፍል “እግዚአብሔር ሰውን በመልኩ እንደ ምሳሌው ፈጠረው”

ይልና “ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው” ይላል። ለምን “ፈጠረው” ደግሞም

“ፈጠራቸው” አለ? በአማርኛ ፈጠረው እንዲሁም ፈጠራቸው የሚል

የተደጋገመ ቃል ቢመስልም በዕብራይስጥ የመጀመሪያው ፈጠረው (bara)

ሲሆን ሁለተኛው ፈጠራቸው የሚለው (asah) የሚል የተለየ ቃል ነው።

(bara) እግዚአብሔር ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ አንድ ነገር ሲፈጥር ማለት

ሲሆን እግዚአብሔር አዳምን ከአፈር ካበጀው (asah) በኋላ የሕይወትን

እስትንፋስ እፍ (bara) ሲልበት የአዳም ብቻ ሳይሆን የሔዋንንም ከዚያ

ሕይወት መካፈል ያሳያል።

ይህንን ሓሳብ የበለጠ ለመረዳት የሰው አካል የተሰራው ከአፈር (asah)

ሲሆን እግዚአብሔር የሰውን መንፈስ ያለ ምንም ቀድሞ የነበረ ነገር በራሱ

እስትንፋስ (bara) ፈጠረው። በአካልና በስሜት ወንድና ሴት የተለያየን

ብንሆንም ሕያው የሆንነው በአንዱ በእግዚአብሔር መንፈስ ስለሆነ

የእግዚአብሔር መልክና ምሳሌዎች ነን። ስለዚህም ነው አዳምን በፈጠረ

ቀን ፈጠራቸው ያለው። ሌላው የባልና የሚስትን አንድነት የሚያጸናው

የተጠሩበት ስም ነው። በአማርኛ “ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል”

የሚለው ርቀት ያለው ቢያስመስልም በዕብራይስጥ ከወንድ (Eshah)

ተገኝታለችና ሴት (Esah) ትባል ሲል በእንግሊዘኛው ደግሞ ከወንድ

(Man) ተገኝታለችና ሴት (woman) ትባል የሚሉት እንዴት አንድነትና

ቅርበት እንዳላቸው ያሳዩናል። ስለዚህ ባልና ሚስት ማለት በእግዚአብሔር

104 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 105: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

8 ክፍል

መልክና አምሳል የተፈጠሩ እንደ ሆኑ በቀላሉ ማየት እንችላለን። ይኸው

አንዱ የእግዚአብሔር መንፈስ አንድ እንዳደረጋቸው መመልከት ችለናል።

በመቀጠል የአገልግሎት ኀላፊነታቸውን እንመልከት።

የባልና የሚስት አገልግሎት

እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥

ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፤ የባሕርን

ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀ

ሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው። ዘፍ. 1፥28

ይህ የመግዛት፣ በምድር ላይ የሚሆነው ነገር ለእግዚአብሔር እንደ ራሴ ሆኖ

የማስተዳደር ኀላፊነት ለወንድ (ለባል) ብቻ ሳይሆን ለወንድና ለሴት (ለባልና

ለሚስት)፣ ለአዳም እና ለሔዋን እንደ ተሰጠ ማየት እንችላለን። ይሄ መረዳት

ወደዚህ እውነት ያመጣናል፤ ይህን አለመረዳት ደግሞ ኀላፈነቱ የአንዱ ወገን

ብቻ እንደ ሆነ እንድናይ ያደርገናል። ወይም ከባሰ ደግሞ ወንዱም ሆነ ሴቷ

ኀላፊነት በጎደለው ሁኔታ ውስጥ እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል። ታድያ ለምን

አብረው አያገለግሉም?

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 105

Page 106: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

8 ክፍል

ተግዳሮቶች (Challenges)

1. አለማወቅ ትልቅ ችግር ነው። ከመቶ ዘጠና እጅ የሚጠፋው ጥፋት የሚመጣው ከአለማወቅ ነው ይባላል።

አውቀንም ሆነ ሳናውቅ ብናጠፋ ጥፋት ያው ጥፋት ነው። እንደዚሁ በትዳር

ውስጥ አንዳችን በአንዳችን ውስጥ ያለውን ውበት፣ የአገልግሎት ጸጋ

ባለማየታችን የተነሳ እኛም ሆነ በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ተጠቃሚ መሆን

አልቻሉም። ከዚህ የሚበልጠው ደግሞ እግዚአብሔር እኛን የፈጠረበትን

ዓላማ አውቆ ለተፈጠርንበት ዓላማ አለመኖር የኑሮን ጣዕም ማጣት ነው።

2. በአንድነት ላይ ሳይሆን በልዮነት ላይ ማተኮራችን ነው።

በእግዚአብሔር መልክና አምሳል መፈጠራችን እግዚአብሔር ለማገልገል

የሰጠን ማንነት፣ ብቃት፣ ችሎታ ላይ ማተኮር እየቻልን ብዙ ጊዜ ትኩረት

የምናደርገው ጥቃቅን ልዮነቶች ላይ መሆኑ ነው። ለምሳሌ የስጦታዎቻችን፣

የአመለካከት እና የስሜት (personality) ልዮነቶች ላይ ማተኮር።

ሰው ፓስታ የሚበላው በሁለት ማንኪያ ወይም በሁለት ሹካ አይደለም፤

ለምን ቢባል ሁለቱ ተመሳሳይ ናቸው። ግን በአንድ ማንኪያ እና በአንድ

ሹካ መብላት አዋጪ ነው። ለምን ቢባል ሁለቱ በመጠኑም ቢሆን ልዮነት

አላቸው፤ እነዚያን ልዩነቶች ስናቀናጅ ግን ሥራውን ያቀላጥፍልናል።

106 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 107: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

8 ክፍል

ባልና ሚስት ይደጋገፋሉ (complement) ይደራረጋሉ ሲባል ተመሳሳይ

ናቸው ሳይሆን የአንዱ ልዩ መሆን የሌላውን ጉድለት ይሸፍናል ማለት ነው።

3. የአገልግሎት መስክን አለመረዳት።

ብዙ ጊዜ አገልግሎት የምንለው በዘልማድ መስበክ፣ መዘመር ወይም

የመድረክ አገልግሎት ከመሰለን እንደ ባልና ሚስት ተቀናጅቶ ማገልገል

ይቸግረን ይሆናል። ሆኖም አገልግሎት ከዚያ የሰፋና የጠለቀ መሆኑን

ስንረዳ መቀናጀቱ ይቀላል። መጽሐፍ ቅዱስ አገልግሎት ልዩ ልዩ እንደ ሆነ

ይነግረናል።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 107

Page 108: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

8 ክፍል

“የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው መንፈስ ግን አንድ ነው፤

አገልግሎትም ልዩ ልዩ ነው ጌታም አንድ ነው፤ አሠራርም

ልዩ ልዩ ነው፥ ሁሉን በሁሉ የሚያደርግ እግዚአብሔር ግን

አንድ ነው።” (1ቆሮ. 12፥4-6)

እግዚአብሔርም በቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀ

ድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን ፥ ሦስተኛም

አስተማሪዎችን፥ ቀጥሎም ተአምራት ማድረግን፥ ቀጥ

ሎም የመፈወስን ስጦታ፥ ርዳታንም፥ አገዛዝንም፥ የልዩ

ልዩ ዓይነት ልሳኖችንም አድርጎአል። ሁሉ ሐዋርያት

ናቸውን? ሁሉስ ነቢያት ናቸውን? ሁሉስ አስተማሪዎች

ናቸውን? ሁሉስ ተአምራትን ይሠራሉን? ሁሉስ የመፈወስ

ስጦታ አላቸውን? ሁሉስ በልሳኖች ይናገራሉን? ሁሉስ

ይተረጉማሉን? ነገር ግን የሚበልጠውን የጸጋ ስጦታ

በብርቱ ፈልጉ። ደግሞም ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ

አሳያችኋለሁ። 1ቆሮ. 12፥28-31

አገልግሎታችን በቤታችን (ትዳራችንና ልጆቻችን)፣ በቤተ ክርስቲያንና

በማኅበረሰብ እንደ ሆነ አንዘንጋ።

4. ከእግዚአብሔር ባሕል ይልቅ የህብረተሰብን ባሕል ማስቀደም።

አንዳንድ ባሕል ሴቶች በጸጋቸው እንዳያገለግሉ ተጽእኖ ያደርጋል።

ሌላው ህብረተሰብ ደግሞ ወንዶችም ሴቶችም ራሳቸውን እንዲገልጹ፣

108 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 109: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

8 ክፍል

በመክሊታቸው እንዲነግዱ ያደፋፍራል። ካልተጠነቀቅን በስተቀር ባሕልና

ወግ በቤተ ክርስቲያን ላይ ተጽእኖ ሊፈጥር ይችላል። የእግዚአብሔርን ቃል

ለማይቃረን ባሕል ሥፍራ እየሰጠን ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ባሕላችን

ሲጋጭ የእግዚአብሔርን ቃል በመታዘዝና በማስቀደም ሴቶችንም

ወንዶችንም ለአገልግሎት ማደፋፈር ይጠበቅብናል።

ከመጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔርን አብሮ ያገለገሉ ቤተሰብ ምሳሌ

የአቂላ እና ጵርስቅላ

በሐዋርያት ሥራ 18፥1-4 ባለው ክፍል ላይ እንደምንመለከተው አቂላ እና

ጵርስቅላ ከሮም ተሰደው ወደ ቆሮንቶስ ከተማ የመጡ አይሁድ ክርስቲያኖች

ሲሆኑ በሙያቸውም ልክ እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ በድንኳን መሥፋት

የሚተዳደሩ ነበሩ። ይህንንም ትንሽ የሚመስል የሙያ አጋጣሚ በመጠቀም

ጳውሎስን በአገልግሎቱ ይደግፉት ነበር። ስለ እነርሱም ሲመሰክር በሮሜ

16፥3 ላይ “በክርስቶስ አብረውኝ ለሚሠሩ” ሲል በዚሁ ምእራፍ ቁጥር 4

ላይ ደግሞ “ነፍሳቸውን ስለ ነፍሴ ለሞት አቀረቡ” ይላል። ለዚህም ነው

ጳውሎስ በሐዋርያት ሥራ 18፥18-19 ወደ ኤፌሶን በሄደበት ጊዜ ይዟቸው

ሊጓዝ የወደደው።

እንደዚሁም በሐዋርያት ሥራ 18፥24-26 ላይ እንደምናየው አጵሎስ የተባለ

በወገኑም የእስክንድርያ የሆነ ሰው የዮሐንስን ጥምቀት ብቻ አውቆ በቅንዓት

ስለ ኢየሱስ ሲናገርና ሲያስተምር በሰሙት ጊዜ ወደ እነርሱ ወስደው

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 109

Page 110: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

8 ክፍል

“የእግዚአብሔርን መንገድ ከፊት ይልቅ በትክክል ገለጡለት ይላል።”

ወደ እነርሱ ወስደው የሚለው ቃል ሓሳብ ከአንድ ጊዜ ያለፈን ግንኙነት እና

ትጋትን የሚያሳይ ነው። በ1ኛ ቆሮንቶስ 3፥6 ላይ እንደምናየው ጳውሎስ

“እኔ ተከልኩ አጵሎስ አጠጣ” ብሎ ስለ አገልግሎቱ ጥራት ሲመሰክርለት

የእነዚህን ሰዎች አገልግሎት ፍሬ እናያለን።

ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮንቶስ 16፥19 በኤፌሶን ሆኖ ለቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን

በጻፈው ደብዳቤ ላይ “አቂላና ጵርስቅላ በቤታቸው ካለች ቤተ ክርስቲያን

ጋር በጌታ እጅግ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል“ ሲል በሮሜ 16፥5 ላይ ደግሞ

“በቤታቸውም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልኝ” ብሎ ሲጽፍ

እንመለከታለን። ከዚህ የምንረዳው አቂላ እና ጵርስቅላ በሄዱበት ከተማ

ሁሉ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን በአንድነት እንደ ጥንድ ሆነው

ለማገልገል ቤታቸውን የከፈቱ እንደ ነበረ ነው። አቂላ እና ጵርስቅላ በአዲስ

ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ ለስድስት ጊዜ ያህል ስማቸው ተጠቅሷል፤ ነገር

ግን በተጠቀሱባቸው ቦታዎች ሁሉ በአንድነት እንደ ጥንድ እንጂ በተናጠል

ሲጠሩ አናይም።

በመካከላችን ያሉ ምሳሌዎች

አቂላ እና ጵርስቅላን ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ለምሳሌ ተመልክተናል ነገር ግን

በዚህም ዘመን በተለያየ ቦታ እና ጊዜ እንደ ጥንድ እና እንደ ቤተሰብ ሆነው

ጌታን የሚያገለግሉ ሰዎች አሉ።

110 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 111: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

8 ክፍል

ለምሳሌነት በቤተ ክርስቲያናችን ካሉት አገልጋዮች መካከል መጋቢ ስታን

(Pastor Stan) እና ባለቤቱ ርኔ (Mrs. Renee) ሊጠቀሱ ይችላሉ። እነዚህ

አገልጋዮቻችን ምንም እንኳ በዘርና በቀለም እኛን ባይመስሉም ከሃያ

ዓመታት በላይ በቤተ ክርስቲያናችን የሕጻናት እና የወጣቶች አገልግሎትን

እንደ ጥንድ እና እንደ ቤተሰብ ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ። ለዚህም አገልግሎት

ውጤታማነት የብዙዎቻችን ልጆች ሕይወት ምስክር ነው።

የመግቢያ ጥያቄዎች

1. የዛሬው ጥናት እንደ ጥንድ በትዳራችን ውስጥ እግዚአብሔርንና

ሰዎችን ለማገልገል ምን ያህል ፍላጎት እንዳሳደረባችሁ ለቡድኑ

ያካፍሉ።

2. እግዚአብሔርንና ሰዎችን አንደ ባልና ሚስት በአንድነት

የማገልገል ጥቅም ምንድን ነው?

ማጠቃለያ

እግዚአብሔር የሚሠራው በአንድነት ውስጥ ነው። ባልና ሚስት በዓላማ

አብረው ቆመው ቢጸልዩ፣ ቢያገለግሉ እግዚአብሔር የበለጠ አብሮአቸው

ይሠራል። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲህ የሚል ቃል አለ። “እርሱ

አምላካቸው ካልሸጣቸው፥ እግዚአብሔርም አሳልፎ ካልሰጣቸው፥

አንድ ሰው እንዴት ሺህን ያሳድድ ነበር? ሁለቱሳ እንዴት አሥሩን ሺህ

ያሸሹ ነበር? (ዘዳ 32፥30)። ይህ ጥቅስ የባልና ሚስት የጋራ አገልግሎት

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

111

Page 112: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

8 ክፍል

ውጤታማነት ይጠቁመናል። እንደ ባልና ሚስት አብሮ ማገልገል ትልቅ

ውጤት እንዳለውም ያሳየናል።

የቤት ሥራ

❖ እንደ ባልና ሚስት የአገልግሎት ጸጋችሁን ለመለየት፣

ለማሳደግ ብሎም አብራችሁ ለማገልገል ተነጋገሩ።

❖ እንደ አስፈላጊነቱ አገልጋዮቻችሁን በዚህ ነገር

እንዲረዱአችሁ አነጋግሩ።

112 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 113: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

ጊዜ አጠቃቀም (Time management)

9 ክፍል

ዓላማ

የሰው ሕይወት በምድር ላይ በጊዜ የታጠረ ወይም የተወሰነ ነው። ሰው

በምድር ላይ ሊኖረው የሚችለው ዘመን በትናንሽ የሰዓትና የደቂቃ

ክፍልፋዮች ወይም ክልሎች ውስጥ የተወሰነ ነው። የዚህ ጥናት ዋነኛ

ዓላማም ጊዜን በማወቅ ውጤታማ የሆነ የጊዜ አጠቃቀም ሥልት እና ዘዴ

እንድናጎለብት ማሳየት ነው።

መግቢያ

በዚህ ዘመን ውስጥ ሰው ደግሞ ሊያደርገው የሚገባው፣ የሚፈልገው፣

የሚጠበቅበት ብዙ ነገሮች አሉ። ስለዚህ ሰው ጊዜንና ነገሮችን በሕይወት

አመጣጥኖ መሄድ ይኖርበታል። እነዚህ ሁለቱ ማለትም ጊዜና ሰው

በሕይወት ማድረግ ያለበት፣ የሚፈልገው፣ የሚጠቀምበት ሳይመጣጠን

ሲቀር ሕይወት የተወጠረ (Stresseful) እና እርካታ የሌለበት ይሆናል።

ስለዚህ ይህ ጥናት እነዚህን ሓሳቦች በመዳሰስ የተመጠነ ኑሮ እና እርካታ

ያለበት ሕይወት ለመኖር ጊዜንና ነገሮችን የምናመጣጥንበትን መንገድ

ይጠቁማል።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 113

Page 114: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

9 ክፍል

ጊዜ (Time) ምንድን ነው?

ጊዜ ውድ ነው።

የጊዜን ትርጉም ከመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ የመለኮት ሓሳቦች ጋር

አስተሳስሮ ማየቱ በቀላሉ ለመረዳት ያግዛል። ጊዜን መጽሐፍ ቅዱስ ከሰው

ልጅ ሕይወት ጋር በማያያዝ በተደጋጋሚ ተጠቅሷል።

እግዚአብሔርም አለ ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ብርሃ

ናትን በሰማይ ጠፈር ይሁኑ፤ ለምልክቶች ለዘመኖች

ለዕለታት ለዓመታትም ይሁኑ። ዘፍ. 1፥14

ሺህ ዓመት በፊትህ እንዳለፈች እንደ ትናንት ቀን፣ እንደ

ሌሊትም ትጋት ነውና። መዝ. 90፥4

ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ፣ አም

ላክሽም ክብርሽ ይሆናልና ፀሐይ በቀን ብርሃን አይሆን

ልሽም፤ የጨረቃም ብርሃን በሌሊት አይበራልሽም።

እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ ይሆናልና የልቅሶሽም

ወራት ታልቃለችና ፀሐይሽ ከዚያ በኋላ አትጠልቅም

ጨረቃሽም አይቋረጥም። ኢሳ. 60፥19-20

ጊዜን የፈጠረው እግዚአብሔር እንደሆነና ይህም ደግሞ በጊዜ ላይ የመወሰን

114 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 115: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

9 ክፍል

ሙሉ ችሎታ ያለው እርሱ እንደ ሆነ እንረዳለን። የሰው ልጅም ደግሞ በጊዜ

የተገደበ ነው። እግዚአብሔር የሰው ልጅን ሲፈጥር በዓላማ እና ለዓላማ እንደ

ሆነ ማወቅ እንደዚሁም ጊዜ የሰው ልጅ ዓላማውን ለመፈጸም የተሰጠውን

መክሊት የሚፈጽምበት አንዱ መለኮታዊ ሃብት ወይም ስጦታ ነው።

ከላይ የተቀመጡትን ጥቅሶች ይዘት ስንመረምር በጥቅሉ የጊዜ ባለቤትና

ፈጣሪ እግዚአብሔር እንደሆነ፣ ጊዜ እግዚአብሔር የፈጠረው የዘመን

መለኪያ እንደሆነ እና የሰው ልጅ በጊዜ የተወሰነ ማለትም የሚወለድ፣

የሚያድግ እና የሚሞት ፍጥረት እንደ ሆነ እንገነዘባለን።

ስለዚህ የሰው ልጅ በጊዜ ሂደት ውስጥ የሚሠራበት ዘመን አለው። ሰባኪው

በመክብብ መጽሐፍ በተደጋጋሚ “ለሁሉም ጊዜ አለው” በማለት እንደ

ተናገረው ሥራ ካለ የተሠራበት ዘመን እንዳለ እና ሊኖርም እንደሚገባ

ያስረዳል። ጊዜ ደግሞ ካለፈ የማይመለስ ስጦታ መሆኑን በሚገባ ማወቅ

እና በንቃት ጊዜን መጠቀም የክርስቲያን ሰው እና ቤተሰብ ኀላፊነት ሊሆን

ይገባል።

የጊዜ አጠቃቀምን ማወቅ

ጊዜ በሕይወታችን ላይ የሚያስከትለው ተጽእኖ ስላለ በጊዜያችን የምናደ

ርገው ነገር ወይም ጊዜያችንን በየቀኑ እንዴት እንደ ተጠቀምን ማወቅ

አለብን። የጊዜ አጠቃቀም እውቀት ለክርስቲያን ሕይወት ተፈላጊ ነው። ጊዜ

እንዳይባክን መለወጥ ያለበትን በመለወጥ እንደዚሁም መስተካከል

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 115

Page 116: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

9 ክፍል

ያለበትን የጊዜ አጠቃቀም ልማድ ለውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ያግዛል።

በአገራችን ሁኔታ የጊዜ አጠቃቅም እና ለጊዜ ያለን ግንዛቤ አብዛኛውን

ሊያስማማ በሚችልበት ደረጃ ችግር ያለበት ነው። በዚህም ምክንያት እንደ

ግለሰብም ሆነ እንደ ማህበረሰብ የጊዜ አጠቃቀም ብቃታችንን ማሻሻል

ኀላፊነት አለብን። ይህንን ለውጥ ለማምጣት ደግሞ ስለጊዜ በጥልቀት

በመረዳት፣ መረዳታችንም ደግሞ ስለጊዜ ያለንን ውስጣዊ አመለካከት

እንዲቀይረው በማድረግ በጊዜ ሂደት ውስጥ ድርጊታችን በውጤት የታቀፈ

ለውጥ ማምጣት ይቻላል።

የመወያያ ጥያቄዎች

1. ጊዜ ለአንተ ምንድን ነው? እንዴት ትረዳዋለህ?

2. ጊዜን መቆጣጠር እንችላለን? ተወያዩ ።

3. ጊዜን ለመጠቀም ማድረግ ያለብንን ወይም መውሰድ ያለብንን

እርምጃ በመዘርዘር ተወያያዩ።

4. ጊዜን እንቆጥብ፣ ጊዜን እንቆጣጠር ስንል ምን ማለታችን ነው?

5. ጊዜን እንዴት ማትረፍ ይቻላል? ጊዜስ እንዴት

ይባክናል? በዝርዝር ተወያዩ።

ጊዜን መቆጣጠር እንችልም። መቆጣጠር የምንችለው በጊዜ ውስጥ

የምናደርጋቸውን ድርጊቶች ነው። በቀን ወይም በተሰጠን ዘመን ውስጥ

116 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 117: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

9 ክፍል

ብዙ ማድረግ የምንፈልጋቸው ነገሮች አሉን። የሚበቃ ጊዜ ግን የለንም።

ስለዚህ መፍትሔው የምንሰራቸውን ሥራዎች ወይም ድርጊቶች መቆጣጠር

ነው። ድርጊታችንን ስንቆጣጠር ደግሞ ጊዜያችንን እንቆጣጠራለን።

ለትምህርት የቀረበ ታሪክ

አልማዝና ከበደ እሁድ ጠዋት ቡና ለመጠጣት ስታርባክስ ገቡ። ቡና

ጠጥተው ተጫውተው ወደ ቤተ ክርስቲያን መጡ። ቤተ ክርስቲያን በር

ላይ እንደደረሱ ከበደ ስታርባክስ ጠረጴዛ ላይ ስልኩን እንደረሳው ትዝ

አለው። ስልኩን ለማምጣት ወደ ስታርባክስ በፍጥነት ተመልሶ ስልኩን

አግኝቶ ሲመለስ አልማዝ ፕሮግራም እየተካፈለች ነው።

ከበደ የረሳውን ስልክ ማምጣት ችሏል። ግን ያሳለፈውን ጊዜ መመለስ

አልቻለም። ለአምልኮ የተቀጠረው ጊዜ አልፏል። ስለዚህ የኛ ዘመን ሆነ

ጊዜያችን እንዲሁ ነው። ብዙ ነገር መልሰን እናገኝ ይሆናል ጊዜያችን ግን

አንዴ ካለፈ አይመለስም።

በየቀኑ እያንዳንዳችን በሕይወታችን በአስቸኳይ እና በአስፈላጊ ነገሮች

የተሞላ ነው። ስለዚህ በየቀኑ የምንወስነው ውሳኔ ከሁለት እንዱ ላይ

የተመረኮዘ ነው። የቀኑ ሕይወታችንም ወይም ውሎአችን ስንመለከት ያደረ

ግነው የትኛውን ነው? አስቸኳይ የሆነውን ወይስ አስፈላጊ የሆነውን?

እንወያይበት።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 117

Page 118: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

9 ክፍል

የመወያያ ጥያቄዎች

1. ዛሬ ወይም በዚህ ሳምንት ያለህን ውሎ ተመልክተህ ሰዓቱ ወይም

ቀኑ ያለፈው የትኛውን በማድረግ ነው? ልምዳችሁን ተከፋፈሉ።

2. ከአቅጣጫ (Compass) እና ከጊዜ (Clock/Time) የቱን

ትመርጣለህ? ለምን?

ከዚህ ውይይት እንደምንመለከተው መጀመሪያ የሚያስፈልገው (Com-

pass) መሆኑን ነው። አንድ ሰው ጊዜን ከመቆጣጠሩ በፊት ወይም ጊዜውን

ለመቆጣጠር ወዴት መሄድ እንዳለበት ማወቅ ይኖርበታል። የሚሄድበት

መንገድ ጊዜውን ይወስናል። ወዴት እንደሚሄድ ማወቅ በጣም አስፈላጊ

ነው። አካሄድና ፍጥነት ሁለተኛ ነው። (Where you are heading is

more important than how fast you are going)፤ ከከበደ እንደምናየው

ያለፈ ጊዜ አለ። የሚቀጥለው ነገ ደግሞ ገና አልደረሰም። ስለዚህ መወሰን

የምንችለው አሁን ላይ ብቻ ነው። ከላይ በከበደ ሁኔታም ያየነው ይህንን

እውነታ ነው። ከበደ መወሰን አለበት፤ አሁን ማለትም ልክ ስልኩን እንደረሳ

እንዳወቀ ማድረግ ያለበትን መወሰን አለበት። ስለዚህ ውሳኔ መስጠት

የምንችለው በአሁን ላይ ብቻ ነው። ሰለዚህ አሁናችንን እንዴት ለማሳለፍ

ወይም ለመጠቀም እየወሰንን ነው?

ስለ ጊዜ መታወቅ ያለበት ሌላው ትልቁ ነገር ከዚህ በላይ እንደ ተነጋገርነው

አሁን የምናደርገውን ብንወስንም ባንወስንም አሁን ያልፋል። ስለዚህ

118 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 119: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

9 ክፍል

በአሁን ላይ ወስነን ሕይወታችንን ወደ ምንፈልገው አቅጣጫ መውሰድ ብቻ

የእኛ ኀላፊነት ነው። ይህ ካልሆነ ግን ሕይወት እኛ ባልወሰንነው ወይም

ባላቀድነው ነገር ተወስኖ ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ ይሄዳል። ያለ ኮምፓስ የት

እንደምንሄድ አናውቅም። ኮምፓስ ያለንበትን ይጠቁማል። አይቀያየርም።

ውይይት

❖ ዓይናችሁን ጨፍኑ። የሰሜን እና የምዕራብን አቅጣጫ

ተራ በተራ አቅጣጫውን ጠቁሙ።

❖ እንደምንመለከተው ሰው ሁሉ ወደ ተለያየ አቅጣጫ ነው

የሚመለከተው።

ስለዚህ ሕይወትም እንዲሁ ነው። በምድር ያለን ጊዜ ሰዓት፣ ቀን፣ ዓመት፣

ዓመታት በጊዜ ልኬት አይበላለጡም። ውስን ነው። እኛ ግን በጊዜ ውስጥ

የምናደርገውን ነገር መወሰንና ማስተካከል እንችላለን። ስለዚህ ለሕይወት

ያለን ዓላማ ምንድን ነው? ይህንን ዓላማ በደንብ አትኩሮ ማየቱ ይረዳል።

ጊዜያችንን እንዴት እንደምናጠፋ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር ከሰጠን ዓላማ

አንጻር እንዴት እንደሚሄድ ማወቅ አለብን?

❖ ለመንፈሳዊ ሕይወት

❖ ለቤተሰብ

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 119

Page 120: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

9 ክፍል

❖ ለትዳር

❖ ለልጆች

❖ ለራሳችን

እነዚህ ከላይ የጠቀስናቸው እውነቶች ወይም (Compass) ሲሆኑ ይህንን

ግን በየዕለቱ እያደረግን አይደለንም ያለነው፤ ለምን?

ምክንያቱ ጊዜያችን በአስፈላጊው ሳይሆን በማያስፈልግ እና በአስቸኳይ ነገር

ስለ ተሞላ ነው። ስለዚህ ያለንበትን ተረድተን የቀኑ ውሎአችን መለወጥ

ያለብን እኛው ራሳችን ነን።

ያለን ጊዜ አሁን ነው። አሁን ደግሞ የሚለካው በደቂቃ፣ በሰዓት ነው።

ጊዜአችንን የምናጠፋው ወይም የምንጠቀመው በደቂቃ ነው። በአንድ

ጊዜ 15፣ 30፣ 45 ወይም 60 ደቂቃ መጠቀም ማጥፋት አንችልም። ስለዚህ

የምናደርገው ነገር በደቂቃ ከዚያ በሰዓት ከሆነ እያንዳንዱን ሰዓትና ደቂቃ

ማክበር ይኖርብናል። የሰው ሕይወት የደቂቃዎችና በደቂቃዎች ውስጥ

የሚደረጉ ነገሮች ውጤት ነው። በየደቂቃው የምናደርገው ነገር

ሕይወታችንን ይወስነዋል። ስለዚህ ደቂቃችንን፣ ሰዓታችንን፣ ቀናችንን

ወይም ሳምንታችንን የምናጠፋው እንዴት ነው? ሕይወታችን የእነዚህ

ትንንሽ ደቂቃዎችና ሰዓታት ጥርቅም ስለ ሆነ የምናደርገው ነገር በሰዓት

ወይም በጊዜ ካላደረግነው የምንቀንሰው የራሳችንን ሕይወት ነው። ሰው

120 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 121: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

9 ክፍል

ደቂቃ ካላከበረ ሰዓት ማክበር አይችልም፤ ሰዓት ካላከበረ ቀን ማክበር

አይችልም፤ ቀን ካላከበረ ሳምንታት፣ ወራት እና ዓመታት እንዲሁ ይሄዳሉ።

ስለዚህ የእኛ ኀላፊነት ደቂቃችንን የማክበር እና አሁንን በሚገባ መጠቀም

ነው።

ለማጠቃለል የሰው ልጅ ዕድሜ የተገደበ መሆኑን እያሰብን በቀሪ ጊዜያችን

እግዚአብሔር ለፈጠረን ዓላማ እና በምድር ላይ በምንኖርበት ጊዜ ደግሞ

ለተሰጠን ዓላማ ጊዜያችንን እንዴት መጠቀም እንዳለብን ዛሬውኑ መወሰን

ይኖርብናል።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 121

Page 122: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

10 ክፍል

በትዳር ውስጥ ኀላፊነትን መወጣት (Expectations in marriage and sharing responsibilities)

ባልና ሚስት በትዳራቸው የሚፈልጉት ወይንም ከትዳራቸው የሚጠብቁት ነገሮችና የሥራ ክፍፍል

ዓላማዎች ❖ ኀላፊነትን በትክክል መረዳት፤

❖ የተሳሳቱ አመለካከቶችን ማረም፤

❖ ኀላፊነትን በትክክል የመወጣትን ጥቅም ማየት ናቸው።

መግቢያ በአንድ ሴትና በአንድ ወንድ መካከል ፍቅር ሲጀመር በትዳራቸው ውስጥ

የሚፈልጉትንና ከተጋቡም በኋላ በቤት ውስጥ ያሉትን የሥራዎች ክፍፍል

እንዴት እንደሚወጡት ብዙም አያሳስባቸውም። አብዛኛዎቻችንም

እንደዚህ ነው ወደ ትዳር የገባነው። ከትዳር በፊት በለመድነው የብቸኝነት

ኑሮ ዛሬ መቀጠል አይታሰብም። ስለዚህ የቤት ውስጥ ሥርዓትና ኀላፊነት

መለወጥና መሻሻል ይኖርበታል። እንደ ድሮ ልቀጥል ማለት አላስፈላጊ

122 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 123: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

10 ክፍል

ግጭቶችንና ችግሮችን ሊያመጣ ይችላል። ስለዚህ በዚህ ጥናት እንዴት

ራስን ለመለወጥ እና በደስታ ቤት ውስጥ ያለውን የሥራ ኀላፊነት ማከናወን

እንደሚቻል ለማየት እንሞክራለን።

የመወያያ ጥያቄዎች

1. ከቤት ውስጥ ሥራ መሥራት የምትወዱት ምንድን ነው?

2. ከቤት ውስጥ ሥራ መሥራት የምትጠሉት ምንድን ነው?

3. ባለፈው ወር በቤት ሥራ የተነሳ ለክርክር ወይንም ለጥል

ምክንያት የሆነው ምን ነበር?

የጥናቱ ይዘት

ፎከስ ኦን ዘ ፋሚሊ (Focus on the family) ባወጣው ጽሑፍ ላይ ብዙ

ጊዜ ባልና ሚስት በቤት ውስጥ ያሉትን ሥራዎች የሚከፋፈሉት በወንዶችና

በሴቶች የተለመዱትን በመከተል ነው። ለምሳሌ፣ ሚስት ወጥ መሥራት

ጠንቅቃ እንድታውቅ ይጠበቃል። ባል ደግሞ የተበላሸ ምድጃ እንዲጠግን

ይጠበቅበታል። ሌሎች ደግሞ የሥራ ክፍፍል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው ብለው

ሊያስቡ ይችላሉ። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ የወንድና የሴት ሥራ ብሎ

አይከፋፍልም።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 123

Page 124: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

10 ክፍል

እያንዳንዳችሁ ሌሎችን የሚጠቅመውንም እንጂ፣ ራሳች

ሁን የሚጠቅመውን ብቻ አትመልከቱ። በክርስቶስ

ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተም ዘንድ ይሁን።

ፊልጵ. 2፥4-5።

እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር

መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።

እግዚአብሔርም ባረካቸው፣ እንዲህም አላቸው፡- “ብዙ

ተባዙ፤ ምድርንም ሙሉአት፤ ግዙአትም፤ የባሕርን

ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ

ትንም ሁሉ ግዙአቸው።”

(ዘፍ. 1፥27-28)

የመወያያ ጥያቄ

❖ በቤት ውስጥ ያለውን የሥራ ክፍፍል በተመለከተ ልምዳችሁ

ምን ይመስላል?

ብዙውን ጊዜ ሰዎች ወደ ትዳር ዓለም ሲገቡ ከወላጆቻቸው የወረሱትን

ባሕርይ የማንጸባረቅ ዝንባሌ አላቸው። እንደ ክርስቲያን የእግዚአብሔር

ቃል ምን ይላል የሚለውን ማየቱ በጣም ይጠቅማል።

124 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 125: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

10 ክፍል

ኤፌሶን 5፥22-26 ያለውን ክፍል አንብቡና ተወያዩበት። መጽሐፍ ቅዱስ በቤት ውስጥ እንዴት መኖር እንዳለብን በግልጽ

ያስተምረናል። ሚስቶች ባሎቻቸውን ሲያከብሩ ባሎች ደግሞ ሚስቶቻቸውን

ሲወዱ እግዚአብሔር በረከቱን ያዛል። በመሥራት የሚመጣውን ድካም

በመቀነስ ትርፍ የዕረፍት ጊዜን ለማግኘትም ይረዳል።

❖ እንደ ባልና ሚስት ወይም እንደ ቤተሰብ በቀን ስንት ሰዓት ያህል ያለ

ሥራ አብራችሁ ታሳልፋላችሁ?

ቤተሰብ አብሮ ጊዜ የሚያሳልፉ ከሆነ የበለጠ መተዋወቅ፣ መቀራረብና

በፍቅር ማደግን ያበረክታል። አብሮ ለእራት በመውጣት፣ አልፎም ከተቻለ

በዓመት አንድ ጊዜ ለአንድ ወይም ለሁለት ሳምንት አብሮ ከከተማ መውጣት

እጅግ ጠቃሚ ነው።

ለምሳሌ፡-

❖ ደስ የሚሉ ትዝታዎችን መፍጠር፤

❖ አዳዲስ የሕይወት ልምዶችን ከሌሎች ማግኘት፤

❖ የሌሎችን ሰዎች ሕይወት በማየት አእምሮን ማስፋት እና የሕይወት ትርጉም ሰፋ ባለ መንገድ ማየት መልካም ነው።

Discover Corp. vacation with purpose በ April 27, 2017 ባወጣው

ጥናት ላይ 99 በመቶ ሰዎች ከሚኖሩት አካባቢ ርቀው ለዕረፍት ሲሄዱ ብዙ

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

125

Page 126: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

10 ክፍል

ደስ የሚሉ ጊዜ ያሳልፋሉ። 98 በመቶ የሚሆኑ ልጆች አዳዲስ ነገር ለመማር

ችለዋል። 92 በመቶ የሚሆኑት ቤተሰብ ደግሞ በቤት ውስጥ በቀላሉ

ለመግባባት አስችሏቸዋል።

እንደ ክርስቲያን ቤተሰብም ወደምንሄድበት ሁሉ የክርስቶስን ወንጌል ይዘን

ስለምንሄድ ለሌሎችም ይህንን የወንጌል ብርሃን የምንወስድበትም መልካም

አጋጣሚ ነው። ማርቆስ 6፥15 “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልን ለፍጥረት

ሁሉ ስበኩ” ይላል።

በቤተሰብ የዕረፍት ጉዞ ላይ ያጋጠማችሁን ጠቃሚ ልምምዶች ለቡድናችሁ

አካፍሉ።

ተግዳሮት በባልና ሚስት ትዳር ውስጥ የሚፈልጉትን ነገር አለማግኘት ደስታንና

ሰላምን ከጊዜ ብዛት ሊያደበዝዝ ይችላል። ዕድሜ ሲጨምር አቅም ሲደክም

ፍላጎትም ሊቀየር ይችላል። በቤት ውስጥ የተመጣጠነ የኀላፊነት ክፍፍል

ከሌለ ድካም እና መሰላቸትን ያስከትላል።

❖ ደስታችሁና ፍቅራችሁ አሁንም ትኩስ ነው? ወይስ መታደስ

ያለባቸው ነገሮች አለ ብላችሁ ታስባላችሁ?

126 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 127: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

10 ክፍል

የትዳርን ደስታ ከሚያቀዘቀዙ ተግዳሮቶች/ እውነታዎች በጥቂቱ፤

1. የትዳር ጓደኛችንን ፍላጎት ሁሉ አሟላለሁ ብሎ ማሰብ።

2. ጓደኝነት ሁሉ በትዳር ውስጥ ብቻ ነው ብሎ ማሰብ።

3. ባል የሚስት ሚስትም የባል ትኩረት ብቻ ነው ብሎ ማሰብ።

4. ትዳር ሲጀመር የነበረውን ስሜት ሁል ጊዜ መጠበቅ።

5. የቤት ውስጥን የሥራ ክፍፍል በአግባቡ አለመወጣት። ከላይ የተጠቀሱት Divorce magazine በ July 24, 2019 ከጠቀሳቸው

ዝርዝሮች መካከል ናቸው። ሌላውና መረሳት የሌለበት በ1848 የተጀመረው

የሴቶች እኩልነት ጥያቄ ከመጠን በላይና ከታሰበው ጥቅም አልፎ የቤት

ውስጥ ማስፈራሪያ ሲሆን ትዳርን ያቀዘቅዛል።

ለሁሉም መልስ የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ከትዳራችን ስለምንፈልገውና

ስለ እያንዳንዳችን ኀላፊነት መወጣት ምን ይላል? በዚህ ዘመን ትዳር

መጠቀሚያና ፍላጎትን ብቻ ማሟያ ተቋም ሆኗል።

የመፍትሔ ሀሳብ

ትዳርን የመሠረተው እግዚአብሔር በዋናነት ያስቀመጠው የምናገለግልበትና

የምንሰጥበት ተቋም አድርጎ እንጂ የምንቀበልበት ተቋም ብቻ አድርጎ

አይደለም።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 127

Page 128: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

10 ክፍል

ጌታ ኢየሱስ በማቴዎስ 19፥6 እንዲህም አለ፤ “ሰው አባቱንና እናቱን

ይተዋል፤ ከሚስቱም ጋር ይጣመራል፣ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ’

የተባለው በዚህ ምክንያት አይደለምን? ከእንግዲህ አንድ ሥጋ ናቸው

እንጂ ሁለት አይደሉም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ያጣመረውን ሰው

አይለየው።”

ስለዚህ ራስ ወዳድነትን በመተው እግዚአብሔር የሰጠንን ትዳር በፍቅርና

በአክብሮት እንያዝ። የቤት ውስጥ ሥራን አመጣጥኖ በመከፋፈል ድካምን

እንቀንስና ብዙ ደስ የሚሉ የጋራ ጊዜን እናብዛ።

የመወያያ ጥያቄዎች

1. ወደ ትዳር ስትገቡ ወይንም ትዳርን ስታስቡ በመጀመሪያ ወደ

ሐሳባችሁ የሚመጣው ማገልገል ወይንስ መገልገል?

2. የቤት ውስጥ ሥራን የተከፋፈላችሁት እንዴት ነው?

3. በዓመት ስንት ጊዜ የቤተሰብ የዕረፍት ጊዜ አላችሁ?

128 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 129: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

መልካም ምሳሌ

10 ክፍል

ጠባየ መልካምን ሚስት ማን ያገኛታል? ከቀይ ዕንቊ

እጅግ ትበልጣለች። ባሏ ሙሉ በሙሉ ይተማመንባታል፤

የሚጐድልበትም ነገር የለም። በሕይወት ዘመኗ ሁሉ፣

መልካም ታደርግለታለች እንጂ አትጐዳውም።

ምሳሌ 31፥10-12

ማጠቃለያ

❖ በቤት ውስጥ ብዙ ጊዜ የሚያጣላችሁን የሥራ ዓይነት/ቶች

ዘርዝሯቸው፡፡

❖ በመስማማት የቤት ውስጥ ሥራዎችን ተከፋፈሏቸው።

❖ በዓመት ቢያንስ ለአንድ ሳምንት ከከተማ በመውጣት እንደ

ቤተሰብ ለመዝናናት ሞክሩ።

❖ በተቻላችሁ መጠን አብራችሁ ለእራት ውጡ።

የቤት ስራ

1. የምትወዱትን የሥራ ዓይነት ዘርዝሩ።

2. መሥራት እየፈለጋችሁ ያቃታችሁን የሥራ ዓይነት ዘርዝሩ።

3. አዳዲስ ሙያዎችን ለመማር ሞክሩ።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 129

Page 130: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

11 ክፍል

ኑሮ በአሜሪካ

ክርስቶስን ማእከል ያደረገ ቤተሰብ የተሳካ ኑሮ ምን ይመስላል?

ዓላማዎች

❖ የምንኖርበትን አገር እሴት ማወቅ፣

❖ የክርስትናን ሕይወት ተግዳሮቶች መለየት፣

❖ የክርስትናን ኑሮ ተግዳሮቶችን ማሸነፍ፣

መግቢያ

አሜሪካ ሠፊ፣ ሀብታም እና በዘመናችን ካሉት ሃያል አገራት መካከል ቀዳሚ

ናት። እኛ በዚች አገር የምንኖር ስለዚች አገር በቂ እውቀት ቢኖረን

የሚጠቅመንንና የሚጎዳንን ነገር ለይተን ለማወቅ ይረዳናል። ምክንያቱም

እውቀት የሕይወትን ጉዞ ሲያቀልልን አለማወቅ ደግሞ ኑሮን ከባድ

ሊያደርገው ስለሚችል ነው። እኛ በአሜሪካን የምንኖር ከአገራችን ስንወጣ

እንደ ማንኛውም ስደተኛ ኑሮአችን እንዲቀልና እንዲሻሻል ፈልገን ነው።

130 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 131: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

11 ክፍል

“Coming to America” የተባለው ፊልም በአስቂኝ ሁኔታ ያሳየው ታሪክ

እውነተኛ ሆኖ በሰው ላይ ቢደርስ ግን ከማሳቅ ይልቅ ሊያስለቅስ ይችላል።

የአሜሪካንን ብልጽግናና የተደላደለ ኑሮ በተለያዩ አቅጣጫዎች ስለ

ሰማንና ስለ ተረዳን ወደ እዚህ መጥተናል። በድሮ ጊዜ ሰዎች ወደ አሜሪካ

የሚመጡት ለትምህርትና ለተለያዩ ሥልጠናዎች ነበር። አሁን ግን ይህ

በጣም ተቀይሯል። ብዙዎች ከዓለም ዙሪያ የኢኮኖሚና የፓለቲካ ስደተኛ

በመሆን ወደ አሜሪካ ይገባሉ።

ተወልደው ያደጉበትን አገር ወደ ኋላ በመተው አዲስን ኑሮ ይጀምራሉ።

በአእምሮአቸው የተሳለው ብልጽግናና ነጻነት ደምቆ እየታያቸው የአሜሪ

ካንን ኑሮ ለመኖር ሩጫን ይጀምራሉ። አሜሪካ ምንም ሀብታምና ሰላማዊ

ሀገር ብትሆንም ብዙዎች እንደሚያስቡአት ግን ገነት አይደለችም። በውስ

ጧም ብዙ ጠቃሚና ጐጂ የሆኑ ባሕሎች እና ልምዶች ያላት ሕዝቡ ለፍቶ

የሚኖርባት አገር ናት።

ሰርተው ሀብት በማካበት፣ ተምረውም የትምህርት ጥማታቸውን በማርካት

የአሜሪካንን ሕልም እየኖሩ ያሉ ብዙ ሰዎች አሉ። በአንጻሩ ደግሞ እንዳሰቡት

ሳይሆን ግን የከሰሩ፣ ትዳር የፈረሰባቸው እና ቤተሰባቸው የተበተኑባቸውም

አሉ። ሌሎች ደግሞ ክርስቶስን የሕይወታቸው ዋና አድርገው በመጠን

እየኖሩ በክርስትና ሕይወታቸው በርትተዋል።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 131

Page 132: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

11 ክፍል

የመወያያ ጥያቄዎች

1. እናንተስ ኑሮን በአሜሪካ እንዴት አገኛችሁት?

ከዚህ በመቀጠል በአንድ አገር ውስጥ ሰዎች የተለያየ ኑሮን የሚኖሩት ለምን

እንደ ሆነ ለማየት እንሞክራለን። በመጀመሪያ አሜሪካውያን ዋና እሴት ነው

የሚሉትን እንመለከታለን። በመቀጠል የእግዚአብሔር ቃል ስለ ስኬት

የሚያስተምረንን እናያለን። በ2014 Strayer University ስለ ስኬት

ባወጣው ጥናት ላይ 90% አሜሪካውያን ስኬትን የሚለኩበት መለኪያ

አስገርሟቸዋል። ስኬት ማለት አንድ ሰው የሕይወት ሕልሙን፣

የሚደርስበት ቦታና ሰዎች ከቤተሰባቸው ጋር ጥሩ የሆነ ኅብረት ሲኖራቸው

ነው ብለዋል። በጥናቱም ላይ በደስታ መኖር ዋናው የስኬት መለኪያ

መሆኑን ጠቁመዋል። ይሄ ሁሉ እንዲከናወን ጠንክሮ ሥራን መሥራትና

ገንዘብ በማግኘት የሚፈልጉትን ማከናወን ያስችላል ብለው ያምናሉ።

ስለዚህ ጠንክሮ መሥራት ሀብት በማካበት ከዚያም ወደ ሥልጣን በማደግና

ዝነኛ በመሆንም ሰዎች ሕልማቸውን እንዲኖሩ ዕድልን ይሰጣል። ይህ

ጥቂት ሰዎች የደረሱበት የመሰላል ጫፍ ሌሎችን ተግተው እንዲሰሩና

የስኬት ውጤት ተካፋዮች እንዲሆኑ ተስፋን ይሰጣል።

132 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 133: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

2. ስኬት ለእናንተ ምንድን ነው?

11 ክፍል

3. እንደ ጥንድ የጋራ የሆነ ሕልማችሁ ምንድን ነው? ጥቂት ተወያዩ።

ስኬት (success) በኦክስፎርድ መዝገበ ቃላት ትርጉም መሠረት፣ “ሰው

ያቀደውን ሕልም ወደ ግብ ሲያደርሰው ነው” ይላል።

ሰዎች በየትኛውም አገር ላይ ሲኖሩ የራሳቸው የሆነ ዕቅድ አላቸው።

ብዙ ጊዜ ግን ሰዎች አሜሪካ መግባትን ብቻ እንደ አንድ የሕይወት ዕቅድ

ይይዙታል። ነገር ግን አንድ ሰው የማደግ ፍላጎት ካለው በተሰጠው ዕድል

ተጠቅሞ ጠንክሮ በመሥራት ሕልሙ ጋር መድረስ ይችላል። የሰው የዕድገት

አመለካከት (growth mindset) ሁኔታዎችን ለመልመድ፣ ለመቋቋም፣

ለማሻሻል እና ለመለወጥ ያስችለዋል፤ ከዚያም በራስ መተማመንንም

ያሳድጋል። የራስንም ኑሮ በማሸነፍ ለሌሎች የመትረፍንም ዕድል ያስገኛል።

የሰው ልጅ በተፈጥሮው ከራሱ ተርፎ ሌሎችን ሲረዳ በኑሮው የበለጠ

ርካታን ሊያገኝ ይችላል ይባላል። በአንጻሩ ደግሞ ለውጥን የሚፈራ (fixed

mindset) ያለው ሰው በየትም አገር ቢኖር ብዙ ሊቸገር ይችላል።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 133

Page 134: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

11 ክፍል

4. የእግዚአብሔር ቃል ስለ ስኬት ምን ይላል?

ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈ

ልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግን አስቀድ

ማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት፣ ጽድቁንም ፈልጉ፣

ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴ. 6፥32-33

እንደ ቃሉ እንዳንኖር የሚያደርጉ ተግዳሮቶች፡- እውነተኛና የተሟላ፣ እንደ እግዚአብሔር ቃል የሆነ ስኬት ያለበትን ሕይወት

ብዙ ሰዎች አይኖሩትም። ለዚህም ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩትም የተወሰኑትን

በዚህ ጥናት እናያለን። ብዙ ሰዎች ወደ አሜሪካ መጥተው ኑሮን ሲጀምሩ

የሚያዩትን ቁሳዊ ነገሮች ለማግኘት ይመኛሉ። ይህም ከአቅም በላይ የሆነን

ኑሮ እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል።

አሜሪካ ምንም ሀብታም አገር ብትሆንም በውስጧ የሚኖሩት ሰዎች በኑሮ

ደረጃ የተከፋፈሉ ናቸው። Pew Research Center የተባለው የጥናት

ድርጅት ባወጣው ጥናት ላይ። በ2019 የሰዎችን የዓመት ገቢ በማየት በ3

ከፍሎታል። በዓመት ከ $120 ሺህ በላይ የሚያገኙትን ቤተሰብ ከፍተኛ ገቢ

(upper class)፣ በዓመት ከ $40 ሺህ እስከ $119 ሺህ የሚያገኙትን ቤተሰብ

መካከለኛ ገቢ (middle class) እና በዓመት ከ $39 ሺህ በታች የሚያገኙትን

ደግሞ ዝቅተኛ ወይም (lower class) በማለት አሳይቷል። ስለዚህ ሁሉም

አሜሪካዊ የፈለገውን ነገር የማግኘት እድል የተወሰነ ያደርገዋል። ይህንን

134 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 135: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

11 ክፍል

እውነታ አለማወቅ ግን ያለ አቅም ወደ መኖር ሕይወት ውስጥ ያስገባል።

ከገቢ በላይ የሆነ ኑሮ መኖር ሦስት ጉዳቶችን ሊያመጣ ይችላል።

❖ ሁለትና ከዚያም በላይ የሆኑ ሥራዎችን በመሥራት

እንቅልፍ በማጣት ለተለያዩ በሽታዎችና አደጋዎች ይዳርጋል።

❖ ከቤተሰብ ጋር ጊዜን ባለማግኘት ትዳር ሊያናጋና ቤተሰብን

ሊያፈርስ ይችላል።

❖ ለጸሎትና የእግዚአብሔርን ቃል የማንበብያን ጊዜ

በማሳጣት ወደ መንፈሳዊ ድርቀትና ድኅነት ያደርሳል።

ከእግዚአብሔር (ከምንጩ) የራቀ ሕይወት እንድንኖር

ያደርጋል። እንደ ክርስቲያን በየትኛውም ዘመን እና

በየትኛውም አገር ስንኖር ስኬት ገንዘብ ወይም ሀብት

መለኪያው መሆን የለበትም። ብዙዎች ግን ይህንን ሓሳብ

በመሳት ደስታቸው በሀዘንና በጭንቀት ይተካል። ስለዚህ

በጥበብ መኖር ይኖርብናል ማለት ነው።

“ትጸልዩም ዘንድ በመጠን ኑሩ” 1ኛ ጴጥ. 4፥8

ስለዚህ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ሓሳብና ፈቃዱን ተረድተን እርሱን

እስቀድመን ሕይወትን በነጻነትና በደስታ እንኑር። ጌታ በሚከፍትልንም በር

ራሳችንን በማሳደግ ስኬታማ በመሆንና በዚያም ውስጥ የሚገኙትን የዕድል

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 135

Page 136: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

11 ክፍል

ፍሬዎች ለእኛና ለመጪውም ትውልድ እንዲኖርና እንዲጠበቅ በቃልና

በተግባር ማስተማር አለብን። በዚህ ትምህርት ያልተጠቀሱ ብዙ ጠቃሚና

ጐጂ ባሕሎች ያሉበት ምድር ስለምንኖር ለግላችንም ሆነ ለቤተሰባችን

በጥበብ እንመላለስ።

እነሆ እኔ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤

ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።

(ማቴ.10፥16)

ብዙ አሜሪካውያን ከእግዚአብሔር ይልቅ ለስፖርት (football, basket-

ball, baseball etc.) ከሰው ይልቅ ለእንስሳ ቦታን የሚሰጡ ይመስላል።

ስለ ሌሎች አገራትና ባሕሎቻቸው ብዙ ግድ አይላቸውም። ብዙ ጊዜ

የራሳቸውን ምቾት ከሌላው ማስቀደም ይፈልጋሉ። እነዚህን የመሳሰሉ

ነገሮችን አለማወቅ ወደማያስፈልጉ ግጭቶችና አለመግባባቶች ሊወስዱን

ይችላሉ።

በመጨረሻም የምንኖርበት አገር ገንዘብን የስኬት መመዘኛ፣ ጥሎ

ማለፍን የአቅም መለኪያ ያደረገ ስለ ሆነ መጠንቅቀ አለብን። ምክንያቱም

ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ኅብረት፣ ከቤተሰባችን ጋር ያለንን ሕይወትና

ከአገሩም ሕዝብ ጋር ያለንን ማኅበራዊ ኑሮ ሊያበላሸው ይችላል።

136 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 137: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

11 ክፍል

መልካም ምሳሌዎች የእግዚአብሔር ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ከአገራቸው ወጥተው

በስደት ምድር እየኖሩ እግዚአብሔርን በመተማመን እና ቃሉን በመታዘዝ

ኑሮአቸውን እንዴት በጽድቅ እንደኖሩ ይነግረናል። የነበረባቸውን ችግሮችና

ፈተናዎችም አልፈው አምላካቸውን አስከብረው ወዳሰበላቸው ከፍታ

ለመድረስ ችለዋል። እግዚአብሔርን የሕይወታቸው ማእከል በማድረግ

የራሳቸውን ጊዜያዊ ፍላጐት በትዕግስት በመተው በሚኖሩት አገር መልካም

ተጽእኖ አምጥተዋል። እግዚአብሔርም እነዚህን ሰዎች በምድራዊም ሆነ

በሰማያዊም በረከት ባርኳቸዋል።

ለምሳሌ፣ ዮሴፍ በግብፅ ምድር የሆነውን መመልከት ይቻላል። ዮሴፍ ካየው

ሕልም የተነሳ ብዙ ጥላቻ ከወንድሞቹ ደርሶበታል። በጽድቅ ስለ ኖረም

በእሥር ቤት ተጥሏል። ነገር ግን እግዚአብሔር በመጨረሻው አከበረው።

በዘመኑም ለነበረው ረሃብ መፍትሔ አድርጎት የአገር ገዥ አድርጎታል።

(ዘፍ. 39፥9)

ሌላው ዳንኤል በባቢሎን መንግስት ሥር በነበረበት ወቅት የሆነውን ማን

ሳት ይቻላል። ዳንኤል በባዕድ ምድር በምርኮ ሄዶ ሳለ ራሱን ከእርኩሰት እና

ከጣኦት አምልኮ ስለ ጠበቀ እግዚአብሔር ከፍ አድርጎታል። በአራት ነገሥ

ታት ውስጥ በመሪነት ቦታ ላይ ተቀምጦ እግዚአብሔርን አስከብሯል። (ዳን.

1፥8)

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 137

Page 138: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

11 ክፍል

በተጨማሪ ሩት ሕዝቧንና አገሯን ትታ ወደ እስራኤል ምድር በመምጣት

እግዚአብሔርን ለማምለክ በመወሰንዋ የክርስቶስ ትውልድ ሐረግ ውስጥ

መግባቷ ሊጠቀስ ይችላል። (ሩት 1፥16-17)

ከላይ የተዘረዘሩትን የእግዚአብሔር ሰዎች ታሪክ ካነበባችሁ በኋላ ስለ

እነዚህ ሰዎች ሕይወት ተወያዩበት።

5. እነዚህን የእግዚአብሔር ሰዎች አንድ ያደረጋቸው ነገር ምንድን ነው?

6. ያለንበት አገር እሴቱና ባሕሉ ምን ያህል መንፈሳዊ ሕይወታችን ላይ ተጽእኖ አድርጓል?

አስተማሪ ታሪክ

ዛሬም በአሜሪካ ምድር እየኖሩ ክርስቶስን የሕይወታቸው ማእከል ያደረጉም

አሉ። በ1990ዎቹ አጋማሽ ግርማ ከቤተሰቦቹ ጋር ወደ አሜሪካን አገር

መጣ። ያኔ እርሱ የ16 ዓመት ወጣት “የሃይ ስኩል” ተማሪ ነበር።

ካሊፎርኒያ በምትገኝ ትንሽ ከተማ ለ3 ዓመታት ያህል ከኖረ በኋላ ግርማ

ቤተሰቦቹን ተከትሎ ወደ ዴንቨር ኮሎራዶ መጣ። በዚያን ጊዜ ኮሎራዶ

እንደ ዛሬው አላደገችም ነበር። ስለዚህ አገር ለመልመድ ብዙ ጊዜ

አልፈጀባቸውም። ግርማም ጌታን እያመለከ እና እያገለገለ ትምህርቱን

እየተማረ ሥራም እየሰራ ቤተሰቡንም በመርዳት ኑሮውን ቀጠለ። በ2004

138 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 139: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

11 ክፍል

ሁለት መኝታ ክፍል ያለውን “ታውን ሆም” በመግዛት ከቤተሰቦቹ ቤት

ወጣና ባለቤት ሆነ። ደባል በማስገባት ግማሹን ሞርጌጅ ብቻ በመክፈል

ገንዘብ ለመቆጠብ ቻለ።

ግርማ በግል ኑሮው ብቻ ሳይሆን በቤተ ክርስቲያን ጌታን ያመልክና ያገለግል

ነበር። በማኅበራዊ ኑሮም በቻለው መጠን ይሳተፋል። በ2006

እግዚአብሔር ግርማን በመልካም ትዳር ባረከው። ግርማና ባለቤቱ በነገር

ሁሉ እግዚአብሔርን እያስቀደሙ የሞቀ ትዳራቸውን መሠረቱ፤ ባለቤቱም

የጀመረችውን ትምህርት በትጋት በመከታተል ልታጠናቅቅ ችላለች።

እግዚአብሔርም በልጆች ባረካቸው። ግርማ አንድ ሥራ በመሥራት ብዙ

ጊዜውን ከቤተሰቡ ጋር ያሳልፋል። ኑሮአቸው መጠነኛ ስለ ነበር ባለቤቱም

አንድ ሥራ በመሥራት በቂ የቤተሰብ ጊዜ እያገኙ ልጆቻቸው እስኪያድጉ

ድረስ ያማራቸውን በዕዳ ከመግዛት ተቆጥበው ለትልቅ ቤት “ዳውን

ፔይመንት” የሚሆን ገንዘብ በማጠራቀም በ2011 በእግዚአብሔር ፈቃድና

ምሪት ግርማና ቤተሰቡ ሰፋ ያለና በቂ የሆነ ቤት ለመግዛት ችለዋል።

በቤታቸው ውስጥ በሳምንት አንድ ጊዜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ይደረጋል።

እነሱም በተቻላቸው መጠን በየቀኑ ከልጆቻቸው ጋር መጽሐፍ ቅዱስን

በማጥናትና አብሮ በመጸለይ ይተጋሉ። ዛሬም ቢሆን ኑሮአቸውን በመጠን

በመኖር ጌታን በማገልገልና ለተቸገሩት በመድረስ ይኖራሉ።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 139

Page 140: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

11 ክፍል

ግርማና ባለቤቱ የጠቀማቸው ምክር በቅድመ ጋብቻ አስተማሪያቸው

የተሰጣቸው መልካም ምክር እንዲህ የሚል ነበር። “ሁል ጊዜ በአቅማችሁ

ሳይሆን ከአቅማችሁ በታች ለመኖር ዕቅድ አድርጉ” የሚለውን ጠቃሚ ምክር

ብዙ ጊዜ ተግባራዊ ያደርጉታል። በዚህ በአሜሪካ ምድር ብድር እንደ ልብ

በሚዛቅበት እየኖሩ ግርማና ቤተሰቡ ግን ራሳቸውን “ከክሬዲት ካርድ”

እና ከማያስፈልጉ ቁሳቁስ በመሸሽ በነጻነት ይኖራሉ። አዳዲስ ነገሮች መጡ

ብለው ያላቸውን የሚሰራ እቃ አይጥሉም። እንደ አስፈላጊነቱ በጥንቃቄ

በመጠነኛ ዋጋ ይገዛሉ። ይህ ስለ ሆነም ብዙ ጊዜያቸውን ዕዳ ለመክፈል

ብዙ ሥራ ሳይሰሩ ያላቸውን ጊዜ ግን ከቤተሰባቸውና ከክርስቲያን ወገኖች

ጋር ኅብረት በማድረግ ያሳልፋሉ።

ማጠቃለያ

ክርስቶስን ማእከል ያደረገ ኑሮን መኖር እግዚአብሔር በሕይወታችን

እንዲከበር ያደርጋል። ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል እንደሚመክረን፣ “ነገር

ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥

ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል” በማለት ጌታ ኢየሱስ የኑሮን ስኬት ቁልፍ

አስቀምጧል (ማቴ. 6፥33)። ዋናው የእግዚአብሔርን መንግሥት አጥብቆ

መፈለግ ነው። የምንኖርበት አሜሪካ ግን አጥብቀን ገንዘብንና ሀብትን

በዚያም ውስጥ የሚመጣውን ሥልጣንና ክብርን እንድናስቀድም

ይገፋፋናል። “መኖሪያህ የዘላለም አምላክ ነው” የሚለውን ቃል ትተን

አሕዛብ ሁሉ የሚያሳድዱትንና የሚፈልጉትን ገንዘብ እንድንተማመንም

140 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 141: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

11 ክፍል

ይጋብዛል። እኛ ግን በእግዚአብሔር በመተማመንና በመጠን እየኖርን

በጸሎትና በቃሉ እየተጋን ብንኖር እግዚአብሔር የሚያስፈልገንን ሁሉ

ሊሰጠን የታመነ ነው። አሜን!!

የቤት ሥራ

1. የአሜሪካ እሴት “ትልቅ እና የተሻለ መሆን” ሲል የእግዚአብሔር

ቃል ግን “ኑሮዬ ይበቃኛል ማለት ትርፍ ነው” ይላል። እናንተስ

ይህን ሓሳብ እንዴት ትረዱታላችሁ?

2. በየዕለቱ በእግዚአብሔር ቃልና በጸሎት ያላችሁ ሕይወት ምን

ይመስላል?

3. በሳምንት ውስጥ ስንት ሰዓት ያህል በሥራ ላይ ታሳልፋላችሁ?

እንዴትስ ከመንፈሳዊ ሕይወታችሁ ጋር ማመጣጠን ትችላላችሁ?

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 141

Page 142: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

12 ክፍል

የማንበብ ባሕልን ማጎልበት (How to develop reading culture)

ለክርስቲያን ማንበብ ለምን ይጠቅማል? እንዴትስ የማንበብ ባሕልን ማዳበር እንችላለን?

ዓላማዎች

❖ አጥኚዎች የማንበብን ጥቅም በይበልጥ ይረዳሉ፤

❖ ምን ማንበብ እንዳለባቸው ለመለየት ይችላሉ፤

❖ የማንበብ ባሕላቸውን ለማሳደግ ይነሳሳሉ።

መግቢያ

እንደ ክርስቲያን ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ዕድገትም ሆነ በምድር ላይ

ለምንኖረው ሕይወት ያለንን መረዳት ወይም ግንዛቤ ለማሳደግ፣ በጎ

የሆነውንና ያልሆነውን ለመለየት እንዲሁም ጠቃሚ የሆነውን ለይተን

በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል ብሎም መንፈሳዊ ሕይወታችንን ለማሳደግ

ያለንን እውቀት ያለማቋረጥ ማሳደግ ያስፈልገናል። ይህንንም እውቀት በመ

142 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 143: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

12 ክፍል

ስኩ እውቀት ካላቸው ሰዎች በመካፈል፣ በመደበኛ ትምህርት በመማር

እንዲሁም መደበኛ ባልሆነ መልኩ ከተለያየ ምንጭ ተሞክሮ በመውሰድ

ልናገኝ እንችላለን። ሌላው ዋነኛ የእውቀት ምንጭ ደግሞ በዘርፉ የተጻፉ

ጽሑፎችን በማንበብ የሚገኝ ነው። በየዕለቱ በሕይወታችን ለሚያጋጥመን

ጉዳይ መረጃ ወይም እውቀት ማግኘት ሲያስፈልገን ትምህርት ቤት መግባት

እና መማር ሳያስፈልገን በመስኩ የተጻፉ መጻሕፍትን በማንበብ በቀላሉ

ልናገኝ እንችላለን። በመሆኑም መጻሕፍትን ማንበብ በቀላሉ ተደራሽ የሆነ

በመሆኑና በተለያየ መልኩ ለማግኘት ስለሚቻል ተመራጭ ያደርገዋል። ባለን

በት ዘመን እና በምንኖርበት አገር መጽሐፍን ተውሶም ሆነ ገዝቶ ለማንበብ

እጅግ አመቺ የሆነበት ሁኔታ አለ። ከመጽሐፍ ሱቆች በመግዛት፣ በመዋስ

እንዲሁም “በኦንላይን” በመዋስም ሆነ ገዝቶ በማንበብ ለመጠቀም ሠፊ

ዕድል አለ። ጉዳዩ ይህን ዕድል ምን ያህል ተጠቅመንበታል ወይም ደግሞ

ዕድሉን ምን ያህል ለመጠቀም ተዘጋጅተናል የሚለውን ጥያቄ መመለሱ ላይ

ነው።

በዚህ ምእራፍ መጽሐፍ ማንበብ ለክርስትና ሕይወታችን የሚሰጠንን ጥቅም

በአጭሩ በማንሳት ለማነቃቃት፣ ቀድሞ ካልጀመርን ከአሁኑ እንድንጀምር፣

ቀድሞ ስናነብ ከነበረና በጊዜ ሂደት ተዳክሞ የመጣ ከሆነም ለማነሳሳት ጥረት

እናደርጋለን። በመሆኑም ለምን እንደምናነብ፣ ምን እንደምናነብ፣ እንዴት

ማንበብ እንደምንችል የመነሻ ሓሳብ በማቅረብ እንወያያለን ወደ ተግባር

በመግባት ሕይወታችንን በእውቀት ለማሳደግ እንድንችል የሚያግዙንን

ነገሮች ማድረግ እንጀምራለን።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 143

Page 144: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

12 ክፍል

1. አሁን ያለነው በምን ደረጃ ላይ ነዉ? ምንስ ተግዳሮት ይታያል? መነሻ እና የመጽሐፍ ዳሰሳ

የመወያያ ጥያቄ

❖ የኛ ማኅበረሰብ የማንበብ ባሕል እንዴት ነው ብላችሁ ታስባ

ላችሁ? ላለንበት ሁኔታ መንሥዔ ነው የምትሉትን በማንሳት

ተወያዩበት።

ኢትዮጵያውያን በብዛት የማንበብ ልምድ የለንም፤ ለዚህም በርካታ

ምክንያቶችን ማንሳት ይቻላል። በትምህርት ሥርዓታችን ከነበረው ውስን

ነት እንዲሁም ሠፊ የመጽሐፍ አቅርቦት ባለመኖሩ ስለ አግዚአብሔር

ቃል፣ ስለ ክርስትና ሕይወት እንዲሁም በምድር ላይ ለምንኖረው ኑሮ

የሚደግፉ በአማርኛ ቋንቋ ወይም በእንግሊዘኛ የተጻፉ መጻሕፍት በብዛት

ባለመኖራቸው ከሌላው የዓለም ህብረተሰብ ጋር ሲነጻጸር የንባብ ባሕላችን

አናሳ ነው። የተለያዩ ጥናቶች በተለይም በትምህርት ዘርፍ የተሰማሩ እና

ሙያተኞች እና ደራሲያን በአሁኑ ወቅት የሕዝባችን የማንበብ ባሕል

አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንዳለ ያነሳሉ። ከዚህ መነሻነት እንዲሁም የጊዜ

አጠቃቀም ውስንነት የተነሳ ብዙ ዕድል ባለበት አሜሪካ ስንኖርም ይህን

ዕድል እንደሚገባ አንጠቀምበትም። ለዚህም ብዙ ምክንያቶችን ማንሳት

ይቻላል። ኑሮን ለማሸነፍ የምናደርገው ሩጫ አንደኛው ሲሆን በተለይም

የተንቀሳቃሽ ስልክ መሥፋት፣ የኢንተርኔት ተደራሽነት ማደግ፣ እንዲሁም

የማኅበራዊ ሚዲያ መሥፋፋት መረጃን በቀላሉ ማግኘት በመቻላችን

144 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 145: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

12 ክፍል

የማንበብ ፍላጎታችንን ቀንሶታል ወይም ፍላጎታችንን ተክቶታል። የዚህም

ነጸብራቅ ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ጠቃሚ የሆኑ መንፈሳዊ መጻሕፍትን

እንኳን ለማንበብ ያለን ተነሳሽነት ዝቅተኛ መሆኑ ነው። በመሆኑም ቆም

ብለን ራሳችንን ማየት የሚገባ ወቅት ላይ እንገኛለን።

በብዙ የሕይወት ጉዳዮች ላይ እንዲሁም አከራካሪ ጉዳዮች ሲያጋጥሙን ልዩ

ልዩ መጻሕፍትን በማንበብ እና መረጃዎችን በማደራጀት ለማኅበረሰባችን

የማምጣት እና የማካፈል ባሕል በሥፋት አይታይም። ስለ ዘመናዊ አኗኗር፣

ሕይወታችንን በተሻለ መንገድ ለመምራት የሚያስችለን እውቀት ለማግኘት፣

በተሰማራንበት የሥራ መስክ በየጊዜው የሚገኙ አዳዲስ ግኝቶችን ለማወቅና

ራሳችንን ተወዳዳሪ እንዲሁም ብቁ ለማድረግ ከማንበብ ውጭ ሌላ የተሻለ

እና ቀላል አማራጭ የለም። እንደዚሁም ተወዳዳሪ በሆነው ዓለም ውስጥ

ተመራጭ እንድንሆን በአጠቃላይ ባለንበት ዓለም የተሟላ የሕይወት ስብእና

በመያዝ በመንፈሳዊ ሕይወታችንና በምድራዊ ኑሮአችን ምስክር ለመሆን

ራሳችንን በእውቀትና በጥበብ ማሳደግ እና ማብቃት አማራጭ የሌለው

ጉዳይ ነው።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 145

Page 146: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

12 ክፍል

2. ለእኛ ለአማኞች የሕይወት መመሪያ ከሆነው ከእግዚአብሔር ቃል የሚገኝ ተሞክሮ

የመወያያ ጥያቄ

❖ ምን ያህል ማንበብ አለብን? ምን ያህል ብናነብ በቂ ይሆናል?

በቂ ጊዜ የለንም፤ ታዲያ ማንበብ ያለብን መቼ ነው?

“በውኃውም በር ፊት ባለው አደባባይ ላይ ቆሞ ወንዶ

ችና ሴቶች የሚያስተውሉም ሲሰሙ ከማለዳ ጀምሮ

አስከ ቀትር ድረስ አነበበው፤ የሕዝቡም ሁሉ ጆሮ የሕጉን

መጽሐፍ ለመስማት ያደምጥ ነበር።” (ነህ. 8፥3)

በዚህ ክፍል ላይ በነህምያ ዘመን በምን መልክ ሕዝቡ ቃሉን ለማንበብ

ትጋት ያሳዩ እንደ ነበርና ነህምያም ሠፊ ሥራ ባለበት እንዲሁም ባልተመቻቸ

ሁኔታ ሆኖ ግን የሕጉን መጽሐፍ ለማንበብ ያሳየውን ትጋት እናያለን። ይህ

የነህምያ ተግባር ለብዙዎቻችን የጊዜ የለንም ምክንያት መልስ ይሆናል።

ነህምያ በፊቱ ሊቆጥራቸው የሚችላቸው ብዙ ሥራዎች ነበሩት፤ ነገር ግን

ቅድሚያ ለእግዚአብሔር ቃል መስጠቱ ያለውን ጠቀሜታ የተረዳ መሆኑን

እና ይህንን በማድረጉም ከዓላማው እንዳላስተጓጎለው ከታሪኩ መረዳት

እንችላለን። ብዙ ጊዜ የዕለት ተዕለት ኑሮን ለማሸነፍ በምናደርገው ሩጫ

ምክንያት ለማንበብ ጊዜ እንዳንሰጥ ሲያደርገን ይታያል። ነገር ግን በቅድሚያ

በቂ እውቀት ስለ ነገሩ ባለመያዝ እንዲሁም እንደ ክርስቲያን የሕይወታችን

146 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 147: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

12 ክፍል

ሁሉ መመሪያ የምናገኝበትን የእግዚአብሔር ቃል በአግባቡ ባለመያዝ

መንገዳችን ሲረዝም ወይም እንዳሰብነው ሳይሆን ማየት የተለመደ ክስተት

ነው። ስለዚህ ቃሉን ማንበብ የየዕለት ተግባራችን ብናደርግ ረጅም ርቀት

ለመሄድ የምናደርጋቸውንም ነገሮች በእውቀት ላይ የተመሠረተ እንዲሆን

ያግዘናል።

በየዕለቱ ቃሉን ማንበብን ልምዳችን እስክናደርግ ግን አሰልቺ፣ ጊዜ ወሳጅ እና

ማባከን አድርገን ልናይ እንችላለን። ሆኖም ስለ ጊዜ አጠቃቀም ያገኘናቸውን

መሠረታዊ ዕውቀቶች አሟልተን ብንተገብር በየዕለቱ የተረጋጋ ሕይወት

ለመኖር፣ ኑሮአችን እሴቶቻችንን የሚደግፉ እንዲሆኑና፣ በእውቀት ላይ

የተመሠረቱ ውሳኔዎችን በማድረግ ከጊዜ እና ከገንዘብ ኪሳራ እንዲሁም

ከውጥረት፣ ከመበተን እንዲሁም ተስፋ ከመቁረጥ እንድናለን። ነህምያ

ጠላቶቹ ከዓላማው ለማሳት ሓሳቡን ሊበትኑት፣ ተስፋ ሊያስቆርጡትም ሆነ

ሊያታልሉት አልቻሉም። ከዚህም በተጨማሪ በአይሁድ ደንብ ሁል

ጊዜ በሰንበት በአክብሮት ቃሉን ሲያነቡ እናያለን። በአዲስ ኪዳንም

ሐዋርያት በምን ዓይነት እውቀት ቃሉን ሲያጠኑና ሲያስተምሩ እንደ ነበር

እንደዚሁም ይህንንም ልምምድ ደቀመዛሙርት ይዘው እንዲቀጥሉ

በአንክሮ ሲመክሩ እናያለን። ይህንንም ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ

በሚመለከተው መልኩ መክሮታል፤

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 147

Page 148: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

12 ክፍል

የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ

ሆነህ የተፈተነውን ራስህን ለአግዚአብሔር ልታቀርብ

ትጋ። 2ኛ ጢሞ. 2፥15

እስክመጣ ድረስ ለማንበብና ለመምከር ለማስተማርም

ተጠንቀቅ። 1ኛ ጢሞ. 4፥13

3. ከማንበብ የሚገኙ ጥቅሞች

የመወያያ ጥያቄ

❖ ከማንበብ ይገኛል ብለን የምናስባቸውን ጥቅሞች

ዘርዝረን እንወያይባቸው።

የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ የተዘጋጀ ይሆን

ዘንድ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ

ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም

ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል። 2ኛ ጢሞ. 3፥16-17

ለትምህርት

የትኛውንም እውቀት ወይም ጥበብ ለማግኘት ትምህርት ያለው ድርሻ ትልቅ

ነው። መጽሐፈ ምሳሌ በዋነኛነት እንደዚሁም በወንጌላት ስለ እውቀት እና

ጥበብ በብዙ ሥፍራ ተጽፏል። እግዚአብሔር ሰሎሞንን ምን እንዲሰጠው

148 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 149: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

12 ክፍል

እንደሚፈልግ ሲጠይቀው የለመነው ጥበብ እንዲሰጠው ብቻ ነበር።

ይህን ያደረገው የእግዚአብሔር ሕዝብ ታላቅ በመሆኑ እና ይህን ሕዝብ

ለመምራትም ጥበብ የሚያስፈልገው እንደ ሆነ በመረዳቱ ነበር።

እግዚአብሔርም ሕዝቡን የሚመራ መሪ በጥበብ የተሞላ፣ እርሱን የሚፈራ፣

እንደዚሁም በአግባቡ ሕዝብን ለመምራት አና ለማስተዳደር ትክክለኛ የሆነ

ሚዛን እንዲኖረው ይፈልጋል፤ ይህንንም ደግሞ ለጠየቀ በልግስና ይሰጠዋል።

የአንድ አገር መሪ ሰማያዊ ጥበብ ሲኖረው ነው ሰላም፣ ዕረፍት እንዲሁም

ብልጽግና ያለው ህብረተሰብ ሊመሠረት እና ሊቀጥል የሚችለው። ሕዝቡን

በሥርዓት፣ በሕግ እና በቅንነት ለመምራት በሌላ መልኩም እግዚአብሔርን

በማወቅና በመፍራት ለእርሱ ክብር የሚሆን ሕዝብ ለመሆን ሰማያዊ ጥበብ

ያስፈልጋል።

ጥበብ ይህን ያህል አስፈላጊ ከሆነ እና እንደ ክርስቲያን በምድር በምንኖረው

ሕይወት ጠቃሚያችን ከሆነ በቤተክርስቲያን ለአገልግሎታችን፣ ቤተሰባችንን

ለመምራት እንደዚሁም በምንሰራበት አካባቢ በጎ ምስክር ለመሆን ራሳችንን

በእውቀት ማብቃት እና ማሳደግ ያስፈልገናል።

የአስተዋይ ልብ እውቀትን ያገኛል፣ የጠቢባንም ጆሮ

እውቀትን ትፈልጋለች። ምሳ. 18፥15

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 149

Page 150: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

12 ክፍል

ሕዝቤ እውቀትን ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቶአል፤

አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ

እጠላሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ

ልጆችህን እረሳለሁ። ሆሴ. 4፥6-7

ለተግሣጽ፣ ልብንም ለማቅናት፣ በጽድቅም ላለው ምክር

እውቀት ከጥፋት እንደሚጠብቀን ሆሴዕ 4፥6 እና ምሳሌ 19፥2 ያሳየናል።

ከኀጢአት ለመጠበቅ እና ለመሸሽ ብቻ ሳይሆን በጽድቅ ለመኖር እውቀት

አስፈላጊያችን ነው።

በፍጹም ልብ ፈለግሁህ ከትእዛዝህ አታርቀኝ።

አንተን እንዳልበድል ቃልህን በልቤ ሰወርሁ። መዝ.

119፥10-11

በሌላ በኩል በምንኖርበት ህብረተሰብ እሴት የምንጨምር እንድንሆን

እና ተገቢ ምሳሌ ሆነን ሰዎችን ለክርስቶስ መንግሥት ለመማረክ ራሳችንን

በእውቀት ማሳደግ እንደሚገባን ያስተምረናል።

150 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 151: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

12 ክፍል

ጥበብም ለነፍስህ እንዲሁ እንደሚሆን እወቅ፣

ብታገኘውም ፍጻሜህ መልካም ይሆናል ተስፋህም

አይጠፋም። ምሳ. 24፥14

* * * *

እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት

ያወጣችኋል አላቸው። ዮሐ. 8፥32

* * * *

ነፍስ እውቀት የሌለባት ትሆን ዘንድ መልካም

አይደለም፤ እግሩንም የሚያፈጥን ከመንገድ ይስታል።

ምሳ. 19፥2

ለበጎ ሥራ ዝግጁ ለመሆን

በክርስቶስ በመዳን በእግዚአብሔር ቤት የምንኖረው ኑሮ በየዕለቱ የጠላትን

ፍላጻ በመስበር እና የአምላካችንን ፈቃድ በመፈጸም በሕይወታችን እርሱን

እየገለጥን መኖር ነው።

ያለ እምነት እግዚአብሔርን ማስደሰት አይቻልምና። ስለዚህ ዋነኛው ቁልፍ

ጉዳይ በመንፈሳዊ ሕይወታችን ልናድግ የምንችለው የእግዚአብሔርን ቃል

በማወቅ እና በማጥናት ብቻ ነው። (ዮሐ. 3፥16፤ ኤፌ. 6፥4)

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 151

Page 152: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

12 ክፍል

“የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም

ሰራተኛ ሆነህ የተፈተነውን ራስህን ለአግዚአብሔር

ልታቀርብ ትጋ።” (2ኛ ጢሞ. 2፥15)

* * * *

“እስክመጣ ድረስ ለማንበብ አና ለመምከር

ለማስተማርም ተጠንቀቅ።” (1ኛ ጢሞ. 4፥13)

* * * *

“በበሰሉት መካከል ግን ጥበብን እንናገራለን፣ ነገር ግን

የዚችን ዓለም ጥበብ አይደለም የሚሻሩትን የዚችን

ዓለም ገዦች ጥበብ አይደለም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር

አስቀድሞ ከዘመናት በፊት ለክብራችን የወሰነውን፣

ተሰውሮም የነበረውን የእግዚአብሔርን ጥበብ

በምሥጢር እንናገራለን።” (1ኛ ቆሮ. 2፥6-7)

4. ምን እናንብብ?

“የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ

የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ

ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።” (2ኛ

ጢሞ. 3፥16-17)

152 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 153: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

12 ክፍል

የመወያያ ጥያቄዎች ❖ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ የሚለውን እንዴት

እንረዳለን?

❖ ያነበብናቸውን የተለያዩ መጻሕፍት በማስታወስ በወቅቱ

በሐሳባችን ላይ ያመጡትን ተጽእኖ እንነጋገር።

በመሠረታዊነት ጳውሎስ ይህንን ሲጽፍ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያመለክት

ቢሆንም የመንፈሳዊ ሕይወት ዕድገት የሚመሰረትበት አንዱ መንገድ የቃሉ

እውቀት ማደግ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ከመጽሐፍ ቅዱሳችን በተጨማሪ

ሌሎች ደጋፊ መንፈሳዊ መጻሕፍትን ማንበብ ጠቃሚ ነው። የእግዚአብሔር

ቃል በተደጋጋሚ ሐሳባችንን መጠበቅ እንዳለብን ያስጠነቅቀናል። በማንበብ

የሰው ሓሳብ ምን ያህል ሊያዝ እንደሚችል ለመረዳት አያዳግትም። ሰው

ደግሞ ወዲያውም ሆነ ቆይቶ ያሰበውን ይሆናል። ስለሆነም የምናነባቸውን

መጻሕፍት የመምረጫ ዋነኛው መለኪያ ፍሬው ነው። በጎ ፍሬ እስካላቸው

ድረስ በእግዚአብሔር ቃል መሠረት ተቀባይነት አላቸው። ገላቲያ 5፥22

ላይም “እንደነዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም” ይላል። ስለዚህ

የምናነባቸው መጻሕፍት የመንፍስ ፍሬ እንድናፈራ የሚረዱን መሆን

አለባቸው። እነዚህም ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግስት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣

እምነት፣ የውሃት እና ራስን መግዛት ናችው። ፊልጵስዩስ 4፥8 ላይም

እንደ ተገለጸው የምናነበው ጽሑፍ ሐሳባችንን የሚያቀና፣ ከክርስቶስ

የተቀበልነውን ሰላም ለመጠበቅ የሚያግዘን መሆኑን ማረጋገጥ አለብን።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 153

Page 154: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

12 ክፍል

የእግዚአብሔር ቃል ምን ማሰብ እንዳለብን በዚህ ቃል ላይ ያስገነዝበናል፡፡

ስለዚህ ፍሬው እውነት፣ ጭምትነት፣ ጽድቅ፣ ንጽሕና፣ ፍቅር፣ መልካም

ወሬ፣ በጎነትንና ምስጋናን እንድናሰላስል የሚረዳን መሆኑን ማረጋገጥ

ይኖርብናል። ስለሆነም መጽሐፍ ስለ ማንበብ ስናስብ እንደ እግዚአብሔር

ሰዎች መመርመር ይኖርብናል (የሐዋ. 17፥1-4)።

መጽሐፍ ለመምረጥ ልንከተላቸው የሚገቡ

መርሆዎች

❖ ስለ መጽሐፉ ይዘት ቢቻል ቀድመው ካነበቡ በመጠየቅ መረዳት፤

❖ ስለ ጸሐፊው እሴት እና ማንነት እንዲሁም ስለሚያስተላልፋቸው

❖ መልእክቶች ጤናማነት እና ሚዛናዊነት ለማወቅ እና ለመረዳት

መሞከር፤

❖ በወቅቱ ስለ ምን ማንበብ እና ማወቅ እንደምንፈልግ በመለየት

ቀድመን መጠየቅ፣ መረጃ መያዝ ወይም ማፈላለግ፤

❖ በየወቅቱ የምናነባቸው መጻሕፍት ይዘት በተለያዩ ሓሳቦች ላይ

እንዲሆን በማድረግ የእውቀታችንን አድማስ ለማስፋት እና

ለማዳበር እንዲያስችለን ማድረግ ሊጠቀሱ የሚገባቸው ናቸው።

154 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 155: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

12 ክፍል

የመወያያ ጥያቄዎች ❖ እውቀት ለክርስቲያን ምን ማለት ነው? መጽሐፍ ቅዱሳችን ምን

ያስተምረናል? ለምን ማንበብ ያስፈልገናል? በምን አጀንዳ ወይም

አርእስት ነው ማንበብ ያለብን? ከምንስ እንጀምር?

❖ ምን ማንበብ ይኖርብናል? ምን ማንበብ አንዳለብን አንዴት

እንምረጥ?

5. የግላችንን የማንበብ ተሞክሮ በማንሳት መወያየት

የመወያያ ጥያቄ

❖ ማንበብን ባሕላችን ለማድረግ ወይም ለማንበብ

ያነሳሱንን አጋጣሚዎች በማንሳት እንወያይ።

❖ የራስህን የማንበብ ፍላጎት እና ተግባር በማነጻጸር ልዩነት

ካለው ምክንያቶችን በማንሳት ከተማርነው ጋር በማዛመድ

እንወያይበት።

መጻሕፍትን የማንበብ ልምድን ለማነሳሳት ከጠቀሙን ነገሮች አንዱ

መጻሕፍትን በማንበብ በጋራ የመወያያ መድረክ መፍጠር ሲሆን ለልጆቻችን

ደግሞ በዕድሜያቸው እና በፍላጎቶቻቸው መጻሕፍትን በማቅረብ ከትእዛዝ

ይልቅ በራሳቸው ተነሳሽነት እንዲያነቡ የማድረግ ጠቀሜታውን አይተናል።

በተጨማሪም ልጆቻችን እንደሚባለው ወላጅ የሆነውን ሁለት እጥፍ

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 155

Page 156: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

12 ክፍል

እንዲሆኑ የነገርናቸውን 50% ያደረግነውን ደግሞ 200% ስለሚሆኑ

ከምንም ነገር በላይ ልጆቻችን ከእኛ እንዲማሩ የምንፈልገውን በመሆን

ልናስተምራቸው እንደምንችል በመረዳት በተግባር መምራት አለብን።

ባለንበት ዘመን በርካታ የሆኑ ውጤታማ የቢዝነስ ሰዎች እና የአገር መሪዎች

መደበኛ በሆነ መልኩ መጽሐፍ ያነባሉ፤ ሌሎችን እንዲያነቡ ያነሳሳሉ።

ከአገር መሪዎች ኦባማ፣ የቢዝነስ ታላላቆች ቢል ጌት 50 መጽሐፍ በዓመት፣

ዋረን ብፌት 500 ገጽ በቀን፣ ጄፍ ቤዞ ሮኬት መሥራት ራሱን መጽሐፍ

በማንበብ አስተምሮ ለውጤት ለማብቃት መቻሉን ከሕይወት ተሞክሯቸው

እናያለን። ራሳችንን ለማስለመድ ማድረግ ከምንችላቸው ነገሮች ውስጥ ቤተ

መጻሕፍት በመሄድ የማንበብ፣ በቀን ውስጥ ራሱን የቻለ የማንበቢያ ጊዜ

በመወሰን፣ መጽሐፍን በቀላሉ ተደራሽ በማድረግ፣ ማታ ከመተኛት በፊት

በማንበብ እንደዚሁም ቢቻል በቀን ምን ያህል ማንበብ እንዳለብን በመወሰን

እና ግብ ማስቀመጥ ለምሳሌም በቀን አንድ ወይም ሁለት ምእራፍ ለማንበብ

በመወሰን መጀመር እንችላለን።

156 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 157: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

12 ክፍል

ማጠቃለያ

ማንበብ ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ዕድገት እና ሕልውና እንደዚሁም እንደ

የእግዚአብሔር እንደ ራሴ (አንባሳዳር) በመሆን በምንኖርበት በዚህ ምድር

ያለን ሚና በእግዚአብሔር ቃል ላይ በግልጽ ተቀምጧል። ነገር ግን እኛ

ኢትዮጵያውያን በማንብበ ረገድ ከኋላ የታሪክ ግርዶሽ እና አሁን ካለንበት

የኑሮ ዘይቤ ወይም ከጊዜ አጠቃቀም ጉድለት ያለንበትን ሁኔታ እንደ

ማኅበረሰብም ሆነ እንደ ግል እምብዛም እንዳልሆነ ጥናቶች ያሳያሉ። ስለ

ሆነም ችግራችንን ማወቃችን በራሱ የመፍትሔ አካል መሆኑን በመረዳት

እና የምናነባቸውን መጻሕፍት በጥንቃቄ በመምረጥ ቀነ ቀጠሮ ሳንሰጥ

ማንበብን ቅድሚያ ከምንሰጣቸው ነገሮች ዋነኛው መሆኑን በመገንዘብ እና

ጊዜ በማበጀት ዛሬውኑ ማንበብ በመጀመር ራስን ማብቃት ብሎም ሌሎችን

ከጥፋት ልናድን ይገባል። መጽሐፍ ማንበብ በግልም ሆነ በጋራ ልናደርግ

እንችላለን። በጋራ ማንበብ ለመበረታታት እንደዚሁም ልምድን ለመለዋወጥ

እና ለመማማርም ስለሚያስችል ጠቃሚ ነው። የማንበብ ልምድ በአንድ

ጀምበር የሚገነባ ባለመሆኑ ቀስ በቀስ እንደሚዳብር ተረድተን ቢሰለቸን

እንኳን ባለመታከት ማንበባችንን በመቀጠል ባሕላችንን ማሳደግ ይገባል።

ማንበብን በዓላማ እና ግብ በማስቀመጥ በትዕግስት ልናደርገው እንደሚገባን

መረዳትም ጠቃሚ ነው።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 157

Page 158: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

13 ክፍል

የቤተሰብን ሙሉ ጤንነት መጠበቅ

ዓላማዎች

❖ አጥኚዎች ስለ ጤንነት ሙሉ ግንዛቤን ያገኛሉ።

❖ የራሳቸውን እና የቤተሰባቸውን ጤንነት ሊያዛቡ የሚችሉ ነገሮች

ምን እንደሆኑ ለይተው ያውቃሉ።

❖ የራሳቸውን እና የቤተሰባቸውን ሙሉ ጤንነት እንዴት እንደሚ

ጠብቁ መመሪያ ያገኛሉ።

መግቢያ

ሙሉ ጤንነት ማለት ምን ማለት ነው? ጤንነታችንን ስንመለከት ሙሉ

ጤንነት አለኝ ለማለት ምን ያህል እንደፍራለን? ስለ ጤንነት አስፈላጊነት

ሁላችንም የምንስማማበት ሓሳብ ቢሆንም ስለ ጤና ግን ሙሉ ግንዛቤ

158 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 159: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

13 ክፍል

ላይኖረን ይችላል። ይኸውም ሰው ከሚታይ በሽታ ነጻ ሆነ ማለት ያ ሰው

ፍጹም ጤነኛ ነው ተብሎ ስለሚገመት ነው። ነገር ግን ሰው የሚታይ በሽታ

ሳይኖርበት በሽተኛ ሊሆን ይችላል። በተቃራኒውም ሰው በሽታ ኖሮበት

የሕመም ስሜት ላይሰማው ይችላል። የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) የጤናን

ትርጉም ሲተነትን ”ጤነኝነት የበሽታ ወይም የአካል ጉዳተኛ አለመሆን ብቻ

ሳይሆን የተሟላ ጤንነት ማለትም የአካል ብቃት፣ ጥሩ የማኅበራዊ ግንኙነት፣

የአእምሮ ጤንነት፣ መንፈሳዊነትና የስሜት መረጋጋትን ይጨምራል።”

ስለዚህ የተሟላ የጤና ግንዛቤ ከሌለን የአካል ጤንነታችንን አስፈላጊነት ብቻ

በማሰብ የማኅበራዊ፣ የመንፈሳዊ፣ የአእምሮና የስሜታዊ ገጽታ በጤና ላይ

የሚያመጡትን ተጽእኖ እንዘነጋለን። ስለዚህ ራሳችንንም ሆነ ቤተሰባችንን

በጤንነት ለመምራት መሠረታዊ የጤና ግንዛቤ ሊኖረን ይገባል።

የውይይት ጥያቄዎች

1. ከላይ ከተዘረዘሩት የፍጹም ጤንነት መሥፈርት አንጻር

የቤተሰባችሁን ጤንነት እንዴት ትመዝናላችሁ?

2. ጤንነትን ከመንፈሳዊነት ጋር እንዴት ታዩታላችሁ?

የጥናቱ ይዘት

አዳም ባለመታዘዙ ምክንያት በወደቀና በተበላሸ ዓለም ውስጥ ስንኖር

አካላችንና አእምሮአችን በበሽታ ሊጠቃ ይችላል። ሰው ዘላለማዊ ሥጋ

ባለመልበሱ ሲታመም የሥጋን ሞት ሊሞት ይችላል። ይሁን እንጂ

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 159

Page 160: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

13 ክፍል

እግዚአብሔር እንዴት በጤንነት ልንኖር እንደምንችል መርህን በቃሉ

ሰጥቶናል። የእግዚአብሔር ቃል መሪያችንና ፈዋሻችን ነው። የእግዚአብሔር

ቃል በምሳሌ መጽሐፍ እንዲህ ይላል “ልጄ ሆይ ሕጌን አትርሳ ልብህም

ትእዛዛቴን ይጠብቅ። ብዙ ዘመናትንና ረጅም ዕድሜ ሰላምም

ይጨምሩልሃል … ይህም ለሥጋህ ፈውስ ይሆንልሃል ለአጥንትህም ጠገን”

(ምሳ. 3፥1-2፣ 8)።

እግዚአብሔር ለነፍሳችን ግድ እንደሚለው ሁሉ ለሥጋችንም እንዲሁ

ግድ ይለዋል። ምክንያቱም ሰው ፍጹም ጤንነት ሲኖረዉ እግዚአብሔር

ለፈጠረው ዓላማ ለመኖር አቅም ይኖረዋል። ቤተሰቡንም እንደሚገባ

ያስተዳድራል። የእግዚአብሔር ቃል “ወዳጅ ሆይ ነፍስህ እንደሚከናወን

በነገር ሁሉ እንዲከናወንልህና ጤና እንዲኖርህ እጸልያለሁ” (3ኛ ዮሐ.

1፥2)። በተጨማሪም የሰው አካል የእግዚአብሔር መንፈስ ማደርያ እንደ

መሆኑ መጠን ሰው ሰውነቱን፣ መንፈሱንና አእምሮውን በንጽሕና እና

በጤንነት ሊጠብቅ ይገባል።

በህብረተሰባችን ዘንድ የሚታዩ የጤና ተግዳሮቶች

በህብረተሰባችን ዘንድ የሙሉ ጤንነት አመለካከት የተዛባ በመሆኑ ፍጹም

ጤንነትን ለመጠበቅ ተገቢው እርምጃ አይወሰድም። ለምሳሌ፣ አንድ ሰው

ሕመም እስካልተሰማው ድረስ ጤነኛ ነኝ ብሎ በማሰብ አቅሙ ከሚፈቅድለት

በላይ እንቅልፍና ዕረፍት በማጣት ቀንና ሌሊት በሥራ ይወጠራል። ይህ

160 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 161: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

13 ክፍል

ሰው ያልተገነዘበው ግን ዕረፍትና እንቅልፍ በማጣት፣ ከማኅበራዊ ሕይወት

በመገለልና ከቤተ ክርስቲያን በመራቅ በሰውነቱ፣ በስሜቱና በመንፈሱ

ላይ የሚፈጠረውን ተጽእኖ እና ጥቃት ነው። እንዲህ ዓይነቱ ልምምድ

ሰውን ወደ ከባድ የጤና ቀውስ ሊከተው ይችላል። ወላጆችም በራሳቸው

ላይ የሚፈጠረው የጤና ቀውስ ለልጆቻቸውም እንደሚተርፍ ማስተዋል

ይገባቸዋል።

ወላጆች የልጆቻቸውን ጤንነት መጠበቅ አንዱ የወላጅነት ኀላፊነታቸው

ነው። ወላጆች ልጆቻቸው ለሚመገቡት ምግብ ካልተጠነቀቁ ልጆቻቸው

ገና በወጣት ዕድሜያችው ለተለያዩ በሽታዎች ይጋለጣሉ። በተጨማሪም

ልጆች በቂ የሰውነት እንቅስቃሴ ካላደረጉ እና ለረጅም ግዜ “ኤሌክትሮኒክስ”

ላይ ጊዜያቸውን ሲያጠፉ የአእምሮም ሆነ የሰውነት ጤንነታቸው

ይታወካል። የልጆቻቸውን ጤንነት ለመጠበቅ ወላጆች ልጆቻቸውን ጤነኛ

ምግብ መመገብ፣ በተለያዩ ስፖርቶች ውስጥ ልጆቻቸውን ማሳተፍ፣

ከሌሎች ልጆች ጋር የጨዋታ ጊዜን በመፍጠር፣ ወደ ቤተ ክርስቲያን

በመውሰድና በቂ የቤተሰብ ጊዜን በመፍጠር የልጆችን ሙሉ ጤንነት

መጠበቅ ይገባቸዋል። ይህንን ለመፈጸም ወላጆች የራሳቸውን የአእምሮ፣

የሰውነት፣ የማኅበራዊ፣ ስሜታዊና መንፈሳዊ ሕይወት አመጣጥኖ መኖር

ይጠበቅባቸዋል። ከእነዚህ አንዱ ሲጎድል ሌላውን ጤንነት ያዛባል። ስለዚህ

አንድ ጤናን የሚያዛባ ሁኔታ ሲፈጠር ሌላውን ክፍል ከማወኩ በፊት ጤናን

ወደ ነበረበት ለመመልስ ተገቢውን እርምጃ መውሰድ ግድ ነው።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 161

Page 162: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

13 ክፍል

የውይይት ጥያቄዎች

1. አንድ ሰው ጤነኛ የሚባለው መቼ ነው?

2. ጤነኛ አመጋገብ ምንን ያጠቃልላል?

3. የአእምሮ ጫና የሰውን ጤንነት ሊያዛባ የሚችለው እንዴት ነው?

4. የልጆችን ጤና ሊያውኩ የሚችሉ ነገሮች ምንድን ናቸው?

5. ልጆች የስሜት ጥቃትና ጫና ሲደርስባቸው የሚያሳዩት

ባሕርያት ምን ምንድን ናቸው?

ለምሳሌ የቀረበ አስተማሪ ታሪክ

ዳንኤልና ሰላማዊት ከተጋቡ 12ኛ ዓመታቸውን ባለፈው ወር አከበሩ።

በትዳር ዘመናቸው ያፈሯቸው ሁለቱ ልጆቻቸው ናትናኤልና ልድያ ይባላሉ።

ናትናኤል 11 ዓመት ሲሆነው ልድያ ደግሞ 9 ዓመቷን ይዛለች። ዳንኤልና

ሰላማዊት አሜሪካን አገር ከመጡ 7ኛ ዓመታቸውን ይዘዋል። ዳንኤልም

አሜሪካ ከመጡ ጀምሮ ረጅም ሰዓት ይሠራል። ሰላማዊትም ልጆቿ የሙሉ

ጊዜ ተማሪ ከሆኑ ጀምሮ የሙሉ ጊዜ ሠራተኛ ሆናለች። ሁለቱም በፈረቃ

ይሠራሉ። ስለዚህ ሁለቱ ብዙ ግንኙነታቸው በስልክ ነው። ባለፈው

ዓመትም ትልቅ ቤት ስለ ገዙ የባንክ ዕዳቸውን ለመክፈል ዳንኤል ሌትና ቀን

ይሠራል። ሰላማዊትም በኢትዮጵያ ያሉትን ቤተሰቦቿን ለመደገፍ ተጨማሪ

ሰዓት ትሠራለች።

162 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 163: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

13 ክፍል

ናትናኤልና ልድያ ከትምህርት ቤት እንደ መጡ በሩጫ ቴሌቭዥን በመክፈት

የዕለቱን የድዝኒ ድራማ ይከታተላሉ። አባታቸው ዳንኤል እቤት ሲሆን እራት

ከመሥራት ይልቅ ልጆቹን ወደ ማክዶናልድ መውሰድ ይቀለዋል። ልጆቹም

ምርጫቸው ስለሆነ ደስ ይላቸዋል። ዳናኤል በትራንስፖርት ሥራ ላይ ስለ

ተሰማራ ብዙ የሰውነት እንቅስቃሴ አያደርግም። ቀኑን ሙሉ መኪና ሲነዳ

ውሎ ማታ ሲመጣ እንጀራ በወጥ መመገብ ይመርጣል። የቀረውን ምሽት

“ሶሻል ሚዲያ” በመከታተል ጊዜውን ያሳልፋል። ዳንኤል የሰውነቱ መጨመር

ባያስደስተውም ሕመም ስለማይሰማው ብዙ አይጨነቅም። ሰሞኑን ግን

ከወትሮ በተለየ መልኩ ውሃ ስለሚጠማው ብዙ ውሃ ይጠጣል። መጸዳጃ

ቤትም ብዙ ጊዜ በመሄዱና ለሥራውም እንቅፋት በመሆኑ ይበሳጫል። ቀስ

በቀስም ሰውነቱ ያለ ምንም ሙከራ መቀነስ ጀመረ። በአንድ ወር ውስጥ ሃያ

ፓውንድ በመቀነሱ ተደስቶ ለሰላማዊት ቦርጬ እኮ ጠፋ በማለት በደስታ

ሲያሳያት እርሷ ግን እንደ እርሱ አልተደሰተችም። ይህ የጤና አይመስልም፤

እባክህን ተመርመር ብላ ስትጨቀጭቀው “ባለፈው ውፍረት ቀንስ፣ አሁን

ደግሞ ለምን ቀነስክ ነው የምትይው? በማለት ችላ ይላታል። ሰሞኑን ግን

በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተዘጋጀው የጤና ምርመራ ቀን (9 health

fair) እንዲመረመር ግድ ስላለችው ከእርሷ ንዝነዛ ብሎ ይመረመራል።

የምርመራው ውጤት ግን እንደ ጠበቀው ባለመሆኑ ይደነግጣል። ውጤቱም

ዳንኤል የስኳር በሽታ እንዳለበትና የደም ግፊቱ ከፍ ማለቱን ያሳያል።

ሐኪሙም የዳንኤልን እና የቤተሰቡን የጤንነት ታሪክ፣ የኑሮውን ሁኔታ እና

የየዕለት ውሎውን አጥብቆ ከጠየቀው በኋላ እንዲህ ሲል መከረው፤ “የስኳር

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 163

Page 164: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

13 ክፍል

በሽታ ከሚያመጡ ምክንያቶች አንዱ በቂ የሰውነት እንቅስቃሴ አለማድረግ

እና ብዙ ካርቦሃይድሬት ያላቸውን ምግብ አብዝቶ መመገብ ነው። ነገር ግን

ይህ አንዱ ምክንያት ሲሆን የስኳር በሽታ በዘርም የሚተላለፍ በሽታ ነው።

አንተ ግን ከቤተሰብህ ማንም የለበትም ስላልክ የኑሮ ዘይቤ ለዚህ የዳረገህ

ይመስለኛል” ቀጥሎም ዳንኤል አመጋገቡን ቢያስተካክልና የሰውነት

እንቅስቃሴ ቢጀምር የጤናው ሁኔታ ሊስተካከል እንደሚችል ነገረው።

የውይይት ጥያቄዎች

1. የዳንኤልን እና የሰላማዊትን ቤተሰብ የአኗኗር ዘይቤ እንዴት

ታዩታላችሁ?

2. የዚህን ቤተሰብ ጤንነት የሚያጓድሉ ነገሮች ምንድር ናቸው?

3. ከዚህ ቤተሰብ ምን ትማራላችሁ?

የሰው ልጅ ሙሉ ጤንነት አለው የሚባለው የአእምሮ፣ የሰውነትና የመንፈስ

ጤንነቱ እኩል ሲጠበቅ ነው። ሰው ጤነኛ ሲሆን እግዚአብሔርን በሙሉ

ኃይሉ ሊያገለግል ይችላል። ታድያ ሙሉ ጤንነት እንዲኖረን ምን ማድርግ

ይኖርብናል?

164 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 165: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

የአዕምሮን ጤንነት ለመጠበቅ፡-

13 ክፍል

1. የአዕምሮ ጫና ከሚፈጥሩ ነገሮች ራስን መጠበቅ፤

2. በቂ ዕረፍትና እንቅልፍ ለማግኘት የሚያስፈልገውን ጥረት

ማድረግ (sleep hygiene)፤

3. ጤናማ ማህበረሰባዊ ግንኙነትን መፍጠር፤

4. በመልካም አመለካከት ነገሮችን ለማየት መሞከር፤

5. እርዳታ የሚያስፈልግ ሲሆን እርዳታን መጠየቅ፤

6. ስሜትን በአግባቡ መግለጽ፤

7. ይቅርታ ማድረግና ቂምን በልብ አለመያዝ፤

8. የራሳችንንም ሆነ የልጆችን “ስክሪን” ጊዜ በመጠን ማድረግ፣

ወዘተ. ናቸው።

የሰውነትን ጤንነት ለመጠበቅ፡-

1. ጤነኛና የተመጣጠነ ምግብ መመገብ (ቀይ ስጋ፣ ብዙ ቅቤና

ዘይት ያለው ምግብ፣ ነጭ ዳቦ፣ ፓስታ እና ሩዝ አለማብዛት፣

ስኳር ያላቸውን ምግቦችም ሆነ መጠጦች ማስወገድ ወይም

መቀነስ፤ የጾም ምግቦችን፤ ዓሳና ፍራፍሬዎችን መመገብ፤

በመጠኑ መመገብ)፤

2. የሰውነት እንቅስቃሴ ቢቻል በሳምንት ውስጥ ከ3-4 ጊዜ

ማድረግ፤

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 165

Page 166: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

13 ክፍል

3. ጤናማ የሰውነት ክብደት (ለቁመት የሚመጥን የሰውነት ክብደት

(BMI) መጠበቅ፤

4. በየዓመቱ አስፈላጊውን የጤንነት ምርመራ ማድረግ፤ የሰውነት

ንጽሕናን መጠበቅ፤ ሰውነትን ቢቻል በየቀኑ ወይም በየሁለት

ቀኑ መታጠብ፤ ድዩድራንት መጠቀም፤ ጥርስን ጠዋትና ማታ

መታጠብና ፍሎስ ማድረግ (ጥርስን ፍሎስ አለማድረግ የአፍ

መሽተትን ያመጣል)፤ የጥርስ ሐኪም ጋር በዓመት 1 ወይም 2

ጊዜ በመሄድ የበለጠ ምርመራና ጽዳት ማድረግ፤

5. ከበሽታ መከላከያ አንዱ መንገድ እጅን በሳሙና መታጠብ

ነው። በተለይ ልጆች ከትምህርት ቤት ሲመለሱ ወይንም ብዙ

ሰዎች ያሉበት ቦታ እንደ ገበያ እና ከቤተ ክርስቲያን መልስ እጅን

መታጠብ ወይም (hand sanitizer) መጠቀም አስፈላጊ ነው።

በተጨማሪም ቫይታሚን መውሰድ ከበሸታ ለመከላከል

ይረዳል።

6. የራስንም ሆነ የልጆችን ጸጉር በንጽሕና መጠበቅ፤

7. ልጆች ንጹሕ፣ ሥርዓትና አግባብ ያለው አለባበስን እንዲለብሱ

ማስተማር፤

8. በጤንነት ዙሪያ ያለውን እውቀት ለመጨመር መጻሕፍትን

ማንበብና ሴሚናሮችን መከታተል፤

166 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 167: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

13 ክፍል

9. የጤና ምክርን ከባለ ሙያዎችና በመረጃ ከተደገፉ ክፍሎች እንጂ

የሰማነውን ተባራሪ ሓሳብ ሁሉ አለማስተናገድ፤ ወዘተ. ናቸው።

የመንፈስን ጤንነት ለመጠበቅ፡-

1. በየቀኑ የእግዚአብሔርን ቃል በማንበብና በመጸለይ የጽሞና ግዜ

መውሰድ፤

2. ከቅዱሳን ጋር ኅብረትን ማድረግ፤ ከሌሎች ጋር ያለንን ሰላም

ለመጠበቅ የልብ ቅራኔን በጊዜ መፍታት፤

3. ሕይወትን እንደ እግዚአብሔር ቃል መምራት፤

4. እግዚአብሔር በሰጠን መክሊት እግዚአብሔርንና ህብረተሰ

ባችንን ማገልገል፤

5. በመጠን መኖር፤ ወዘተ. ናቸው።

የመኖሪያ ሥፍራን መምረጥ፡-

1. ለሥጋችንም ሆነ ለመንፈሳችን ጤነኛ የሆነ የመኖሪያ ሥፍራን

መምረጥ፤

2. አካባቢያችን ለምን የተጋለጠ እንደ ሆነ ማወቅ እና መጠንቀቅ

(የፋብሪካ ጭስ ወይም ከፍተኛ ድምጽ፤ የባቡር መንገድ፣

የፍጥነት መኪና መንገድ፣ ለጤና ጠንቅ የሆኑ የማእድን ሽታ)፤

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 167

Page 168: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

13 ክፍል

3. የመኖሪያ ቤታችንን ጽዳት መጠበቅ (በቤት ውስጥ ዋና የጀርም

መከማቻ ቦታ “ኪችን” እና መጸዳጃ ቤት ነው)፤ ፍሪጅ ውስጥ

የቆየ ምግብ መጣል፤ “ካርፔትን” በተወሰነ ግዜ ማጠብ፤

“የኤርኮንድሽን ፊልተር” መቀየር፤ ጋራጅንና መኪናችንን፣

ግቢያችንን ወይም ጓሮአችንን በንጽሕና መጠበቅ፤

4. እቤት ውስጥ ለአደጋ የሚያጋልጡ ነገሮችን ማስወገድ (እንቅፋት

ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን ማንሳት፤ ኤሌክትሪክ ከልጆች

ማራቅ፤ መድኀኒቶችና ኬሚካሎች ልጆች የማይደርሱበት

ቦታ ማስቀመጥ፤ ልጆች በመስኮት እንዳይወድቁ መረብ

ማድረግ፤ መስኮት አጠገብ መንጠልጠያ ሊሆን የሚችል ዕቃ

አለማስቀመጥ፤

5. የፕላስቲክ ዕቃ መቀነስ (ማይክሮዌቭ ውስጥ ሸክላ መጠቀም፣

ለውሃ ኮዳ ጠርሙስ መጠቀም)፤

6. “ሪሳይክል” በማድረግ የአካባቢያችንን ጤንነት መጠበቅ፤ ወዘተ.

ናቸው።

በሥራ ቦታ ጤንነትን ለመጠበቅ

1. በሥራ ላይ ለጤና ጠንቅ የሆነን ነገር ለይቶ ማወቅና አስፈላጊውን

ጥንቃቄ ማድረግ፤

168 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 169: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

13 ክፍል

2. ሥራንና ኑሮን አመጣጥኖ መያዝ፤

3. የምንደሰትበትን ሥራ መሥራት፤

4. ከአቅም ጋር የተመጣጠነን ሥራ መሥራት፤

5. በሥራ ላይ በቂ የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ፤

6. በሥራ ላይ ሊፈጠር ከሚችል የአካል ጉዳት ተገቢውን ቴክኒክ

በመጠቀም ራስን ከጉዳት መጠበቅ፤ ወዘተ.።

የቤት ሥራ

1. ባልና ሚስት አንድ ላይ በመሆን በኑሯችሁ የቤተሰባችሁን

ጤንነት የሚያጎድል ልምድ ምን እንደ ሆነ ተወያዩ።

2. ይህንንም ልምድ እንዴት እንደምታስተካክሉ ዕቅድን በማውጣት

የምትወስዱትን እርምጃ ወስኑ።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 169

Page 170: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

14 ክፍል

የገንዘብ አያያዝ በቤተሰብ ውስጥ

ዓላማ እንደ ክርስቲያን ባልና ሚስት አንድ ቤተስብ ስለ ገንዘብ ያለው አስተያየት

ምን ይመስላል የሚለውን ሓሳብ በጥንቃቄ ለማየት እንሞክራለን።

መግቢያ

ይህንን ሓሳብ በምናይበት ወቅት የተለያዩ አመለካከቶች ቢነሱ እነዚህን

አመለካከቶች በእግዚአብሔር ቃል ላይ ተመሥርተን ለመፍታት መሞከር

አለብን። ይህም ብቻ ሳይሆን ችግሩ የሰፋ ከሆነ በዚህ ትምህርት እና ብስለት

ያላቸውን ሰዎች ምክር መጠየቅ ሊኖርብን ያስፈልግ ይሆናል።

መጽሐፍ ቅዱስ በምድር ላይ ስንኖር ለሁለት ጌቶች መገዛት እንደማንችል

አጥብቆ ያስጠነቅቀናል። ኢየሱስ በምድር ላይ ሲመላለስ በጣም

170 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 171: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

14 ክፍል

ካስጠነቀቃቸውና ከአምላክ ጋር ካነጻጸራቸው ተግዳሮቶች መካከል አንደኛ

ውና ዋነኛው ገንዘብ እንደ ሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል።

ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም

አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፣ ወይም ወደ

አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፣ ለእግዚአብሔርና

ለገንዘብ መገዛት አትችሉም። ማቴ. 6፥24

አንድ ትዳር ጠንካራ መሠረት እንዲኖረው ካስፈለገ የገንዘብ አጠቃቀም

ዘዴን ባልና ሚስት በጥንቃቄ መርምረው ሊያውቁት የሚገባ ትልቅ መረዳት

ነው። በዚህ በምንኖርበት አገር ውስጥ ትልቁ የፍቺ መንሥዔ ሆኖ የተገኘው

ባልና ሚስት በገንዘብ ላይ ያላቸው አመለካከት አንድ አለመሆን እንደሆነ

እንገነዘባለን። ይህም ብቻ ሳይሆን በቤተሰብ ውስጥ ይህንን ኀላፊነት ባል

ለሚስት ብቻ፣ ሚስት ለባል ብቻ አንዳንድ ጊዜ ሲተውም ይስተዋላል።

ይህም የሚሆንበት ዋናው ምክንያት ባለቤቴ ገንዘብ አያያዝ ላይ ጎበዝ ነው

ወይም ናት ብለን ስለምናስብ ሊሆን ይችላል። ሌላው ደግሞ አንዳችን

ከአንዳችን ለመደበቅ ካለንም ፍላጎት የሚመጣም ሊሆን ይችላል። ከዚህም

ባለፈ እኔ ብቻ ስለምሰራ የማትሰራ ሚስት ወይም ባል መብት እንደ ሌላቸው

ስለምናስብም ሊሆን ይችላል፤ ወይም ደግሞ ደመወዙ የሚበልጠው ሰው

ሁሉንም ነገር መቆጣጠር አለበት የሚል የተፋለሰ አስተሳስብ በውስጣችንም

ስላለ ሊሆን ይችላል።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 171

Page 172: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

14 ክፍል

በትዳራችን ውስጥ በፍጹም ደስታ ከትዳር አጋራችን ጋር ለመኖር ከሚረዱን

አንዱ መንገድ ስለ ገንዘብ ያለንን አመለካከት ማጣጣም ነው። ገንዘብ

እግዚአብሔር በምድር ላይ ስንኖር እንደ ማንኛውም ስጦታ እንድንከባከበው

ከተሰጡን ስጦታዎች አንዱና ዋነኛው እንደ ሆነ በጽኑ መገንዘብ አለብን።

ይህ ስጦታ ከእግዚአብሔር እንደ ተሰጠን ካመንን ይህን ስጦታ በሚገባ

ለማስተዳደርና ለመጠበቅ በቂ ዕውቀቱ አለን ወይ ብለን ራሳችንን እንደ ባለ

አደራ ሁል ጊዜ መጠየቅ ይኖርብናል።

አንዳንዶቻችን ይህንን ስጦታ በሚገባና እግዚአብሔር በሚከብርበት

መንገድ በጥንቃቄ እየተጠቀምንበት ነው። አንዳንዶቻችን ደግሞ ይህ ስጦታ

በቤታችን ውስጥ ትልቅ ችግርና ያለመግባባት ዋናው ሥር ሆኖ ለትዳራችን

መናጋት ወይም መፍረስ ምክንያት እየሆነ ይገኛል። ይህንን ስጦታ በትክክል

ይዛችሁ ቤታችሁን እየመራቹህ ያላችሁ ባለ ትዳሮች እንዴት ወደዚህ ግንዛቤ

እንደ ደረሳችሁ በውይይት ጊዜ ለሌሎች ወንድሞቻችሁና እህቶቻችሁ

የሕይወታችሁን ታሪክ በትሕትና አካፍሉ።

እንደ እግዚአብሔር ሓሳብ የሚኖሩ ባልና ሚስት ገንዘብ ከጌታቸው በላይ

ሊሆን እንደማይችል ጠንቅቀው በመረዳታቸው ምክንያት ከብዙ ችግር

እና መከራ ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ማዳን ችለዋል። ስለ ገንዘብ አንድ

ባል እና ሚስት ሁሌ ሊያስቡበት እንዲሁም ሊከተሉት የሚገባው መረዳት

“ያለኝ ይበቃኛል” የሚል አስተሳሰብና የኑሮ ዘይቤ ሊሆን ይገባል። በትዳር

172 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 173: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

14 ክፍል

ውስጥ ያለ አግባብ ገንዘብን መውደድ በጣም ልንጠነቀቅበት የሚገባ ዋና

ነገር ነው። ገንዘብ ብቻ ለማግኘት ብለን ትዳራችንን እና እግዚአብሔርን

ከመበደል እግዚአብሔር ይጠብቀን።

ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፥

አንዳንዶችም ይህን ሲመኙ፥ ከሃይማኖት ተሳስተው

በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ። 1ኛ ጢሞ. 6፥10

በትዳር ውስጥ ዋናው የእግዚአብሔር መለኮታዊ ሓሳብ ከፍጥረት ጀምሮ

ሁለቱ አንድ እንዲሆኑ ከሆነ እኛም በመጀመሪያ እንደ እግዚአብሔር

ሰዎች ቀጥሎም እንደ ባልና ሚስት የገቢ ምንጮቻችንን በአንድ ላይ

ማድረግ እንዳለብን እንረዳለን። ወደ ትዳር ለመግባት በወሰንበት ቀን የእኔ

የምንለውን ነገር ሁሉ ትተን በእግዚአብሔር እና በእግዚአብሔር ሕዝብ ፊት

የገባነውን የእርስ በእርስ ቃል ኪዳን ሁሌ እንድናስታውስ እግዚአብሔር

ይርዳን። ይህንን ሓሳብ በምናነሳበት ጊዜ ብዙ ሰዎች የእኔ ሚስት ብር ዝም

ብላ ነው የምታጠፋው ወይም የእኔ ባል ብር መያዝ አይችልበትም ስለዚህ

ሁለታችንም የተለያየ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ሊኖረን ይገባል ሊሉ ይችላሉ፡፡

እኔ የራሴን ገቢ እና ወጪ እቆጣጠራለሁ፤ እርሱም የራሱን ገቢ እና ወጪ

ይቆጣጠር የሚል ሓሳብ ሊኖር ይችላል። ነገር ግን ሁሌ በትዳራችን ውስጥ

ልናስተውለው የሚገባው ነገር በትዳራችን ውስጥ የተሰጡን ስጦታዎች

በሙሉ ከእግዚአብሔር እንደ ተሰጡን እኛም የስጦታው አስተዳዳሪ

ባሪያዎች እንደ ሆንን ከተረዳን የእግዚአብሔር ሙሉ ሓሳብ በትክክሉ

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

173

Page 174: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

14 ክፍል

ገብቶናል ማለት ነው። ባልና ሚስት እግዚአብሔር ወዳሰበው በረከት ሙሉ

በሙሉ ለመግባት ከፈለጉ ገንዘባቸውን በአንድነት እና በጥንቃቄ

እግዚአብሔር በሚከብርበት ሁኔታ መጠቀም ይኖርባቸዋል።

ይህ ጥናት የተዘጋጀው ባልና ሚስት ሁሉን በአንድ ላይ አድርገው

የሚጠበቅባቸውን ግዴታዎች ይወጣሉ በሚል አስተሳሰብ ላይ ተመሥርቶ

ነው።

የመወያያ ጥያቄዎች

1. ባል፣ የአንተ ገንዘብ የሚስትህም እንደ ሆነ ታምናለህ?

2. ሚስት፣ የአንቺ ገንዘብ የባልሽም ገንዘብ እንደ ሆነ ታምኛለሽ?

3. ባል፣ ገንዘብ የምታገኝባቸውን የገቢ ምንጮች ሁሉ ባለቤትህ

ታውቃለች?

4. ሚስት፣ ገንዘብ የምታገኚባቸውን የገቢ ምንጮች ሁሉ ባለቤትሽ

ያውቃል?

እነዚህን ጥያቄዎች ከመለስን በኋላ በዋነኛነት እግዚአብሔር የሰጠንን የገንዘብ

ስጦታ በጥንቃቄ መጠቀም የምንችልባቸውን ዘዴዎች እንመለከታለን።

174 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 175: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

በጀት

14 ክፍል

በጀት ማለት አንድ ቤተሰብ ገቢውንና ወጪውን ካወቀ በኋላ ለተወሰነ ጊዜ

የሚመድበው ገቢና ወጪ ነው። ባልና ሚስት ወጪ ብለው በጀት ሲሰሩ

የገቢን ምንጭ በቀላሉ ለማየት ጊዜ ይኖራቸዋል። ይህም ብቻ ሳይሆን በቂ ገቢ

ከሌላቸው እንዴት አድርገው ገቢያቸውን ሊጨምሩ ወይም ወጪያቸውን

ሊቀንሱ እንደሚችሉ ለማየት ዕድልን ያገኛሉ። ሁል ጊዜ በአንድ ቤተሰብ

ውስጥ ቋሚ የሆኑ ወጪዎች እንደሚኖሩ የታወቀ ነው። ለምሳሌ፣ የቤት

ዕዳ ክፍያ፣ የቤት ኪራይ፣ “ትራንስፖርቴሽን” እና ለምግብ ወጭ የመሳሰሉት

በየወሩ ቋሚ የሆኑ ወጪዎች ይኖሩብናል።

ከዚህም ጋር ተያይዞ ብዙ የየዕለቱ ሌላ ወጪዎች ይኖራል። እነዚህ ወጪዎች

ከወር ወር የማያቋርጡ ከሆነ የምናገኘውስ ገቢ በቂ ነው? በቂ ካልሆነ ገቢን

ለማሳደግ ሥራ መጨመር አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ በተጨማሪም ባል

ወይም ሚስት የትምህርት ደረጃቸውን በማሻሻል ገቢያቸውን ሊያሳድጉ

የሚችሉባቸውን መንገዶች በአንድ ላይ ቁጭ ብለው እንዲወያዩ ጥሩ በር

ሊከፍትላቸው ይችላል።

ገቢን በደንብ ካወቁ በኋላ ደግሞ ወጪዎችን በደንብ ዘርዝሮ ማወቅ

አስፈላጊ ነው። ይህም ሲደረግ ወጪዎችን አስፈላጊ እና አላስፈላጊ ወጪዎች

በማለት በሁለት መክፈል ይኖርብናል። የወጪ ዓይነቶችን ካወቅን በኋላ

ልናስወግዳቸው የሚገቡን ወጪዎች ተስማምተን ማስወገድ ይኖርብናል።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 175

Page 176: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

14 ክፍል

በቀደመው ክፍል ውስጥ እንዳየነው ገቢን እንዴት መጨመር እንደምንችል

አብረን አይተን ነበረ፤ ጤነኛ ለሆነ በጀት ገቢን መጨመር ብቻ ሳይሆን

ወጪንም መቆጣጠር በጣም አስፈላጊ ነው።

ብዙ ባልና ሚስቶች ወደ ገንዘብ ችግር ውስጥ የሚገቡት ገቢ አንሷቸው

ሳይሆን ወጪያቸውን መቆጣጠር ባለመቻላቸው ነው። ይህንን ትምህርት

ከተማራችሁ በኋላ እንደ ጠንካራ ባለ ትዳር በአንድ ላይ ሆናችሁ በጀት

ለመሥራት በቂ የሆነ እውቀት ይኖራችኋል ብለን እናምናለን።

በጀት ከማውጣታችን በፊት ልናውቃቸው የሚገቡን ዋና ዋና ነገሮች፡-

1. ገቢያችንን በዝርዝር መጻፍ፤

❖ ሚስት የምትሰራ ከሆነ ገቢዋ ምን ያህል ነው?

❖ ባል የሚሰራ ከሆነ ገቢው ምን ያህል ነው?

❖ ሌሎች የገቢ ምንጮች አሉን? ካሉን ገቢውስ ምን

ያህል ነው?

2. ወጪያችንን በዝርዝር መጻፍ፤

❖ የቤት ሞርጌጅ ወይም የቤት ኪራይ ስንት ነው?

❖ ያሉብን የ “credit card” ዕዳዎች ስንት ናቸው?

❖ የወር አስቤዛ ወጪ ስንት ነው?

❖ የመኪና ዕዳ ክፍያ ስንት ነው?

176 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 177: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

14 ክፍል

❖ የመኪና “ኢንሹራንስ” ስንት ነው?

❖ ለመዝናኛ የሚያስፈልገን ገንዘብ ስንት ነው? ወዘተ.

ዝርዝሩ ይቀጥላል።

ያለንን ወጪ እና ገቢ ካወቅን በኋላ በጀታችንን በሚከተለው መንገድ

መከፋፈል ይገባናል። በእነዚህ ሓሳቦች ላይ ከተስማማን ወደፊት

እግዚአብሔር ቢረዳን እንዴት አድርገን ለጡረታና ለሕይወት ዋስትና

ገንዘብ ማስቀመጥ እና መግዛት እንዳለብን አብረን እናያለን።

❖ ለእግዚአብሔር ቤት ሥራ (አስራት)፤10%

❖ ተቀማጭ ገንዘብ፤ 20%

❖ ልዮ ልዮ ወጪ፤ 70%

እግዚአብሔር የሰጠንን ገንዘባችንን በጥንቃቄ መጠቀም ወይም ማስተዳደር

ካልቻልን በሕይወታችንና በጤናችን ለይ የሚያመጣው ራሱን የቻለ አሉታዊ

እና አዎንታዊ ተጽእኖዎች አሉ። ከእነዚህም መካከል ጥቂቶች የሚከተሉት

ናቸው፡-

❖ ጭንቀት

❖ ስጋት

❖ ክብደት መጨመር /መቀነስ/

❖ እንቅልፍ ማጣት

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 177

Page 178: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

14 ክፍል

❖ ከባለቤት ጋር አለመስማማት

❖ የፍትወተ ሥጋ ፍላጎት መቀነስ /ከነጭራሹ አለመኖር/

❖ የልብ በሽታ፤ የመሳሰሉት ናቸው።

የመወያያ ጥያቄዎች

1. በትዳራችሁ ውስጥ በጀት አላችሁ?

2. በበጀታችሁ ውስጥ ቅድሚያ የምትሰጡት ነገር ምንድን ነው?

3. እየኖራችሁ ያላችሁት ከበጀት በላይ ወይስ ከበጀት በታች ነው?

4. ሚስት፣ ለሁሉም የሂሳብ ቁጥር (including credit cards)

ያልተከለከለ “access” አለሽ?

5. ባል፣ ለሁሉም የሂሳብ ቁጥር (including credit cards)

ያልተከለከለ “access” አለህ?

ቁጠባ

መቆጠብ ወይም ማስቀመጥ ለምን ያስፈልጋል? የእግዚአብሔር ቃል

የምድር እንስሳትን እንደ ምሳሌ እያሳየ እኛ እንዴት መኖር እንዳለብን

ያስተምረናል። በምሳሌ መጽሐፍ ውስጥ “…መብልዋን በበጋ ታሰናዳለች

መኖዋንም በመከር ትሰበስባለች” (6፥8)፤ “ነገር ግን በበጋ መኖዋቸውን

ይሰበስባሉ።” (30፥25)።

178 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 179: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

14 ክፍል

ከእነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍለ ምንባባት የምንረዳው ዋናው ሓሳብ

እግዚአብሔር በሰጠን ጊዜ እና ሰዓት በደንብ መሥራት ብቻ ሳይሆን

ከሥራችን ፍሬ ከምናገኘው ገንዘብ የተወሰነውን ማስቀመጥ /መቆጠብ/

እንዳለብንም ጭምር ነው። መቆጠብ ወይም ለወደፊቱ በማሰብ እንደ

ቤተሰብ በአንድነት ከበጀታቸው ውስጥ 20% የሚያህለውን የገቢ ገንዘብ

ማስቀመጥ አስፈላጊ ነው። ይህንንም የምናደርግበት ብዙ ምክንያቶች አሉ።

በዚህ በምንኖርበት አገር ውስጥ ሰዎች በቀላሉ ሥራ እንደሚያገኙ ሁሉ

እንዲሁ ሥራቸውን በቀላሉ ደግሞ ሊያጡ ይችላሉ። ይህ በሚሆንበት

ወቅት አንድ ቤተሰብ ቢያንስ የ6 ወር ወጪን የሚሸፍንበት ገንዘብ (sav-

ing) ሊኖረው የግድ ያስፈልጋል።

በምንኖርበት ሀገር ውስጥ ገንዘብ እንዳንቆጥብ የሚያደርጉን በጣም ብዙ

ነገሮች አሉ። ከእነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹ የሚከተሉትን ይመስላሉ፤

❖ “ይህን ነገር አሁን ካላገኘሁ ሞቼ እገኛለሁ?” የሚል

አስተሳሰብ አንዳንድ ጊዜ በውስጣችን ሊመላለስ

ይችላል። በዚህ ጊዜ ውስጣችንን ካዳመጥን ስሜታችንን

ተከትለን በጣም የማይጠቅም እርምጃ ልንወስድ እንችላለን።

ይህ ሓሳብ ወደ ውስጥ በሚመጣበት ጊዜ በቅጽበት

ከመወሰን ይልቅ ጥቂት ጊዜ ወስደን ጉዳቱንና ጥቅሙን

ከባለቤታችን ጋር በጥንቃቄ መወያየት በጣም አስፈላጊ ነው።

ባልና ሚስት በአንድ ሓሳብ

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 179

Page 180: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

14 ክፍል

መስማማት ካልቻሉ ይህን ሓሳብ ለጊዜውም ቢሆን ወደ ጐን

ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

❖ በቅጽበት ውስጥ የሚገኝን ደስታ መፈለግ፤ ይህ ሓሳብ ወደ ውስጥ

የሚመጣው በዓይናችን በምናየው ነገር ስንሳብ ነው። ይህም

የሚሆነው በቴሌቪዥን ውስጥ ማስታወቂያ ስናይ እንዲሁም

ደግሞ ወደ ጓደኞቻችን እና ጐረቤቶቻችን ማየት ስንጀምር ነው።

ይህ በሚሆንበት ወቅት ራሳችንን ገዝተን “ሰው እንደ ቤቱ እንጂ

እንደ ጐረቤቱ ሊኖር አይችልም” የሚለውን ሓሳብ በትዳራችን

ውስጥ መተግበር ይጠበቅብናል።

❖ ሌላው ደግሞ “ይህቺ ክፍያዋ ትንሽ ናት ወይም ደግሞ ይህንን

መግዛት እችላለሁ” የሚል አስተሳሰብ ነው፤ ይህ ሓሳብ ወደ

ውስጣችን በሚመጣበት ጊዜ ሁሌ ራሳችንን መጠየቅ ያለብን

“ያስፈልገኛል ወይስ እፈልጋለሁ” የሚለውን ጥያቄ ነው፤

በጥንቃቄ አይተን ጥሩ የሆነውን እና ቤተሰባችንን የሚጠቅም

ውሳኔ መወሰን መቻል አለብን። በጣም ልንጠነቀቅባቸው

ከሚገቡን ነገሮች መካከል ጥቃቅን የሆኑ ወጪዎችን በጥንቃቄ

መወሰን እንዳለብን ነው። በአገራችን አባባል “የውሃ ጠብታ

ድንጋይ ይሰብራል” ተብሎ እንደ ተተረተው ጥቃቅን ወጪዎች

ተጠራቅመው በኋላ ልንወጣበት ወይም ገንዘብ መቆጠብ

የማንችልበት ትልቅ ችግር ውስጥ ሊከቱን ይችላሉ።

180 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 181: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

181

ለምን ማስቀመጥ/መቆጠብ ያስፈልጋል?

1. ለራሳችን፣ ለቤተሰባችን በማሰብ፣

2. ለክፉ ቀን፣

3. ራሳችንን ከሥጋት እና ከጭንቀት ለማዳን፣

14 ክፍል

በእናንተስ ቤት ውስጥ ያለው ተግዳሮት ምንድን ነው? ባል ስለ ሚስት

እንዲሁም ሚስት ስለ ባል በተሰጣችሁ ቦታ ላይ ሦስት ነገሮችን ዘርዝሩ።

ፈቃደኛ ከሆናችሁ የጻፋችሁትን ሓሳብ ለቡድናችሁ አካፍሉ።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

181

Page 182: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

14 ክፍል

ባል ስለ ሚስት ሚስት ስለ ባል

1.

2.

3.

1.

2.

3.

የመወያያ ጥያቄዎች

1. በእናንተ ቤት ውስጥ የማስቀመጥ ወይም የመቆጠብ ችግር ካለ

ይህንን ችግር ለመፍታት የወሰዳችሁት እርምጃ ካለ ለቡድናችሁ

አካፍሉ።

2. ችግሩን ለመፍታት እርምጃ ካልወሰዳችሁ ደግሞ አሁን

የምትወስኑት ውሳኔ ምንድን ነው?

3. ጥሩ የመቆጠብ ሥርዓት በቤታችሁ ውስጥ ካለ ለቡድናችሁ

አካፍሉ።

4. በትዳራችሁ ውስጥ መቆጠብ ወይም ማስቀምጥ አስፈላጊ ነው

ብላችሁ ታምናላችሁ? ለምን?

ዕዳ

በዚህ በምንኖርበት ምድር ውሰጥ ብድር/credit/ ትልቅ ሚና ይጫወታል።

በዚህ ክፍል ውስጥ ብድር/credit/ በሁለት መልኩ ለማየት እንሞክራለን።

182 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 183: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

14 ክፍል

አስፈላጊ እና አላስፈላጊ የሆኑ ዕዳዎች፤ እንዲሁም የእግዚአብሔር ቃል ስለ

ብድር ምን ይላል? የእግዚአብሔር ቃል መበደርን ይከለክላል? የሚሉትን

ሓሳቦች በጥቂቱ እንመለከታለን።

አንዳንድ ጊዜ ሰዎች በሕመም ወይም ለረጅም ጊዜ ሥራ በማጣት ውስጥ

ሲያልፉ ሳይወዱ በግዳቸው ወደ ብድር የሚገቡበት ሁኔታ ይኖራል። ይህ

በሚሆንበት ጊዜ ባልና ሚስት አብረው በመወያየት በተቻለ መጠን ወደ

ብዙ ዕዳ እንዳይገቡ መጣር አለባቸው።

የእግዚአብሔር ቃል መበደር እንዳለብን ባይናገርም መበደርን ግን

አይከለክልም። አማኞች በተለያየ ምክንያት ወደ ብድር ሊገቡ ይችላሉ።

ከእነዚህም መካከል ቤት ስንገዛ አብዛኛዎቻችን የግዴታ ወደ ብድር ውስጥ

መግባት ይኖርብናል። ነገር ግን አንዳንድ የብድር ምክንያቶች “ያለኝ

ይበቃኛል” ማለት ስላቃተን ብቻ የምንጠቅሳቸው ምክንያቶች ናቸው።

“ያለኝ ይበቃኛል” ማለት ስላቃታችሁ የገባችሁባቸው ዕዳዎች ካሉና

ለቡድናችሁ ይጠቅማል ብላችሁ ካሰባችሁ ለትምህርት እንዲሆን አካፍሉ።

አስፈላጊ ከምንላቸው የዕዳ ዓይነቶች ውስጥ አንደኛው የቤት ግዢ ዕዳ

ነው። ለአብዛኛዎቻችን ይህ ዕዳ በምንም መልኩ ልናስቀረው የምንችለው

አይደለም። ልናስቀረው ካልቻልንስ እንዴት አድርገን ነው ልንቆጣጠረው

የምንችለው? ብለን በደንብ ማሰብ ይገባናል። ቤት ከመግዛታችን በፊት

ለማድረግ የፈለኩት አቅሜ የሚፈቅደውን ነው? በማለት ራሳችንን

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 183

Page 184: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

14 ክፍል

መጠየቅ ይኖርብናል። የቤት ሞርጌጅ (ብድር) ከገቢያችን 40% መብለጥ

አይኖርበትም፤ ይህንንም ስንል ሁሉንም ከቤት ወጪ ጋር የተያያዙ ወጪዎችን

ሁሉ ማጠቃለል አለበት፤ ለምሳሌ፣ የቤት ክፍያ፤ የቤት “ኢንሹራንስ፤” የቤት

ግብር እና የመሳሰሉት ወጪዎች ይገኙበታል። በበጀት አስራር ውስጥ

እንዳየነው ይህ ወጪ የሚወጣው ከ70% ውስጥ ነው፤ 40% ወደ ቤት

ቀጥታ ወጪ ከሄደ በእጃችን ላይ የሚቀረው ገንዘብ 30% ብቻ ይሆናል፤

ይህ 30% ሌሎችን ወጪዎች ሁሉ እንደሚሸፍን በጣም እርግጠኞች መሆን

አለብን። ሌላው ልናተኩርበት የሚገባው ነገር ባል ወይም ሚስት ሥራ

ቢፈታ/ብትፈታ በአንዳችን ገቢ ወጪዎቻችንን ከፍለን መኖር እንችላለን

ወይ የሚለውን ጥያቄ በአትኩሮት ልናስብበት ይገባል።

አላስፈላጊ ዕዳ ብለን የምንቆጥራቸው የተለያዮ “credit card” ዕዳዎች፣

የመገበያያ ቦታ ዕዳዎች እና የመኪና ዕዳ የመሳሰሉትን ያጠቃልላል። እንደ

እነዚህ ዓይነት ዕዳዎች ብዙዎችን ሰዎች ወደ ብዙ የገንዘብ ችግር ውስጥ

ሲከቱ ይስተዋላል። ችግሩ በአንድ ጊዜ የሚመጣ ሳይሆን ቀስ በቀስ እያደገ

የሚሄድ ሲሆን ችግሩ እንዳለ በሚታወቅበት ጊዜ ከችግሩ ለመውጣት

በጣም አስቸጋሪ ይሆናል። ወደ እነዚህ ዕዳዎች በዋናነት የምንገባባቸው

ምክንያቶች እነዚህን ይመስላሉ፡- ለጊዜያዊ ደስታ መሸነፍ፣ ወርሃዊ ክፍያው

ትንሽ ናት ብሎ ማስብ፣ አስፈላጊውን እና የምንፈልገውን ለይተን አለማወቅ፣

በአካባቢያችን በሚኖር ግፊት፣ በአቅም አለመኖር /ከማን አንሳለሁ/ የሚል

የማይጠቅም አስተሳስብ ሁለንተናችንን ሲገዛን የመሳስሉት ናቸው። መበደር

ብቻ ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ሰዎች የተበደርነውን ብድር በታማኝነትና

184 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 185: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

14 ክፍል

በጊዜው የመክፈል ባሕልን ማዳበር ከአንድ ቤትሰብ የሚጠበቅ ተግባር

ነው። ይህንንም ባሕል በማዳበር የጥሩ ተበዳሪነት መልካም ውጤት ሊኖረን

ይገባል። ይህንንም ስናደርግ ወደ ፊት በአንዳንድ ችግሮች ምክንያት መበደር

ቢያስፈልገን እንኳን በትንሽ አራጣ (interest rate) በቀላሉ መበደር

የምንችልበት ሁኔታን ለራሳችን ለመፍጠር እንችላለን። ይህም ብቻ ሳይሆን

አንዳንድ መሥሪያ ቤቶች ውስጥ ተቀጥረን መሥራት ብንፈልግ እና የዕዳ

ታሪክ መታየት ቢያስፈልግ እና እኛ ጥሩ የሆነ የዕዳ ታሪክ ካለን ካለምንም

ችግር ወደ ፈለግነው ሥራ ለመግባት በሩን ሊከፍትልን ይችላል።

ከዚህም ባለፈ ሁኔታ እንደ ክርስቲያን ባልና ሚስት የተበደርነውን ብድር

እንደ ባለ ዐደራ በአግባቡ መክፈል እንዳለብን አሰቀድመን ማወቅና መረዳት

በጣም አስፈላጊ ነው። ከዚህም ባለፈ ለቤት ሆነ ለምናደርጋቸው ነገሮች

ሁሉ ከፊት ለፊት ገንዘብ የመክፈል እና የመግዛት ባሕልን ልናዳብር ይገባል።

ዕዳ ውስጥ መግባት በምንኖርበት አገር ውስጥ በጣም ቀላል ከሆኑት ነገሮች

ውስጥ አንዱ ነው። ዕዳ ብዙ ጊዜ ቤታችን ድረስ ፈልጎን ነው የሚመጣው፤

ይህም የሚሆነበት ምክንያት ለእኛ አዝነው ወይም ሊጠቅሙን ሳይሆን

እኛን በቀላሉ በዕዳ ውስጥ በመክተት በየወሩ በጣም ትልቅ አራጣ እና የዘገየ

ክፍያ ቅጣት በመሰብሰብ ትልቅ ትርፍን ማትረፍ ዋናውና በጣም አብዝተው

የሚሰሩበት የአሰራር ዘይቤ ስለ ሆነ ብቻ ነው። ዕዳ ውስጥ መግባት ቀላል

ነው፤ ከዕዳ ውስጥ መውጣት ግን ብዙ ዋጋ ያስከፍላል።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 185

Page 186: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

14 ክፍል

የመወያያ ጥያቄዎች

እነዚህን ጥያቄዎች በቡድናችሁ ውስጥ ስትመልሱ የባሎቻችሁን እና

የሚስቶቻችሁን ስሜት እንዳትጎዱ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እናሳስባን።

1. የቤታችሁ ዕዳ ክፍያ ከገቢያችሁ 40% የሚያክለውን ይወስዳል?

2. ልትገዙ/ልትከራዩ ያሰባችሁት ቤት ከገቢ አቅማችሁ ጋር

ይስማማል?

3. አላስፈላጊ ዕዳዎች ውስጥ ገብታችሁ የተማራችሁት ትምህርት

ካለ ለቡድናችሁ አካፍሉ።

186 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 187: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

ባዶ ጎጆ (Empty nest)

15 ክፍል

የጋብቻ ሕይወት ትርጉም እና ዓላማ

ወላጆች ልጆቻቸው አድገው ከቤት ሲውጡ የሚኖሩት የብቸኝነት ዘመን

ዓላማዎች

❖ ባዶ ጎጆ የሚባለው ወቅትና ጊዜ ባልና ሚስት የበለጠ

እርስ በእርስ የሚቀራረቡበትና ጌታን የሚያገለግሉበት

የሕይወት ዘመን መሆን እንደሚችል ለማስገንዘብ፤

❖ በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ልጆች አድገው በትምህርት ወይም

በሥራ ምክንያት ከቤት ሲወጡ በባልና በሚስት መካከል

ሊፈጠር ይችላል ተብሎ የሚታሰበውን ባዶነት ለማሳየት፤

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 187

Page 188: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

15 ክፍል

❖ ከወዲሁ ችግሩን ለማስገንዘብና የመፍትሔ ሃሳቦችን ለማስተናገድ

ነው።

መግቢያ

በምዕራባውያንና በእኛ መካከል የባዶ ጎጆ ችግር ዓውዱ ይለያያል።

በምዕራባውያን ከልጅነት አስከ ሽምግልና በብዙ የሰዎች ኑሮ በግላዊነት

(individualistic) ላይ ያተኮረ ነው። ትኩረታቸው ከራሳቸው ካለፈ ደግሞ

በልጆቻቸው ዙርያ ይሆናል። ስለዚህ የባልና ሚስት ሕይወት በራሳቸውና

በልጆቻቸው ዙሪያ ነው የሚሽከረከረው። ልጆቹ ከቤት ሲወጡ በተለይ

በብዙ ቤተሰብ መካከል እንደሚታየው ዓላማቸው ልጆችን ማሳደግ፣ ስለ

ልጆች መወያየት፣ ስለ ልጆች ማሰብ ብቻ ከሆነ ልጆች ከመካከል ሲወጡ

ባልና ሚስት ዓላማ የማጣት ስሜት ውስጥ ይገባሉ።

የመወያያ ጥያቄ

❖ በህብረተሰባችን ባዶ ጎጆ ለየት ያለ ዓውድ (context) አለው

ብለው ያምናሉ? ከሆነስ እንዴት?

❖ በባዶ ጎጆ ምክንያት በትዳራቸው የተጎዱ ወይም ደግሞ ባዶ ጎጆ

መሆናቸው እንዲያውም የበለጠ አቀራርቦአቸዋል የሚሉት

ቤተሰብ ካለ ለኅብረቱ በምሳሌነት አጫውቱ።

188 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 189: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

15 ክፍል

የጥናቱ ይዘት

እግዚአብሔር ለሰዎች በምድር ላይ የምንኖርበትን የዕድሜ ዘመን ገድቧል።

ሰሎሞን በመጽሐፉ እንደተናገረው፤

ለሁሉ ዘመን አለው፥ ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ

ጊዜ አለው። ለመወለድ ጊዜ አለው፥ ለመሞትም ጊዜ

አለው፤ ለመትከል ጊዜ አለው፤ የተተከለውንም ለመንቀል

ጊዜ አለው … ለመውደድ ጊዜ አለው፤ ለመጥላትም ጊዜ

አለው፤ ለጦርነት ጊዜ አለው፥ ለሰላምም ጊዜ አለው።

ለሠራተኛ የድካሙ ትርፍ ምንድር ነው? መክ. 3፥1-9

በዚህ ሥፍራ ላይ ጸሐፊው ስለ ሰዎች ዘመንና የሕይወት ወቅት እንዴት

እንዳሰፈረው መመልከቱ በቂ ነው። የትናንትናው ሁኔታችን ትምህርታዊ

ከሆነ፣ የዛሬን ኀላፊነታችንን በመወጣት፣ በፊታችን ያለውን ዘመን

እግዚአብሔር ቢፈቅድና ብንኖር ብሎ ማቀድ ከመንፈሳዊነት መጉደል

አይደለም። በተቃራኒው ኀላፊነት እንዳለው ሰው መዘጋጀታችን ለእኛ

ጥቅም ለእግዚአብሔር ክብርን ያመጣል። ብዙ ጊዜ ልጆች ከቤት ከወጡ

በኋላ ይህንን ወይም ያንን እናደርጋለን ብለው ያቀዱ ሰዎች ጊዜው ሲደርስ

ሳይጨናነቁ በዓለም ኑሮአቸውን ሲቀጥሉ ያልተዘጋጁ ሰዎች ግን ራሳቸውም

በልጆቻቸውም ላይ ውጥረት ሲፈጥሩ ተስተውለዋል። ነብዩ ኤርሚያስ ስለ

ሰዎች ልጆች ጊዜን ወይም ደግሞ ዘመንን አለማስተዋል ሲናገር፤ “ሽመላ

በሰማይ ጊዜዋን አውቃለች፤ ዋኖስና ጨረባ ዋልያም የመምጣታቸውን

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 189

Page 190: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

15 ክፍል

ጊዜ ይጠብቃሉ፤ ሕዝቤ ግን የእግዚአብሔርን ፍርድ አላወቁም።” (ኤር.

8፥7)

በዚህ ክፍል የእግዚአብሔር ቃል የሚነግረን አእዋፍ እንኳን ጊዜን ሲያውቁ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጊዜያቸውን አለማወቃቸውን ያሳየናል። የልጅነት

የጉብዝና፣ የትዳር ብሎም ልጆችን የማሳደግ ጊዜ እንዳለ ሁሉ ልጆች ከቤት

የሚወጡበት ጊዜም ሰዓቱን ጠብቆ ይመጣል። ታዲያ እግዚአብሔር

ቢፈቅድ በዚያን ጊዜ (ባዶ ጎጆ) ብሎ አሁኑኑ ዝግጅት ማድረግ መንፈሳዊ

አለመሆን አይደለም።

ተግዳሮቶች

1. ስለ ባዶ ጎጆ ጊዜ ማሰብ አለመለመዱ፤

2. ልጆቻችንም ከወዲሁ ስለ ባልና ሚስት ጊዜ አለማስተማር፤

አልፎ ተርፎ ደግሞ አንድ ቀን ራሳቸውን ችለው እንዲወጡ

አለማዘጋጀት፤

3. ማኅበራዊ ኑሮ በራሱ ትልቁ እሴታችን (value) ቢሆንም በአንጻሩ

ደግሞ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚያመጣ አለመገንዘብ፤

4. የሕይወት ዓላማ ልጆች ከማሳደግ ያለፈ መሆኑን አለመገንዘብ፤

5. በባዶ ጎጆ ጊዜ ከሚፈጠረው የብቸኝነት ስሜት የተነሳ ድብርት

(depression) ውስጥ መግባት፣ ወዘተ ናቸው።

190 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 191: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

15 ክፍል

የመፍትሔ ሓሳብ

1. ከመጀመሪያውኑ ባልና ሚስት ትዳራቸውን ማስቀደም ዓላማ

ማድረግ ይኖርባቸዋል። በትዳር ሕይወታቸው እያደጉ ለመሄድ

ሁል ጊዜ ለራስ ጊዜ መጠንቀቅ ተገቢ ነው። ጊዜ አንዱና ትልቁ

የፍቅር መግለጫ መንገድ ነውና። ሰው ለሚወደው ነገር ጊዜውን

ይሰጣል። ከትዳራችን በላይ ለልጆቻችን ብቻ ጊዜ የምንሰጥ

ከሆነ እርስ በእርስ እንደ ባልና ሚስት አብረን ማደግ አንችልም።

2. እግዚአብሔር በመጀመሪያ ትዳርን ሲመሰርት በባልና በሚስት

ነው። ልጆች የዚህ ትዳር ውጤት ናቸው። ለትዳር ሳይሆን

ለልጆች ቅድሚያ መስጠት ማለት ዛፉን ትቶ በቅርንጫፍ ላይ

እንደ መንጠልጠል ይሆናል። በሌላ አገላለጽ ልጆች ግንኙነት

የሚያጣፍጡ ቅመም እንጂ ዋናው ትዳራችን መሆኑን አንዘንጋ።

3. ልጆች ብቻ ሳይሆኑ ጓደኞችም የራሳቸው ቦታ እንዳላቸው ማወቅ

ያስፈልጋል። ብዙ ጊዜ በእኛ ኅብረተሰብ መስመር (bound-

ary) እንደሚገባ አይታይም። ካልተጠነቀቅን በስተቀር ባልና

ሚስት የራሳቸውን ጊዜ ለሌሎች ጓደኞቻቸው ክፍት በማድረግ

ግንኙነታቸው ሊጎዳ ይችላል።

4. በባሕላችን የባልና የሚስት ቤተሰብ ከባልና ከሚስት ጋር ያው

አንድ እንደ ሆኑ ነው የሚታሰቡት። ሆኖም ይህም ቅርበት

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 191

Page 192: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

15 ክፍል

መስመር ካልተበጀለት ወይም በትክክለኛ መንገድ ካልተያዘ ዞሮ

ዞሮ የባልና የሚስትን ጊዜ እንደሚሻማ ማስተዋል ያስፈልጋል።

በጥቅሉ ባልና ሚስት ለራሳቸው ጊዜ ከወሰዱ በኋላ ብቻ ነው

በጋራ ለልጆች፣ ለቤተሰብና ለጓደኞች ቤታቸውን መክፈት

የሚኖርባቸው። ስለዚህ ባልና ሚስት ትዳራቸውን ዋጋ

ከሚያስከፍል ማኅበራዊ ግንኙነቶች ሊጠብቁ ያስፈልጋል።

5. ባልና ሚስት በባዶ ጎጆ ጊዜ እንደ እነርሱ ካሉ ጓደኞቻቸው

ጋር ኅብረት በመፍጠር (support group) ስለሚገጥማቸው

ተግዳሮት መወያየትና መመካከር ጠቃሚ ነው።

6. ባልና ሚስት ልጆች ከቤት ከወጡ በኋላ ጊዜያቸውን በምን ላይ

እንደሚያውሉ አስቀድመው ማቀድ ለዚያም ጊዜ መዘጋጀት

ይኖርባቸዋል።

7. ባልና ሚስት ይህ ጊዜ ከእግዚአብሔር የተሰጣቸው የጸጋ ዘመን

እንደ ሆነ እና ልጆች በመውለድና በማሳደግ የከፈሉትን ዋጋ ፍሬ

የሚያዩበት ጊዜ እንደ ሆነ በመገንዘብ ዘመኑን በደስታ መቀበል

(embracing the season) ይገባቸዋል።

192 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 193: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

15 ክፍል

የማጠቃለያ ምክር

በትዳር ውስጥ በዋናነት መንከባከብና ማሳደግ ያለብን የባልና የሚስትን

ግንኙነት ነው። ምክንያቱም በትዳር ውስጥ ልጆች ሊኖሩም ላይኖሩም

ይችላል። በልጆች ደግሞ ከተባረክን ጊዜ ጠብቀው እነርሱ የራሳቸውን ጎጆ

የሚመሰርቱበት ወቅት ይመጣል። ባልና ሚስት ዓላማ ያደረጉት በልጆች

ላይ ብቻ ከሆነ ልጆቹ ሲወጡ ያልተጠበቀ ባዶነት፣ ዓላማ ማጣት፣ ግራ

መጋባትና ብሎም የትዳር መፍረስ ምክንያት ሊሆን ይችላል። ከወዲሁ ግን

ልጆቻችን የባልና የሚስት ጤነኛ ግንኙነት ተጠቃሚ ቢሆኑ ይሄ ችግር

ላይኖር፣ ቢኖርም መጠኑ የቀነሰ ይሆናል። ከወዲሁ ይህንን ችግር አውቀን

ከተጠነቀቅንና ከተዘጋጀን ባዶ ጎጆ በሚባለው ሰዓት ላይ በነጻነትና በጋራ

ለእግዚአብሔር መንግሥት ሥራ የምንሰማራበት ወቅት ሊሆን እንደሚችል

እንወቅ።

የቤት ሥራ

1. በዚህ ወር እንደ ባልና ሚስት አብራችሁ በመሆን ስለ ረዥም

ጊዜ እቅድ ተወያዩ።

2. ባዶ ጎጆ ብዙ ጊዜ ዕድሜያቸው ከ50 ዓመት በኋላ ለሆኑ

ሰዎች የሚመጣ ክስተት ነው። በባዶ ጎጆ ዘመን ምን ማድረግ

እንዳለባችሁ ተነጋገሩ።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 193

Page 194: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

16 ክፍል

የሥርዓተ ጾታ ትምህርት እና

ተግዳሮቱ

ዓላማዎች

❖ የተሳሳቱ ጾታዊ ግንኙነቶች የሞራላዊ እና የመንፈሳዊ

ውድቀቶች ውጤት መሆናቸውን እና ይህንን ለማረም

ምን መደረግ እንዳለበት ያውቃሉ።

❖ ክርስቲያናዊ፣ትክክለኛ የሆኑ ጾታዊ ግንኙነቶች እና

የወንድና ሴት ግንኙነት ምን መምሰል እንዳለበት

ያውቃሉ።

❖ የጾታ ትምህርት በቤተሰብ ግንኙነት ላይ አሉታዊ

ተጽእኖ እንዳያመጣ በምን መልኩ ትምህርቶቹን

መቋቋም እንደሚገባ ይገነዘባሉ።

194 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 195: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

16 ክፍል

መግቢያ ከቤተ ክርስቲያን ውጪ የሥርዓተ ጾታ ትምህርት በጣም ሠፊ የሆነ እንደ

ባሕሉ እና ማኅበረሰቡ ብዙ ዝርዝር ጉዳዮች ያሉት ለረጅም ጊዜ በከፍተኛ

ደረጃ በልዩ ልዩ መስክ የሚሰጥ የትምህርት ዓይነት ነው። በተጨማሪም

በተለያዩ ቦታዎች በገጠርም ሆነ በከተማ በተለያዩ የእውቀት ደረጃ ላላቸው

ሰዎች በሴሚናር መልክ በመሰጠት ላይ ያለ ሲሆን በጾታ ምክንያት የሚደርሱ

ልዩነቶችን፣ በደሎችን፣ ያልተመጣጠነ የሀብት ክፍፍል እና የትምህርት

ልዩነትን ያካተተ ነው። በዚህ ዓይነት ቅኝት የሚሰጥ ትምህርት በብዙ መልኩ

የሚጠቅም ቢመስልም ሚዛኑን ባልጠበቀ መልኩ ስለሚሰጥ ለብዙዎች

ትዳር ጠንቅ እየሆነ እንደመጣ እና በብዙ መድረኮችም መጽሐፍ ቅዱስን

ለመቃወም መሣሪያ እስከ መሆንም ሲደርስ ይታያል።

በሌላ በኩል እግዚአብሔር ወንድና ሴት አድርጎ የፈጠረውን ተፈጥሮ

ለማጥፋት ትውልድም በዚህ ጉዳይ ላይ ጥያቄ እንዲኖረው በሚያደርግ

ሁኔታ ትምህርቱ የጾታ ማንነትና የተቃራኒ ጾታ ግንኙነትን እንደ ጾታ መብት

በማካተት በሰፊው እየተሰራበት እንዳለ ይስተዋላል። ይህንንም እኛ አማኞች

የእግዚአብሔር ቃል እርስ በእርስ ስላለን ግንኙነትና ዋጋ፣ ስለ ጾታ ምንነትና

ስለ ተቃራኒ ጾታ ግንኙነት ምን እንደሚል በበቂ ሁኔታ ተረድተን እኛና

ቤታችንን የክርስቶስን ቤተ ክርስቲያን በማዳን እንዲሁም ደግሞ ሌሎችን

ከዚህ ጥፋት ልናስመልጥ እንድንችል ትምህርቶቹን በማወቅና

በእግዚአብሔር ቃል መመዘን ይገባናል። በዚህ ጥናት በመሠረታዊ የሥርዓተ

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 195

Page 196: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

16 ክፍል

ጾታ ትምህርት ውስጥ በስፋት የሚነሱ ሁለት ዋና ዋና ሐሳቦች አንስተን እንደ

እግዚአብሔር ቃል እንወያያለን። እነዚህም የጾታ እኩልነትን፣ የጾታ ማንነት

እና ከዚህ ጋር የሚዛመደው የጾታ ጥቃትን የሚመለከቱ ጉዳዮች ናቸው።

1. የጾታ እኩልነት

ውይይት አንድ

1. እንደ አማኝ የጾታ እኩልነት የሚለውን ሐሳብ እንዴት ይረዱታል?

አስተሳሰቡ በክርስትና ሕይወት እና በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት

ላይ የሚያሳድረውን ተጽእኖ አንስታችሁ ተወያዩ። የእኩልነት

መለኪያው ምንድን ነው?

ትርጉም

ስለ ጾታ አኩልነት ምንነት ለመረዳት ቀላል የሆነ ትርጓሜ መስጠት

ያስፈልጋል። ትርጓሜ ላይ የምንደርሰው ስምምነት የሐሳቡን ይዘት እና

የጥናቱን ዓውድ ለመረዳት እጅግ አጋዥ ነው። የጾታ እኩልነት ማለት

ሁለቱም ጾታዎች (ወንድና ሴት) በእግዚአብሔር ፊት ያላቸውን እኩል ዋጋ

ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ፣ እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤

በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አደርጎ ፈጠራቸው (ዘፍ.

1÷27) በማለት የወንድና ሴት በእግዚአብሔር መልክ መለኪያ በእኩልነት

የተፈጠሩ ነገር ግን የተለያየ ዓላማ ያነገቡ መሆናቸውን ይጠቁመናል። ስለ

ጾታ እኩልነት ስናወራ መሠረታዊ እይታችን በዚህ ቃል የተመሠረተ መሆን

ይኖርበታል።

196 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 197: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

16 ክፍል

“አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፣ባርያ ወይም

ጨዋ የለም ወንድም ሴትም የለም ሁላችሁ በክርስቶስ

ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።” (ገላ. 3÷28)

ውይይት ሁለት

አንዳንድ የሥርዓተ ጾታ አስተማሪዎች መጽሐፍ ቅዱስ የወንዶች የበላይነትን

እና ጭቆናን የሚያበረታታ እንደሆነ አድርገው ሲያስተምሩ

ከሚጠቅሱዋቸው ጥቅሶች መካከል ኤፌ. 5÷24፤ ቈላ. 3÷18፣ ቲቶ 2÷4፤

ወዘተ. ይገኙበታል። ሚስት ለባሏ እንድትገዛ የሚናገሩ ክፍለ ምንባባት

የሴትን ጫና ለማብዛት እንደ ተጻፉ ይናገራሉ።

ኤፌ. 5÷21-26፤ ቈላ. 3÷18 -25፤ 1ኛ ቆሮ. 13 እና ቲቶ 2÷4 ከተነበበ በኋላ፤

እውን የእግዚአብሔር ቃል የወንድ የበላይነትን ወይም እኩልነትን (Gen-

der inequality) ያስተምራልን? በሰው ልጆች ዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ

የሚታወቁ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን በመዘርዘር ተወያዩ። ከላይ

ያሉትን ጥቅሶች በደንብ ተረድቶ የሚኖር ቤተሰብ አንዱ ሌላው ላይ ጫና

እንዲያበዛ ሊያበረታታ እንደማይችል መረዳት አያዳግትም።

የሰው ዘር ዋጋ

እግዚአብሔር የሰውን ዘር ሁሉ እኩል ዋጋ እንዲኖረው አድርጎ በእነዚህ

ቃላት ፈጠረ። “ስለዚህ እግዚአብሔር ሰውን በራሱ መልክ ፈጠረው፣

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 197

Page 198: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

16 ክፍል

በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው። ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው” (ዘፍ.

1÷27)። የሰውን ልጅ በራሱ አምሳል በመፍጠር እግዚአብሔር እሴታችንን ለእርሱ

ባለን አምሳል ላይ የተመሠረተ አደረገ። ማንኛውም ሰው ከሌላው የሰው

ልጅ ጋር በተፈጥሮ እኩል የሆነ እኩልነት አለው፤ ምክንያቱም ማንም

ከሌላው የበለጠ ወይም ያነሰ ሆኖ አልተፈጠረም። እግዚአብሔር

ለኀጢአታችን ቅጣትን እንዲወስድ አንድያ ልጁን ወደ ዓለም ሲልክ (ዮሐ.

3÷16-18) ዋጋችንን ለዘላለም አረጋገጠ (2ኛ ቆሮ. 5÷21)። በዚህ ምክንያት

ብቻ እያንዳንዱ ሰብዓዊ ፍጡር በእግዚአብሔር ፊት ውስን እና እኩል ዋጋ

አለው።

“በዚህም የግሪክ ሰው አይሁዳዊም የተገረዘም

ያልተገረዘም አረማዊም አስኩቴስም ባሪያም ጨዋ

ሰውም መሆን አልተቻለም ነገር ግን ክርስቶስ ሁሉ ነው

በሁሉም ነው።” (ቈላ. 3÷11)

“አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም ባሪያ ወይም ጨዋ

ሰው የለም ወንድም ሴትም የለም ሁላችሁ በክርስቶሰ

ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁ።” (ገላ. 3÷28)

198 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 199: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

16 ክፍል

ከእነዚህ ሁለት ክፍለ ምንባባት ሰው ሰራሽ የሆኑት የዘር፣ ጎሳ እና የጾታ

መበላለጥ በክርሰቶስ ድነትና ዳግም በመወለድ እኩልነትን ያውጃሉ። ሰው

ሰራሽ የዘር፣ ጎሳ እና የጾታ እኩልነትን ያፈርሳሉ እናም ለድነት በክርስቶስ

የሚያምኑ ሁሉ እኩል መሆናቸውን ያውጃሉ። እኛ ክርስቲያኖች መለኪያችን

ክርስቶስ መሆኑን ስንረዳ በእኩል እንደ ተፈጠርን እናውቃለን። እኛ ግን

የአካል ክፍላችን እኩል ዋጋ ያላቸው ነን (ኤፌ. 5÷30፤ 1ኛ ቆሮ. 12÷27)።

ስለዚህ በአካል፣ በዘር፣በአእምሮ፣ ወይም በማኅበራዊ እናኢኮኖሚያዊ

ልዩነቶች ላይ በመመስረት ሌላውን ሰው ለማቃለል ወይም መጉዳት ሁልጊዜ

ስህተት ነው (ያዕ. 2÷1-13)።

እኛ ክርስቲያኖች እኩልነትን የሰው ልጅ ትከሻ - ለትከሻ በመለካት

የምናረጋግጠው አይደለም።በአካል፣ በአእምሮአዊ፣ በስሜታዊ፣

በኢኮኖሚያዊ እና በእያንዳንዱ ምድራዊ ንጽጽር የሰው ልጆች እኩል

አይደሉም። አጭር፣ ረጅም፣ ቀጭን፣ ወፍራም፣ ደካማ፣ ብልህ፣ ሀብታም፣

ድሃ፣ ወዘተ. የሚሉ ክፍፍሎች የሰው ልጆች በብዙ ነገር እኩል አለመሆናቸውን

ያስረዳሉ። እነዚህ ሁሉ ልዩነቶች ቢኖሩም የሰውን ዋጋ አያሳዩም። አማኞች፣

ሁሉም ሰዎች በዋጋቸው በክርስቶስ ፊት እኩል ናቸው።አብዛኛው የሰው

ልጅ እኩል አለመሆን በኀጢአት ውጤት ምክንያት ነው። በሽታ፣ ዘረኝነት፣

ድኅነት፣ ጉዳት እና ብልሹነት ሁሉ ይህ ዓለም በኀጢአት ምክንያት

በመጣው እርግማን ምክንያት ነው (ዘፍ. 3÷16-19፤ መዝ. 107÷34፤ ሮሜ

8÷22-23)።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 199

Page 200: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

16 ክፍል

ውይይት ሦስት ❖ ጥንዶች በኅብረት ስንኖር በምናደርገው ዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ

በጾታ ማንነታችን ላይ የሚገለጠው ጸጋችን ሊበላለጥ የሚችልበት

አጋጣሚ እንዳለ አስተውላችሁ ታውቃላችሁ? ቤተሰብን እንደ

አንድ መንፈሳዊ ተቋም በማሰብ ለእያንዳንዳችን የተሰጠንን ጸጋ

በማንሳት እንወያይበት።

ውይይት አራት ❖ በጥንዶች ሕይወት ውስጥ መደማመጥ፣ መገዛት፣ ጥበብ፣ ፍቅር፣

መተሳሰብ ሚዛናቸውን ጠብቀው እንዲጎለብቱ ለማድረግ

ከጥንዶች ምን ይጠበቃል ብለው ያስባሉ?

ውይይት አምስት

❖ ጥንዶች ጾታን መሠረት ያደረገ ልምምዳችን ምን እንደ ሆነ

በግላችን በማሰብ አንዳችን ለሌላችን አገልጋይ ከመሆን አኳያ

ሊስተካከሉ የሚገባቸው፣ ጫናን ሊያስከትሉ ይችላሉ የምንላች

ውን ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር በየግል ከተወያያን በኋላ ተስማ

ምተን ይጠቅማል የምንለውን በቡድን እንወያይበት።

200 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 201: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

16 ክፍል

ውይይት ስድስት ❖ በባሕል ተጽእኖ ውስጥ ላሉ ክርስቲያን ቤተሰቦች ወይም የቃሉን

እውቀት ካለመረዳት የሚፈጸሙ ጾታዊ ጥቃቶች እንዳያጋጥሙ

ምን መደረግ አለበት ብለው ያስባሉ?

ውይይት ሰባት

❖ አንዳንድ የሥርዓተ ጾታ ትምህርት አስተማሪዎች የፍቅር

ግንኙነትን (Love making) በሚመለከት መጽሐፍ ቅዱስ

ሴቶች የወንዶች ፍላጎትን ማስፈጸሚያ አድርጎ ብቻ

እንደሚያስቀምጥ በውድቀት ጊዜ ያለውን (ዘፍ. 3÷16)

ነጥሎ በመጥቀስ ያቀርባሉ። በተጨማሪም የቤት ውስጥ

የወሲብ ጥቃት በባሎች እንደሚፈጸም ሲያስተምሩ ይሰማል።

ይህ ትምህርት በስፋት የሚሰጥ ከመሆኑ አንጻር ክርስቲያን

ቤተሰቦች ከዚህ ጥቃት ነጻ ይሆናሉ ብሎ መገመት አዳጋች

ስለሚሆን በዝርዝር ተወያዩ።

ውይይት ስምንት ❖ 1ኛ ቆሮንቶስ 7÷2-5 በማንበብ ስለ ባልና ሚስት ጾታዊ ግንኙነት

መሆን ስለሚገባው ሥርዓት አንስታቸሁ ተወያዩ። ይህ

ባልሆነበት ጊዜ በባልና ሚስት መካከል የሚኖረውን ግንኙነት

እንደሚያሻክር፣ ለግጭት መንሥዔ እና በሂደትም ትዳርን

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 201

Page 202: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

16 ክፍል

የሚያናጋ መሆኑን በማንሳት ተወያዩ። ጥንዶች በቤታቸው

ስላላቸው ልምምድ ተወያይተውበት ፍቃደኛ ከሆኑ ለቡድናችሁ

ሐሳባቸውን ያካፍሉ።

መጽሐፍ ቅዱስ ለሁሉም የሰው ልጆች ማንነት እኩል ዋጋ ይሰጣል።

በተጨማሪም እኩልነት እንደ ተጠበቀ ሆኖ ወንድና ሴት በጾታ ዓላማቸው

የተለያየ ቢሆንም ግልጽ የሆነ ኀላፊነት/ተልዕኮ በቤተሰብ እና በቤተ

ክርስቲያንም ተሰጥቷቸዋል። ወንዶች እና ሴቶች ጾታቸው ቢለያይም

ተደጋጋፊ የሆኑ ሚናዎች በቤተሰብ ውስጥ (ኤፌ. 5÷21-33) እና በቤተ

ክርስቲያን ተሰጥቷቸዋል (1ኛ ጢሞ. 2÷12)። አማኞች የተለያዩ መንፈሳዊ

ስጦታዎች ተሰጥቷቸዋል (1ኛ ቆሮ. 12)። እዚህ ላይ እንደ ተመለከተው

ሰዎች የተለያዩ ሚናዎች ወይም የተለያዩ ስጦታዎች ማግኘታቸው እኩል

አለመሆናቸውን ለማመልከት አይደለም። ይልቁንም፣ የእግዚአብሔር ጥበብ

እና የፈጠራ ኀይል ማሳያ ነው። ኤፌሶን 2÷10 በኢየሱስ ላመኑ ሁሉ

እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጃቸውን መልካም ሥራዎች ይናገራል።

ጾታዎች በእግዚአብሔር ፊት እኩል ናቸው እናም ሁለቱም

በአክብሮት መያዝ አለባቸው።

202 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 203: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

2. የጾታ ማንነት ጥያቄ እና ተዛማጅ ውድቀቱ

16 ክፍል

የሰው ልጅ ተወልዶ ይህንን ዓለም ሲቀላቀል ሰዎች ወንድ ወይም ሴት መሆኑን

በመጠየቅና በማጣራት ማወቅ ይፈልጋሉ። ሥርዓተ ጾታ በመሠረታዊነት

የተሰጠንን የወንድነትና የሴትነት አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ስጦታ የሚያካትት

ሲሆን ከዚያም ዘለግ ብሎ ሲታይ ከጾታዊ እይታ ውጪ ያሉ ግንኙነቶችንም

ይመለከታል። አዲስ ጨቅላ ሕጻን ስም ሲወጣለት፣ ሲለብስ ወይም ሲያወራ

በሂደትም በዓለም እያደገ ሲሄድ ጾታዊ ዕድገቱን የሚወስኑና ተጽእኖ

የሚያሳድሩ በርካታ ጉዳዮች በመኖራቸው ከነዚህ ሁኔታዎች የመማር ዕድሉ

ከፍተኛ ነው። የተለያዩ ጾታዎች የእግዚአብሔር ጸጋዎች ከመሆናቸው

ባሻገር ተፈላጊ ናቸው። የጾታ ልዩነቶች መኖር እግዚአብሔር የሰጠንን

ብቁነት የሚወሰን አለመሆኑ በዚህ ክፍል ይዳሰሳል።

ሥርዓተ ጾታ የእግዚአብሔር ሐሳብ ነው። ሥርዓተ ጾታ በምድር ላይ

የመጀመሪያው ተቋም ቤተሰብ ከመመሥርቱ በፊት የተፈጠረ ታላቅ

የቤተሰብ መሠረት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ፣ “እግዚአብሔር ሰውን በመልኩ

ፈጠረ፣ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፣ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው”

ይላል (ዘፍ. 1÷27)። የጾታ ዓይነቶች፣ ወንድ እና ሴት ተደርጎ በእግዚአብሔር

ፈቃድና ዘላለማዊ ዕቅድ የተፈጠረ ነው። ከዚህ ቃል እንደምንረዳው

ጾታ የሚሠራ አይደለም። የሰው ልጅ ፈቅዶ ወይም ፈልጎ የሚሆነውም

አይደለም። ሰዎች በቀዶ ጥገና ወይም በሌላ መንገድ ከተፈጠሩበት የጾታ

ዓላማ ውጪ የሚፈጽሙት ድርጊት ሁሉ ኀጢአት ነው።

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 203

Page 204: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

16 ክፍል

በሥርዓተ ጾታ ላይ ያጋጠሙ ችግሮችና ፈተናዎች፡-

❖ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ፣

❖ ጾታን መቀየር፣

❖ አዲስ የጋብቻ ትርጓሜ መስጠት፣

❖ የሐሰት ትምህርት እየተበራከተ መምጣት፣

❖ በተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ ወስጥ የሚደረግ

“አዳፕሽን”፡፡

የሥርዓተ ጾታ ግንኙነት ብልሽቶች መንሥዔ፡-

❖ ኢኮኖሚና ያለ ዕቅድ የሚመራ ሕይወት

❖ የመንፈሳዊ ሕይወት መዳከም/መቀዛቀዝ

❖ ባሕል

❖ ፖለቲካ/አጉል ሥልጣኔ

❖ ቴክኖሎጂያዊ

መሠረቱ፤

የጾታዊ ግንኙነት ሥርዓቶች

“እግዚአብሔር አምላክም በአዳም ከባድ እንቅልፍን ጣለበት፤ አንቀላፋም።

ከጎኑም አንዲት አጥንትን ወስዶ ስፍራውን በሥጋ ዘጋው። እግዚአብሔርም

አምላክም ከአዳም የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት። ወደ አዳምም

አመጣት። አዳምም አለ፡- ይህቺ አጥንት ከአጥንቴ ናት ሥጋም ከሥጋዬ ናት፣

እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል” (ዘፍ. 2÷21-23)። ከዚህ የመጽሐፍ

204 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 205: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

16 ክፍል

ቅዱስ ክፍል አዳምና ሔዋን የሚኖራቸው ቤተሰባዊ ግንኙነት አመሠራረቱ

በጾታዊ ልዩነት ላይ የተመሠረተ መሆኑን ማየት ይቻላል። አዳምና ሔዋን

የተለያየ ጾታ ኖሯቸው የተፈጠሩና ታላቁን የጋብቻ ምሳሌ ለመጀመሪያ ጊዜ

ያሳዩ ባልና ሚስቶች ነበሩ።

እግዚአብሔር ሰውን ወንድና ሴት አድርጎ ሲፈጥር ለተለያየ ዓላማ እንደ ሆነ

በግልጽ ይነግረናል። ወንድን ለአባትነት፣ ሴትን ደግሞ ለእናትነት እንድትሆን

አድርጓል። ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል በሚስቱም ይጣበቃል፤ ሁለቱም

አንድ ሥጋ ይሆናሉ። ወንድን ለባልነት ሴትን ደግሞ ለሚስትነት እንድትሆን

አድርጓል። እግዚአብሔር ሰውን ወንድ እና ሴት አድርጎ ሲፈጥር የማይታካካ

ኀላፊነት እንዲላበሱ አድርጎ ፈጥሯል። ይህ የእግዚአሔር ሐሳብ ትክክል

ነው።

ውይይት ዘጠኝ

❖ ግብረ ሰዶማዊነት/ሌዚቢያንነት ኀጢአት ነው? ይህ ምን

ማለት ነው?

ለተፈጥሮ ወሲባዊ ግንኙነቶች የእግዚአብሔር ንድፍ የዕቅዱ አካል

ነው። ግብረ ሰዶማዊነት/ሌዚቢያንነት እግዚአብሔር ያቀዳቸውን ቅዱስ

የግብረ ሥጋ ግንኙነት ይቃረናል። ኀጢአት ብዙውን ጊዜ እግዚአብሔርን

አለመቀበል ብቻ ሳይሆን እንዴት እና ለምን እንደ ተሠራን መካድ ወይም

አለመቀበል ማለት ነው። በአንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት እና በአንዳንድ

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 205

Page 206: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

16 ክፍል

ሰዎች ዘንድ ዛሬ ተቀባይነት ያለው ቢመስልም እንኳን በእግዚአብሔር ዘንድ

ተቀባይነት የለውም።

በሰዶምና ገሞራ ከተሞች ውስጥ የወሲብ ኀጢአት በጣም ተስፋፍቶ ነበር።

(ይህ ሰዶማዊ የሚለው ቃል አመጣጥ ነው።) ማስጠንቀቂያዎች ቢኖሩም

ንስሐ ለመግባት አሻፈረን አሉ። እግዚአብሔር እነዚያን ከተሞች አጠፋቸው

እናም ለመጪው ትውልድ ሁሉ እንደ ማስጠንቀቂያ ተቆጠረ (ዘፍ. 18÷20-

21፤ 19÷4-5፤ 2ኛ ጴጥ. 2÷6)። በግብረ ሰዶማዊነት ላይ አንዳንድ ተጨማሪ

ጥቅሶች ይገኛሉ። እግዚአብሔር ለኀጢያተኛው የመጨረሻው እና ሉዓላዊ

ገዥ ነው። ግብረ ሰዶም በትእዛዙ ላይ ኀጢአት ነው፤ እርሱ በሕዝብ አስተያየት

ወይም በተታለሉ ወይም የሐሰት ቀሳውስት አይወሰንም። የማኅበረሰቦች

መለወጥ አምላክ ያወጣቸውን መሥፈርቶች አያስለውጡትም።

ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሉዋት ጋብቻ እንደ አንድ የጸጋው አካል በእግዚአብሔር የተሰጠ መሆኑን እና እርሱ

ከሰጠው ውጪ ሌላ ትርጉም እንደ ሌለው እናስተምራለን (ዘፍ. 2÷18-

24)። አማኞች ለመጽሐፍ ቅዱስ በመታዘዝ እና በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር

ሥር በመሆን በእግዚአብሔር የታሰበውን ሰላማዊ፣ ፍሬያማ እና የተሳካ

ጋብቻ ሊጀምሩ ይችላሉ (ዘፍ. 3÷16፤ 1ኛ ጴጥ. 3÷7)።

206 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 207: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

16 ክፍል

ውይይት አስር

❖ የጾታን ሚና እና ትርጉም ከመባዛት፣ ከዘር እና

ከእግዚአብሔር መለኮታዊ ዓላማ አንጻር እንዴት

እንደምትረዱት በዝርዝር ተወያዩ።

በሥርዓተ ጾታ ወንድ ሆኖ የተፈጠረ ሰው ዓላማው የወንድ ነው። ሴት ሆና

የተፈጠረች ሰው ዓላማዋ የሴት ነው። በወንድና በሴት መካከል ወይም

ከሁለቱ ወጪ የሆነ ጾታ የለም።

የሥርዓተ ጾታ፣ ጋብቻ እና ግብረ ሥጋ ግንኙነት

ጋብቻ አንድ ወንድና አንዲት ሴት ለሕይወት ብቸኛ ግንኙነቶች የሚኖሩበት

በእግዚአብሔር የተፈጠረ ተቋም ነው። ቅዱስ ጋብቻ በወንድ ሰው እና

በሴት ሰው መካከል የሚፈጸም፤ ከተጋቡ በኋላም ወንዱ ባል፣ ሴቷ ደግሞ

ሚስት በመሆን የሚኖሩበት ቃል ኪዳን ሲሆን ይኼውም በእግዚአብሔር

ዘንድ ተቀባይነት ያለው ብቸኛው የጋብቻ ዓይነት ነው።

በጋብቻ ውስጥ በተገቢ ሁኔታ ሰውነታችሁን ተጠቀሙ። የግብረ ሥጋ

ግንኙነት የታቀደው ለባልና ለሚስት ብቻ ነው። እንደ ምንዝር፣ ዝሙት፣

ግብረ ሰዶማዊነት/ሌዚቢያንነት፣ ብልሹ ሥነ ምግባር፣ ብልግና፣ ወሲባዊ

ተንቀሳቀሳሽ ምስሎች፣ ወሲባዊ ሥዕሎች፣ ማንኛውንም የአንድን ሰው

የግብረ ሥጋ ግንኙነት ወይም አለመግባባት ለመለወጥ የሚሞክሩ

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 207

Page 208: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

16 ክፍል

ማንኛውም ዓይነት የተለያዩ ብልግና ድርጊቶች በእግዚአብሔር ዘንድ

አስጸያፊ ናቸው (ዘሌ. 18÷1-30፤ ማቴ. 5÷28፤ ሮሜ 1÷26-29፤ 1ኛ ቆሮ.

5÷1፤ 1ኛ ተሰ. 4÷1-8)። ከእግዚአብሔር መለኮታዊ ሐሳብ እና ዓላማ ውጪ

የሚደረጉ የግብረ ሥጋ ግንኙነቶች በሙሉ ኀጢአት ናቸው። ወንድ እና

ወንድ፣ ሴት እና ሴት የሚፈጽሙት ጋብቻ ፍጹም ስህተት እንደ ሆነ

መጽሐፍ ቅዱሳችን አስረግጦ ይነግረናል።

የእግዚአብሔር ሐሳብ ላይ የተመሠረተ ሥርዓተ ጾታ ግንኙነት ለመልካም

ቤተሰብ መሠረቱ ነው። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥርዓተ ጾታን ማወቅና ተግባራዊ

ማድረግ በረከቱ ለራስ፣ ለቤተሰብ ከዚያም ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን የበዛ ነው።

እግዚአብሔር በወንድና ሴት መካከል ያለው ጾታዊ ልዩነት ለጋብቻ መሠረት

እንዲሆን አድርጎ ሠርቷል። የጋብቻና የቤተሰብ ተቋም ለእግዚአብሔር ልብ

ቅርብ የሆነ ተቋም ነው።

ውይይት አስራ አንድ

❖ በሥርዓተ ጾታ ላይ በየማኅበረሰቡ ያጋጠሙ ችግሮችና

ፈተናዎች ምን ምን እንደ ሆኑና ለጤናማ ሥርዓተ ጾታ

ግንኙነት ብልሽቶች መንሥዔ ይሆናሉ የምትሏቸውን ጉዳዮች

በቡድን አንስታችሁ ተወያዩ።

208 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 209: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

16 ክፍል

ውይይት አስራ ሁለት

❖ ዓለማችን ላይ ስንት ዓይነት ጾታዎች አሉ? አሁን ጎልተው

ከወጡት ግበረሰዶማዊነት እና ሌዚቢያኒዝም ውስጥ ያሉ

ወገኖቻችንን አሁን ካገኘነው ትምህርት አንጻር እንዴት

እናያለን?

ውይይት አስራ ሶስት

❖ በአሜሪካን አገር የትምህርት ሥርዓት ቢያንስ ልጆች ከመዋዕለ

ሕጻናት ጀምሮ ትክክለኛ የሆነውን የጾታ ማንነት ማወቅ በሚል

በእግዚአብሔር የተሰጣቸውን ጾታ እንዲጠራጠሩና እንዲጠይቁ

ያደርጋቸዋል። በዚህ ትምህርት እና ውስብስብ መዋቅራዊ ሁኔታ እንደ

ኢትዮጵያዊ ኮሚኒቲ፣ እንደ ቤተሰብ በልጆች ላይ ምን መሥራት

አለበት ብለው ያስባሉ?

ከኀጢያት ነጻ ስለ መውጣት/ስለ መዳን

ከኀጢአታችን እንድንመለስ የሚያግዘን የእግዚአብሔር ኀይል/

መንፈስ ተሰጥቶናል። ከአደንዛዥ ዕፅ ሱሰኝነት፣ ከግብረ ሰዶማዊነት/

ሌዚቢያንነት፣ ከብልግና ምስሎች ወይም ከሌላ ኀጢአት መውጣት ሁል

ጊዜ ቀላል አይደለም። ግን እግዚአብሔር መንገዱን ያዘጋጃል። ክርስቲያኖች

ንስሐ ለመግባት የሚፈልጉ እና በተፈጥሮ ዕቅዱም ለመኖር ወደ መንግሥት

“መውደድ” አለባቸው። የአምላክ ቃል ግብረ ሰዶማዊነት ከተፈጥሮ ውጭ

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 209

Page 210: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

16 ክፍል

የሆነ፣ አስጸያፊ፣ ዝሙት፣ መጥፎ ፍቅርና በእርሱ ላይ ትልቅ ኀጢአት እንደ

ሆነ ይናገራል። ከጋብቻ ውጭ የሚደረግ ማንኛውም የግብረ-ሥጋ ግንኙነት

ምንዝር ነው ይላል (ግብረ-ሰዶማዊ ወይም ግብረ-ሰዶማዊነት)። የግብረ

ሥጋ ግንኙነት በጋብቻ ውስጥ በወንድና በሴት መካከል መሆን አለበት።

በተወሰኑ አብያተ-ክርስቲያናት ውስጥ የተመሳሳይ ጾታ ያላቸውን ግንኙነቶች

ልክ እንደ ሕጋዊ የክርስቲያን ግንኙነት ዓይነት እንዲቀበሉ እና እንዲደግፉ

የሚደረጉትን ግፊቶች በመቃወም እና እንደዚህ ባሉ ግንኙነቶች ውስጥ

ላሉት ሰዎች ቤተክርስቲያናችን ይህንን ተቃርኖ ለማስተካከል በጸሎት

ዘወትር ትቆማለች።

ውይይት አስራ አራት

✓ ለሥርዓተ ጾታ ተገዥ ለመሆን ምን መደረግ አለበት?

በዝርዝር ተወያዩ።

❖ ወቅቱን ያልጠበቀ ግንኙነት አለማድረግ

❖ ለቅዱስ ጋብቻ የተመሠረተ ጾታዊ ግንኙነት ማድረግ

❖ ቅዱስ የሆነ ግንኙነት (Holly relationship)

❖ በጊዜ ትዳር መመስረት

❖ የተነቃቃ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ያለው ትዳር

❖ ታማኝነት፡፡

210 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ

Page 211: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

16 ክፍል

ማጠቃለያ

በዘመናችን መልካም እና ለሰዎች መብት የቆሙ የሚመስሉ፣ ያላሳከከን ቦታ

የሚያኩ፣ ከእግዚአብሔር ቃል ውጭ የሆኑ ብዙ ትምህርቶች አሉ። እነዚህ

ትምህርቶች በቤታችን ውስጥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ያሳደግነውን

ንጽሕና፣ ትሕትና፣ ፍቅር፣ መተሳሰብ እና ሥርዓት የተሞላውን ማንነት

ቀስ በቀስ የሚያስቀይሩ እና በሂደትም ለትዳራችን መናጋት መንሥዔ የሚሆኑ

ናቸው። ማንኛውም ትምህርት ሲመጣ አንደኛ እንደ እግዚአብኅር ቃል

መመዘን ሲኖርብን፣ በሁለተኛ ደረጃ ሐሳባችንን የሚያበላሽ ስለ መሆኑ እና

በትዳር ግንኙነታችን ላይ ጤናማ ስሜት ሊፍጥር ስለ መቻሉ፣ እንዲሁም

እግዚአብሔር ትውልድን ለመተካት ያለውን ዓላማ ማሳካቱን ልንፈትሽ እና

ልናረጋግጥ ይገባል።

በዋናነት በዚህ ጥናት ላይ በጾታ ትምህርት ላይ የሚታዩ በሠፊው የሰውን

ሐሳብ እየበረበሩ የመጪውን ትውልድ አእምሮ እየወሰዱ ያሉትን የጾታ

ማንነት እና የጾታ ግንኙነቶችን ጤናማ ባልሆነ ሁኔታ እያዛቡ የሚገኙትን

ትምህርቶች በመግለጽ ለማስታወቅ ጥረት ተደርጓል። ወንድና ሴት

በፈጣሪያቸው ፊት ሙሉ ተደርገው ለተለያየ ጾታዊ ዓላማ መፈጠራቸው

ሲገባን፣ በወንድና ሴት መካከል እንዲፈላለጉ ፍላጎቱን ያስቀመጠው ጌታ

ራሱ መሆኑን ስንረዳ፣ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በጌታ ፊት ፍጹም ኀጢአት

መሆኑን አውቀን ስንረዳ፣ ራሳችንንና ትውልዱን ከተመሳሳይ የጾታ ጋብቻ

ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ 211

Page 212: Family book study Guide · 2020-08-02 · የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በዴንቨር የቤተሰብ ጥናት መጽሐፍ Ethiopian Evangelical

16 ክፍል

ማስመለጥ ስንችል በቅድስና ኖረን የክብርን አክሊል መልበስ እንችላለን።

እንደዚሁም በጾታ እኩልነት ስም የእግዚአብሔርን ቃል በመቃወም

የተነሱ አስተምህሮዎችን ጤናማ የሆነውን የፍቅር መተሳሰብ፣ መከባበር እና

አንዳቸው ለአንዳቸው ዋጋ እየከፈሉ የሚኖሩበትን ትዳር በማሳደግ እና

እበልጣለሁ የሚል አጉል ትምክህት ለውድቀት የሚያዘጋጅ የትዕቢት

አስተሳሰብ መጣል ይገባል፡፡ በዚህም ቤታችንን በሥርዓት ለመምራት

የተሰጡንን ጸጋዎች ተጠቅመን በቤታችን ባሕል ከመደሰት በተጨማሪ

ልናስተካክል የሚገቡንን በእርጋታ ከማስተካከል ይልቅ ሴቶች እናትነትን እና

በቤት ውስጥ መሥራትን እንደ በደል ከማሰብ ባሎችን ጨቋኝ አድርገው

ከማሰብ ለትዳር መናጋት ከመድረሳቸው በፊት እንደ እግዚአብሔር ቃል

የሆኑና ጤናማ አስተምህሮዎችን በማየት በጽድቅ እና በፍርሃት ለመኖር

መትጋት እንችላለን።

212 ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ቤተሰብ